ወረራ ተፈፅሞብናል “የክተት ጥሪ“፣ የአማራ ክልል አዋጅ | ዋርካው ምሬ በህወሃት ላይ ተነሳ – ከፍተኛ ቁጥር ያለው 2 ክ/ጦ ተቀላቀላቸው |

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም “ዳኛው ይነሱልኝ” ብሎ በመጠየቁ አንድ ሺሕ ብር እንዲቀጣ ተፈረደበት

1 Comment

  1. አስገራሚው የሃበሻ ፓለቲካ ማጥ ውስጥ እንደገባ ካሚዩን ጭቃና አፈር እየረጨ ባለበት ይሽከረከራል። 4ኛው የወያኔ ወረራ ይኸው ጀመረ። የጌታቸው ረዳ መግለጫና የጄ/ታደሰ ወረደ ድንፋታ ልክ እንደበፊቱ ተወረርን እየመከትን ነው በማለት ወረራውን ሲያጧጡፉ፤ በኢሮብና በዛለአምበሳ ግንባር ያሉትን የትግራይ ተወላጆች ኤርትራዊ ሁኑ፤ ለውትድርና ተመዝገቡ ያለበለዚያ መሬቱ የኤርትራ ከሆነ ወደ ሃገራችሁ ሂድ እያለ የሻቢያ ካድሬ ሲለፈልፍ መስማት እጅግ ያስመርራል። ሻብያና ወያኔ ልበ ውልቆች ናቸው። ስብዕናቸው ተሟጦ ምስጥ በበላት መሬት ላይ የቆሙ በድኖች። አሁን ማን ይሙት የኤርትራ የኢትዮጵያ የሚባል መሬት አለ? ይህ ድንበር ባህር ተሻግረው ሃገርን ለራስ ለማድረግ የጣሩ የውጭ ሃይሎች ያሰመሩት መከፋፈል እንጂ ይሄ ያንተ ያ የእኔ የሚባል ነገር የለም። እነዚህ ብሄርተኛ ቡድኖች ያለ ጦርነት መኖር ስለማይችሉ በየቀኑ ሰውን እያስገደድና እያስፈራሩ ወደ እሳት ለመማገድ ማዘጋጀት ከተፈጠሮ ጀምሮ የቆየ ባህሪያቸው ነው። እዚህ ላይ ነው የብልጽግናው መንግስት የውጭ ታዛቢዎችን አስገብቶ ወያኔና ሻቢያ የሚያደርሱትን ግፍና ገመና ለዓለም ህዝብ ማሳወቅ ሲገባው ወያኔንና ሻቢያ በመለማመጥ ጊዜውን የሚያቃጥለው። ወያኔና ሻቢያ ለኢትዮጵያ ህዝብ የለየላቸው ጠላቶች ናቸው። ጊዜ ሂዶ፤ ጸጉራቸው ቀለም ለውጦ ወይም ተመልጦ አይናቸው ደብዝዞ አንድ እግራቸው መቃብር ላይ ቆሞ እንኳን የንጽሃንን ደም ከማፍሰስ ወደኋላ አላሉም። ተፈጥሮአቸው ጽልመታዊ ነውና! ዛሬም ውጊያ ትላንትም ሞት!
    የፌዴራሉ መንግስት ጉረኛውን ሻቢያን ከትግራይ መሬት በግድም ሆነ በውድ ሊያስወጣው ይገባል። ልክ እንደ ዘመቻ ጸሃይ ግባት ወገቡን ሲመታ ለዓለም መንግስታት አድኑኝ በማለት እንደሚጮህ የታወቀ ነው። ግፈኛው ወያኔ ጥላቻውና ውጊያውን ከአማራ ህዝብ ጋር ከማድረግ ይልቅ የነፍስ አባቱን ሻቢያን ቢወጋው የተሻለ ምርጫ ነበር። ግን የምናወራው የሃበሻ ፓለቲካ አይደል? ወያኔና ሻቢያ በሚስጢር እንደገና ቂጥ ገጥመው እንደሆነ ማን የሚያውቅ አለ?
