ለአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጉዞ ጥናታዊ ፅሁፍ መነሻና መንደርደሪያ የሚሆን ግንዛቤ፣

//

ያልተነገሩ የአማራ ህዝብ ተረቶችን፣ ሚስጢራዊ እና የተረሱ ታሪክን ስንመረምር ስለ አማራ ህዝብ ያለን እወቀት እያደገ ይሄዳል።

  • 70% በላይ የአፍሪካ ሰንሰላታማ ተራሮች መገኛ መሆኑ ፣ ውብ መልከአ ምድሩ፣ ዝናባማነቱና የወንዞች መፍለቂያ መሆኑ፣ በድንቅ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት መስጊዶች ያጌጠ መሆኑ፣ ለምለምና ደጋማ የኢትዮጵያ ምድር የሚገኝበት በመሆኑ የአማራ ህዝብ በባህል ካሴት የሸመነ አስደናቂ የታሪክ ምንጭ ሊሆን ችሏል።

የታሪክ መሠረቶቻችንን በማሰስ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የአማራ ህዝብ መሆኑን እንገነዘባለን። ይህም ለኢትዮጲያውያንም ሆነ ለአማራ ህዝብ አስደናቂ የእውቀት ፍንጭ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚህ የብሎግ ጽሁፍ ላይ እንደ ሪቻርድ ኬይር ፔቲክ ፓንክረስት፣ ኤድዋርድ ኡልንዶርፍ፣ ተድላ መላኩ ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑና በፕሮፌሰር አደም ካሚል ታዋቂ ምሁራን የአማራን ህዝብ የዳበረ ታሪክ በመግለጥ አጓጊ የአማራን ታሪካዊ ጉዞ እንመለከታለን።

በተጨማሪም የፈርስት ሂጅራ ሙስሊሞች ወደ አቢሲኒያ /ኢትዮጲያ ያደረጉትን ስደት ጉልህ ክስተት እና በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ገጽታ ላይ ያሳደረውን ትልቅ ተፅእኖ በጥልቀት እንመረምራለን።

 

የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ስር መሰረቶች

የአማራን ህዝብ ለመረዳት መጀመሪያ ታሪካዊ ስረ መሰረቱን ልንመረምር ይገባል። ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅ አማራው የራሱ የሆነ የባህልና የቋንቋ ቅርስ አለው።

እንደ አክሱም እና ዛግዌ የመሰሉት የታወቁ መንግስታት እና ኢምፓየሮች አማራው በትልቅ ደረጃ ከፍ ብሎ ለዘመናት ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳዳሪ እንዲሆን መሠረት ጥለዋል።

የአማራ ማንነትን በመፍጠር የባህልና የሃይማኖት እውቀቶችም ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና አኗኗራቸውን የሚገልጽ መንፈሳዊ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ከጋራ ንቃተ ህሊናቸው ጋር የተሳሰረ ወሳኝ የታሪክ መሠረቶችን አስቀምጠዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔ በአብይ አህመድ የተሳሳተ፣ ደካማ አመራር እየተመራ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት ሊያሸንፉ ይችላሉ

ከመጀመሪያው ሂጂሪያ ጀምሮ እስልምናን በመቀበል የኢትዮጲያው ሰለሞናዊ የአማራ ንጉስ ከመካ ቀጥሎ ከአለም ሁለተኛ ቀዳሚ የእስልምና ተከታይ አድርጎናል። ይህም በመሆኑ ኢትዮጲያ በነቢ መሀመድ የተመረቀች አገር ስትሆን በኢትዮጲያ ላይ የጅሀድ ጦርነት ማድረግ የተከለከለ መሆኑን የነቢ መሀመድ መለከታዊ ቃል በሀዲስ ተመዝግቦ ይገኛል።

