October 1, 2023
12 mins read

ከአማራ ፋኖ፣ ከኢትዮጵያ ፋኖ፣ ይድረስ ለሎንዶን ፋኖ!!! ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

5688966979 1 1

5688966979 1 1ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን ለመሸጥና የጦር መሳሪያዎች ለመግዛት በሎንዶን ከተማ  በ9 ኦክቶበር 2023እኤአ ቀጠሮ ይዘዋል፣ በሠልፍ እናክሽፈው!!!

Ethiopian Investment Summit scheduled for Monday, 9th October 2023.

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ Ethiopian Investment Holdings (EIH) የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሃብት ምንጭ ቌት ሲሆን የመንግሥታዊ ልማታዊ ድርጅቶች ለምሳሌ የመንግስታዊ ካንፓኒዎች ሃብት ሽያጭ ንብረትና ኃብት ስርጭትና ድልድል ስትራቴጂ ለመቀየስ የተመሠረተ በአብይ ዘመን የተቌቌመ ድርጅት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በስሩ የሚገኙትን መንግሥታዊ ኢንተርፕራይዞች ለመሸጥ የወደፊቱን የሃገሪቱ ኢንቨስትመንት ምንጭ ይሆናል ተብሎ የተቆቆመ ድርጅት ነው፡፡ አብዱራህማን ኢድ ጣሒር የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ  ፕራዜዳንት ለኤዥያን ኢንቨስተር በሰጠው ቃለ ምልልስ መሠረት ‹‹ኢንቨስትመንት ጀምረናል፣ የተለያዩ አማራጮችንና ተስፋዎች አሉን›› በሚቀጥሉት አመታት ውስጥ የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶችን በከፍተኛ ፍጥነት ሽያጭ እናከናውናለን፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በስሩ ባሉ ሃያ አራት ኢንቨስትመንት፣ የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶች ውስጥ የሚተዳደሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር Public Enterprises Holding and Administration (PEHA) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ኢትዮፖስት(ፖስታ ቤት)፣ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት፣ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (ሜቴክ)፣ ንብረቶችን ጠቅልሎ ከ150 (መቶ ሃምሳ ) ቢሊዮን ዶላር  በላይ ኃብትና ንብረት ያለው ድርጅት ሲሆን ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ሚኒስትር ኮነሬል አብይ አህመድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በነደፈው የአምስት አመት ኢንቨስትመንት ፕላን መሠረት፣ ከፊሉን የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ ኢንቨስተሮች የማዘዋወር መርሃግብር በመዘርጋት፣  ከሽያጩ የገንዘብ ኃብት በማሰባሰብ ለሌላ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በግብርና፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ሪል ስቴት፣ ላይፍ ሳይንስና ሎጂስቲክስ አገልግሎት  ለማዋል ታቅዶል፡፡ በቦርድ ግን ገና አልፀደቀም፡፡

የኮነሬል አብይ መንግሥት በአፍሪካ ኢንቨስት አድርጉ በ2023እኤአ በኢትዮጵያ- ‹‹በአዲሱ የንግድ መዕከል፣ በሮቹ ተከፍተዋልና እድሎች ተፈጥረዋል፡፡›› በሚል  መርህ የኢትዮጵያ ልዑካኖች ብድን የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት አውቶሪቲ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ የኢትዮጵያ ሴኩሪቲ ኤክስቼንጅና፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑካን ብድን ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት በዓለም ባንክና በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የብድርና እርዳታ ማዕቀብ ተጥሎበታል፡፡ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ከትግራይ ክልል ጦርነት ወጥቶ በአማራ ክልል ጦርነት በማድረግ የሃገሪቱን በስብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በመዳረግ ኢኮኖሚውንም መቀመቅ ውስጥ ከቶታል፡፡ ኮነሬል አብይ ለጦርነቱ የሚያስፈልጉትን የጦር መሳሪያዎችና ተተኮሾች ለመሸመት የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶችን ለመሸጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ኢትዮቴሌኮም፣ ኢትዮፖስት፣   ሂልተን ሆቴል፣ ጊዮን ሆቴል ወዘተን ለውጭ ኢንቨስተሮች በሽያጭ አቅርቦ በመሸጥ ጦርነቱን ለማሸነፍ ጎምጅቶል፡፡ የኢትዮጵያዊያኑን አንጡራ ኃብት ለጦርነት ለመዳረግና ሥልጣኑን ለማቆየት ይሻል፡፡ በኢትዮጵያና ትግራይ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኃብትና ንብረት ወድሞል፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት ከዚህ ስህተት ባለመማር በአማራ ክልል ህዝብ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ጦርነት ከቀሰቀሰ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ ጦርነቱ እንዲያበቃ የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶችን ለመሸጥ የሚደረገውን ሙከራ ለዓለም ህብረተሰብ በሠላማዊ ሠልፍ በማጋለጥ ውድቅ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ  ጉዳይ ነው፡፡ የኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል  የመንግስት ልማታዊ ድርጅቶችን የመሸጥ እቅድ ለማስቆምና ለማገድ በተባበሩት መንግሥታት፣ በአፍሪካ ህብረት፣ በአውሮፓ ህብረት ለአሜሪካ መንግሥት ለሚመለከተው ሁሉ ደብዳቤ ማስገባት ያስፈልጋል እንላለን፡፡ የሎንዶን ፋኖዎች ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ተወጡ እንላለን፡፡ የባህር ማዶ ፋኖዎች ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ተወጡ እንላለን፡፡

Ethiopian Delegation to AFSIC – Investing in Africa 2023 Ethiopia – “The New Frontier Market, Opening Doors and Creating Opportunities” By / September 28, 2023 / AMAMedia

LONDON, United Kingdom, 28 September 2022, /African Media Agency/- FSD Ethiopia is coordinating a delegation from Ethiopia to attend AFSIC 2023 and will be sponsoring the Ethiopian Investment Summit scheduled for Monday, 9th October 2023. FSD Ethiopia is a development agency that aims to support the development of accessible, inclusive, and sustainable financial markets for economic growth with a vision to contribute to a thriving financial system that delivers real value to the broader economy and to the people of Ethiopia.