    አሁን የአማራውን ምድር እሳት የሚለቁበት የፋኖና የፌዴራል መንግስት ሃይሎች በወያኔው 4ኛ ወረራና በሻቢያው ድንፋታ የሚሉት ምን ይሆን? የሚያስገርመው ቆራጥ መሪ ቢኖር ኑሮ አሁን ላይ ትግራይ የሰላም ምድር በሆነች ነበር። ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው የአብይ አመራር በውጭ ሃይሎች ማስፈራሪያ እየተለወሰ ይኸው እንሆ የሰላም ውል የሚባለው ነገር ሁሉ አፈር ላይ ወደቀ። አሜሪካ ባላት ረጅም እጅና ሃይል ዓለምን ማስፈራራቱ አይቀሬ ነው። ቆርጦ ግን እናንተን አንሰማም በማለት እርምጃ ወስዶ ነገሮችን ለለወጠ ሃይል እጅ እንደሰጡ ታሪክ ያሳያል። አሜሪካኖችን ማመን ወይም የእነርሱን ምክር መስማት መደንቆር ነው። ዪክሬን እነርሱን ተማምነው አሁን ወገቤን ሲሉ ራሺያ በመገስገስ ላይ ትገኛለች። ስለሆነም ብልጽግና በእስራት ላይ ያሉ የኢትዮጵያን ቁርጥ ልጆችን ሁሉ በመፍታት፤ በውስጥ ለወያኔና ለሻቢያ በንግድ፤ በትምህርት፤ በሥራና በሌላ በኩል የስለላ ሰራተኞችና ደጋፊዎችን በመመንጠርና ወደ ናፈቁት ስፍራ በመሸኘት ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔንና ሻቢያን ስፍራቸውን በማስያዝ ህዝባችን በሰላም አብሮ እንዲኖር ማድረግ ይኖርበታል። ሻቢያና ወያኔ እያሉ ምድሪቱ ሰላም አታገኝም። ስለዚህ ከመቀሌም ሆነ ከአዲስ አበባ በወያኔ ሰዎች ስለ ወረራው የሚነገረው ተቃራኒ ወሬና መግለጫ ሁሉ ሆን ተብሎ የሚደረግ እንጂ የዘፈቀደ ስሌት አይደለም። Confuse and Diffuse ነው መርሆቻቸው። ለወያኔ ወረራ፤ ለሻቢያ መስፋፋት ማንም ሰው ህይወቱን ሊሰጥ አይገባም። ለተጠቃለለና ዘርና ቋንቋን፤ ሃይማኖትን ባልተደገፈ እይታ ስብዕናን ተላብሶ እነዚህን ሁለት የሙታን ቡድኖች መፋለም ግን ፍትሃዊ ነው። በዚህም ተባለ በዚያ ግን ምድሪቱ ከመገዳደል አዙሪት አትወጣም። ውጊያው እኛው በእኛው የለኮስነው በመሆኑ አንድ አንድን እያጠቃ ዝንተ ዓለም እንደተገዳደልን መኖራችን አይቀሬ ነው። አይ የእኛ ህዝብ ውስልትናው ብዛቱ አሁን ማን ይሙት ወያኔና ሻቢያ ጀግኖች ተብለው መወደስ ነበረባቸው? ግን ያኔ ንጉሱን ሺህ ዓመት ንገስ ይሉ የነበሩት ደርግ ከቤ/መንግስት ሲያስወጣቸው ሌባ ሌባ እያለ አይደል የጮኸባቸው? ያን ትውልድ ደርግ መነጠረው? የአሁኑን ትውልድ ደግሞ ሻቢያና ወያኔ ከብልጽግናና ብልጽግናን የሚፋለሙት ብሄርተኞች በዚህም በዚያም እያሳበቡ እያመነመኑትና እየማገድት ይገኛሉ። ሰንካላ ፓለቲካ። ሁልጊዜ ኡኡታ፤ ገደልኩት እንጂ ሞተብኝ የማይል። አይ ሃገር… ቀጥሎ የሚሆነውን ቆይተን እንይ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share