ይህ እጅግ ፍትሀዊነትና ጥበብ የተሞላበት ዲፕሎማሲያዊ ድል የተገኘው በሰለሞናዊው የአማራ ነገስታቶች ታላቅ አዋቂነት ነው።

የአማራ ህዝብ የክርስቲያንና የእስልምና ተከታዮች በጋራ የሚገኙበት ከመሆኑም በላይ በመጀመሪያው ሂጅሪያ ዘመን የኢትዮጲያው ንጉስ በዘር ሀረጋቸው አማራ በመሆናቸው ይህ ታላቅ ውለታ በሙስሊሙ አለም በይፋ እንዲታወቅ ማድረግ ጠቃሚ ነው።

(Richard Keir Pethick Pankhurst)

ታሪካዊ ቅርሶችን በማሰስ የአማራን ያለፈ ታሪክ ለመግለፅ ህይወታቸውን ከሰጡ ፈር ቀዳጅ ምሁራን አንዱ ሪቻርድ ፓንክረስት ናቸው።

ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የታሪክ መዛግብትን እና የአርኪዮሎጂ ግኝቶችን በማውጣት ያደረጓቸው ጥናቶች በአማራ ባህልና የተረሱ ገፅታዎች ላይ ብርሃን ፈንጥቀዋል።

የፓንክረስት ስራ ስለ አማራ ህዝብ ያለንን ግንዛቤ ከማሳደጉም በላይ በታወቁ የታሪክ ዘገባዎች ሲሸፈኑ የቆዩ ታሪኮችንም ወደ ፊት አምጥተዋል።

 

ኤድዋርድ ኡለንደርፍ እና ልጅ ተድላ መላኩ፡

 

Edward Ullendorff

ኤድዋርድ ኢለንደርፍ ቋንቋና ባህላዊ ቅርሶችን በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

ኤድዋርድ ኡለንደርፍ በአማራና በአማርኛ ስነጽሁፍ ላይ ያደረጉት ምርመራ ስለ አማራ ማንነት እና አገላለጽ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖርን የሚያስችል ወሳኝ የቋንቋችንን ግንዛቤዎችን ሰጥተውናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ልጅ ተድላ መላኩ የቃል ወጎችን እና አፈ ታሪኮችን በማስረጃ በማረጋጠጥ ረገድ ያደረጉት ጥረት በዋጋ ሊተመን የማይችል የባህል እውቀት እንዳይጠፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ከለውጥ ሃይሉ በበለጠ የለውጥ አደናቃፊ እየሆነ ያለው የልሂቃን ያልተገባ መቆራቆስ ነው! - አበጋዝ ወንድሙ

ልጅ ተድላ መላኩ

ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑ፡ የአማራን ታሪክ እንደገና በመተንተን ለንባብ መፅሀፍ አቅርበዋል

ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑ ከቀደምቶቹ ስራ በመነሳት የአማራን ታሪክ እንደገና የመግለጽ ካባ ወስደዋል።

በአማራ ታሪክ እና ባህል ላይ ያደረጉት ጥናት ቅድመ-ግምቶችን እና አመለካከቶችን የሚፈታተን ሲሆን ይህም ስለ አማራ ህዝብ የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖረን አድርገዋል።

ግርማ ብርሃኑ በተለይ በዲያስፖራው ላይ ትኩረት በማድረግ የአማራ ማህበረሰቦች ከኢትዮጵያ ውጭ ያለንን ግኑኘትና አስተዋፅዖ በማጉላት ስለአማራ ማንነት ያለንን ግንዛቤ የበለጠ እንዲጨምር አድርገዋል።

 

(First Hijra) የመጀመሪያው ሂጅራ፡ ሙስሊሞች ወደ አቢሲኒያ መሰደዳቸው

ከአማራ ህዝብ ታሪካዊ ዳራ አንፃር የፈርስት ሂጅራ – የሙስሊሞችን ወደ አቢሲኒያ መሰደድ ያለውን ጠቀሜታ ልንዘነጋው አንችልም።

ይህ አንገብጋቢ ክስተት የተከሰተው በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሙስሊሞች ከመካ ወደ ኢትዮጲያ በተሰደዱበት ዘመን ነው።