The Ethiopian delegation includes the key financial sector actors, including the Ministry of Finance, Ethiopian Capital Market Authority, Ethiopian Investment Holdings, Ethiopian Securities Exchange, and Ethiopian Investment Commission– a truly comprehensive grouping and an exciting agenda item to look forward to.

The Ethiopian summit is organized under the theme “Ethiopia – The New Frontier Market, Opening Doors and Creating Opportunities”. The summit aims to provide a comprehensive overview of Ethiopia’s emerging opportunities and highlight Ethiopia’s recent economic reforms, favorable investment climate, and growing investment opportunities. The high-level officials in the panel will discuss significant developments strengthening Ethiopia’s financial architecture. The event will feature a road show to raise capital for the recently established Ethiopian Securities Exchange (ESX). ESX will highlight opportunities for forming strategic partnerships with financial actors in Africa and beyond. Ethiopia investment holding aims to attract investors and inform global finance practitioners of Ethiopia’s capital market and opportunities. ………(1)

Subscribeየኢትዮጵያን  ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን› ፕራይቬታይዝ የሚያደርግ በትንሹ ሃምሳ ካንፓኒዎችን ስም ዝርዝር በኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ (ESX) በሚቀጥለው ሁለት አመት ውስጥ በግልፅ እንደሚጀመር ተገልጾል፡፡ ኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ የጋራ ፕሮጀክት ሲሆን  በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (Ethiopia Investment Holdings (EIH))፣ የገንዘብ ሚኒስቴርና፣መሠረቱን ናይሮቢ ያደረገው ፋይናንሻል ሴክተር ዲፕኒንግ አፍሪካ (Financial Sector Deepening Africa (FSDA)) በጋራ ፕሮጀክቱ መረጃ መሠረት የኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ ከ25 እስከ 55 በመቶ  ድርሻ የሚሸጠው ለኮርፖሬሽኖች፣ ካፒታል ማርኬት፣ ኢንተርሚዲአርሪስና ኦፕሬቶርስ ኦፍ ኢንተርናሽናል ሴኩሪቲስ ኤክስቼንጅስ ሲሆን የመንግስት ድርሻ ከሃያ አምስት በመቶ እንደማይበልጥ ተገልፆል፡፡ በ2021እኤአ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (EIH))፣ በስሩ የሚቆጣጠረው ንብረትና ኃብት $38bn (የሠላሳ ስምንት ቢሊዮን ዶላር)  ወይም 34% (ሠላሳ አራት በመቶ) የኢትዮጵያን ጂዲፒ ኃብት ሲሆን በዚህም የሚያመነጨው አመታዊ ገቢ $6.2bn.(ስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር) ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ትልልቆቹ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን› ፖርትፎሊዮ ውስጥ የኢትዮጵያ አየርመንገድ፣የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮቴሌኮም መሳሰሉት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር ሆነው ኢኮኖሚውን ነፃና ክፍት በማድረግ ጎዳናውን በመጥረግ የፕራይቬታይዤሽኑን ሽያጭ ያሳልጣሉ፡፡ “At least 50 companies are expected to list on the Ethiopian Stock Exchange (ESX), set to launch in two years. The ESX is a joint project between the country’s giant new sovereign wealth fund, Ethiopia Investment Holdings (EIH), Ministry of Finance and Nairobi-based Financial Sector Deepening Africa (FSDA). Between 25% and 55% of the ownership of the ESX will be for corporations, capital market intermediaries and operators of international securities exchanges, while government will not own more than 25%. Meanwhile, the establishment of EIH, one of Africa’s biggest sovereign wealth funds, could be the start of a massive turnaround in Ethiopia’s long-established economic heterodoxy. It was set up in late 2021 and will control assets worth some $38bn, or 34% of Ethiopia’s GDP, generating annual revenues of $6.2bn. It has some of Ethiopia’s largest and most productive state-owned enterprises in its portfolio, such as Ethiopian Airlines, the Commercial Bank of Ethiopia or Ethio Telecom, and with its active participation in the establishment of the country’s first securities exchange, is likely to pave the way for the liberalization of the economy and increase the pace of privatization.”

SOURCE: NORTH AFRICA POST……………………….(2)

 

ምንጭ

 

 

 

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ የፕራይቬታዜሽን ጨረታ ይታገድ!!! – ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Lisane Gufuan 2 1
Previous Story

የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ፀጋዬ እሸቴ በግፍ መታፈን አስመልክቶ ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

christian and Yohanes 1 2
Next Story

በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በመንግስታዊ እገታ ሥር የሚገኙት እነ ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቦያለውን ጨምሮ ሌሎች የማንነት፣ የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ከነገ ጀምሮ የርሃብ አድማ እንደሚያደርጉ ገለጹ፤

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop