በገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)
ኢትዮጵያ ውስጥ ቴክኒካል ተጫዋቾችን አሰልጣኞች የጉልበትና የፍጥነት ስልጠና መስጠት ብዙ ተጫዋቾችን ችሎታቸው እንዲጠፋና ከሁለቱም (ከጉልበቱም ከቴክኒኩም) እንዳይሆኑ አድረገዋቸዋል፡፡የኛ ተጫዋቾች በቴክኒክ ጥሩ መሆናችውን እኛ ብቻ ሳንሆን ከውጪ የመጡ አሰልጠኞች የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ያለን ቴክኒኩ ነው፡፡ ይህንን ችሎታችንን በስልጠና የሚያሳድግልን ነው ያጣነው፡፡ ባለን ነገር ሰርተን ጥሩ መሆን እንችላለን፡፡ አሰልጣኞቹ ያለንን የቴክኒክ ችሎታ አጥፍተው በሌለን የጉልበት ጨዋታ እነድንገባ ነው ያደረጉን፡፡ በጉልበት ደግሞ እንደማንችል የትላንቱ ውጤታችንና መበለጣችን ምስክር ነው፡፡ እኛ ከቡርኪናፋሶ ከመጫወታችን በፊት ዋናው አሰልጣኝ በሬዲዮ ፋና ‹‹ ቡርኪናፋሶን በጉልበት ስለማንችል ኳስ ይዘን አጭር ኳስ ተጫውተን ውጤት እናመጣለን፡፡ ምክትሉም በ97.1 ቴክኒኩ ስላለን በአጭር ኳስ ተጫውትን እንበልጣለን ኡለን። ነገር ግን የመረጧቸው ተጫዋቾች ለጉልበትና ፍጥነት የሚሆኑ ናቸው ግን ተጋጣሚያችን በጉልበት የተሻለ እንደሆኑ አሰልጣኞቻችንም ስለመሰከሩ ጉልበትም አልቻሉም፡፡ ኳስ ይዘን እንጫወታልን ሲሉ ለዚህ የሚሆን ተጫዋች መርጠው ለዚህ የሚሆን ስልጠና ሰጥተው(ካወቁበት) ወደ ሜዳ መግባት ይችሉ ነበር፡፡ ቡድን ውሰጥ 5 ነጣቂ ተጫዋች ነው ያለው፡፡ ተጫዋቾቹ ነጥቀው ለባለጋር ተጫዋቾች ነው የሚሰጡት፡፡ ዳዊት እስጢፋኖስ ለምን እንደማይሰለፍ ሲጠየቁ ተጋፍቶ መጫወትና ኳስ መንጠቅ አይችለም የሚል ምላሽ ነው የሰጡት፡፡ የኛ ቡድን ትልቁ ችግሩ ኳስ በትክክል የሚሰጥ ነው ፡፡ ዳዊት ኳስ መንጠቅ ቢችልና ማቀበል ባይችል ይሰለፋል፡፡ ዋናው ትኩረቱ በትክክል ማቀበል ሳይሆን መንጠቁ ነው የሚፈለገው፡፡ ዳዊትን የመሰሉት በስልጠናው ላይ ያላቻውን ችሎታ ሳይሆን የሌላቸው እንዲየዳብሩ ነው ስልጠናው የሚሰጠው ፡፡ የሌላቸው ችሎታ ማለት በጉልበት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ በጉልበት ሲገቡ ደግሞ እንደ ቡርኪናፋሶ፣ ናይጄሪያ እንዲበልጡን ማድረግ ነው፡፡ እኛ ብንጫውትም ያለንነ ቴክኒክ አሳድገን መጫወት ስንችልነው፡፡ ህፃናት ሰፈር ውስጥ የቴክኒክ ችሎታቸውን ነው የሚያሳዩት፡፡ ይህ የተፈጥሮ ችሎታ ነው፡፡ ማንም አሰልጣኝ አላስተማራቸውም ፡፡ ይህ የተፈጥሮ ችሎታቸው በስልጠና የሚሳድግላቸው ሰው ነው ያጡት ፡፡ አሁን ያሉት አሰልጣኞች በተፈጥሮ ወደ ሌላቸው የሃይል ስራ ነው የሚወስዷቸው፡፡
ሰይፈ ውብሸት ቤቴክኒክ ችሎታ የተዋጣለት ነበረ፡፡ ይህ ተጫዋች ያለውን ችሎታ ከማሳደግ ይልቅ ወደ ኃይል ጨዋታ አስገቡት ያለውንም አጠፉበት፣ባሰለጠኑትም ነገር ውጤታማ አልሆነም፡፡ ከሁለቱም ሳይን ቀረ፡፡ ብርሃኑ ፋዲጋ በአዲስ አበባ ታዳጊ ቡድን ሲጫወት ሳየው ተአምረኛ ተጫዋች ነበር ፡፡ አብዶ አሰራሩ፣ ኳስ አሰጣጡ፣ በዚያ እድሜተው የማይጠበቅ ነው፡፡ ወደ ክለብ ሲገባ የኃይል ስራ ውሰጥ አስገቡት በኢንተርናሽናል ጌም ብቻ ለብቻ ሲገናኙ ብልጫ መውሰድ አልቻሉም፡፡ ተጫዋቹ ወደ ኃይል ሲገባ ብቻውን እንዲገኝ ነው የሚፈልገው፡፡ በቴክኒኩ ከሆነ ግን ከጋደኛው ጋር ተረዳድቶ ስለሚጫወት ብልጫ መውሰድ ይችላል፡፡ አሰልጣኞቹ ግን ተጫዋቾቹ ያለውን የተፈጥሮ ችሎታ ያጠፉና በጉልበት ስራ አስገብተው ብቻውን እንዲገኝ አድረገው ብልጫ እንዲወሰድብን አድርጓል፡፡ ተጫዋቹ ከሁለቱም አይሆንም የቡድኑም ውጤት ደካማ ይሆናል፡፡ አሰልጣኞች ስንቱን ተጫዋች ነው ያለውን ችሎታ አጥፍተው ወደ ማይችለው ያስገቡት፡፡