ሰለሞናዊና የአማራ የዘር ሀረግ ባላቸው በንጉስ ትመራ በነበረችው አቢሲኒያ ወይም ኢትዮጲያ ፍትሃዊ አገርና መንግስት ውስጥ መሸሸጊያ ቦታ ባገኙበት ወቅት ነው።

የመጀመሪያው ሒጅራ የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ገጽታ በመቅረጽ አብሮ የመኖር እና የባህል ልውውጥ ስሜትን በማጎልበት ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

 

በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የተለያዩ ማንነቶች

የአማራን ህዝብ ታሪክ እና የፈርስት ሒጅራ ታሪክ ስናሰላስል በኢትዮጵያም ሆነ በአማራ ህዝብ ውስጥ ለተፈጠሩት ልዩ ልዩ ማንነቶች እውቅና መስጠት አስፈላጊ ሆኖ እናገኛዋለን ።

በአማራ ህዝብ ውስጥ በክርስቲያንና በሙስሊም ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ትስስር በመገንዘብ የሀገሪቱን የባህል እሴት ብልጽግና መቀበል ተገቢ መሆኑን እንረዳለን።

ማጠቃለያ፡

በአማራ ህዝብ ጉዞ በድልም ሆነ በፈተና የተሸመነ ያለፈ ታሪክን ይፋ አድርገናል። እንደ ሪቻርድ ፓንክረስት፣ ኤድዋርድ ኡለንዶርፍ፣ ልጅ ተድላ መላኩ እና ፕሮፌሰር ግርማ ብርሃኑ ያሉ ምሁራን ያደረጉትን በዋጋ ሊተመን የማይችል ምርምር የአማራ ማንነትን ዘርፈ ብዙ ተፈጥሮ እንድናደንቅ አስችሎናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በበርካታ ሱዳናውያን እየተተፋ ያለው ሌ/ጄነራል አብዱል-ፈታህ አል-ቡርሃንና በአል-ቡርሃን እየተነዳች ያለችው ሱዳን አሁናዊ ገጽታ - ጌታቸው ወልዩ (ከሜክሲኮ ባህረ-ሰላጤ)

የእውቀት እና የማስተዋል ጉዟችንን ስንቀጥል ከአማራ ህዝብ ቅርስ እና የሙስሊሞች ወደ አቢሲኒያ/ኢትዮጲያ የስደት ታሪክን ተመስጦ የማወቅ እና የመተሳሰብ መንፈስን እንድናዳብር ግንዛቤ አግኝተናል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ ሞዛይክ የሚቀርጸው አንድነት፣ የባህል ጥበቃ እና የመከባበር ትሩፋት ላይ የየበኩላችንን ጥረት ስናደርግ ህብረታችን ይጠነክራል ።

ምንጮች ፣

 

የሚከተሉትን መፅሀፍቶችና ዌብ ሳይት ያንብቡ።

ፐሮፌሰር አደም ካሚል በኢትዮጲያ ሙስሊሞች ታሪክ ያደረጉት ንግግር በዩቱብ ያዳም

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Migration_to_Abyssini

ክብረ አምሓራ የማንነታችን አምድ በልጅ ተድላ መላኩ

ፍኖተ አማራ በፕሮፌሰር ግርማ ብርሀኑ

EDWARD ULLENDORFF

An Amharic

Chrestomathy

a collection of

Amharic passages

 

together with an introduction

grammatical tables

ETHIOPIAN REMINISCENCES

Early Days

RICHARD AND RITA PANKHURST

1 Comment

  1. እንግዲህ ምን ትሆን ያማራቅ ታሪክ እክል ነገረኝ ከቅድመ አያቴ ሰማሁ የምትለው ሳይሆን አለም አቀፍ እውቅና ያገኘ ተሰንዶ የተቀመጠ ወዲያ ወዲህ የማያስብል አጥፍተህ አትጨርሰውም። ባይመችህም ተቀበለው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share