February 8, 2013
10 mins read

በናይጄሪያ እዚህ መድረስ የብሄራዊ ቡድናችንን ብቃት መለካት ይችላል?

ከቦጋለ አበበ

በሃያ ዘጠነኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሦስት ተደልድለው የነበሩት ናይጄሪያና ቡርኪናፋሶ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆናቸውን አረጋገጠዋል። ናይጄሪያና ቡርኪናፋሶ በአፍሪካ ዋንጫው ግምት ያልተሰጣቸው ሀገሮች ቢሆኑም ባልታሰበ ሁኔታ ጫፍ መድረስ ችለዋል።

ናይጄሪያና ቡርኪናፋሶ በምድብ ጨዋታቸው ከኢትዮጵያና ከአምናዋ ሻምፒዮን ዛምቢያ ጋር ተደልድለው ወደ ሩብ ፍፃሜ ቢያልፉም ግማሽ ፍፃሜ ይደርሳሉ ብሎ የገመተ አልነበረም።ይሁን እንጂ ሁለቱ ሀገሮች ከግማሽ ፍፃሜም አልፈው የዋንጫ ተፋላሚ መሆን ችለዋል።

ናይጄሪያ በተለይም በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የአፍሪካ እግር ኳስ ቁንጮ የሆኑትን ኮትዲቯሮችን ጥላ ግማሽ ፍፃሜ ትደርሳለች ብሎ ማሰብ አዳጋች ነበር።ናይጄሪያ ዝሆኖቹ በመባል የሚታወቁትን የኮትዲቯር እግር ኳስ ወርቃማው ትውልድን እንደማያሸንፉ የተገመተው በመጨረሻ የምድብ ጨዋታቸው ከዋልያዎቹ በገጠማቸው ትልቅ ፈተና ነው።

አረንጓዴ ንስር በመባል የሚታወቀው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከዋልያዎቹ በነበራቸው ጨዋታ ከምድባቸው ለማለፍ ጠንካራ ፉክክር ገጥሟ ቸዋል። ከዋልያዎቹ ከባድ ፈተና የገጠማቸው አረንጓዴ ንስሮቹ በጨዋታ ብልጫ ቢወሰድባቸውም ባለቀ ሰዓት እድል ቀንቷቸው አሸናፊ መሆን ችለው ነበር።ናይጄሪያዎች ዋልያዎቹን አሳማኝ ባልሆነ ጨዋታ አሸንፈው ኮትዲቯርን በሩብ ፍፃሜ ሲገጥሙ ይከብዳቸዋል ቢባልም ኮትዲቯርን እንደማይፈሯትና ከባዱ ጨዋታቸው ከዋልያዎቹ ጋር ያደረጉት እንደነበር በአንደበታቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።

በእርግጥም አረንጓዴ ንስሮቹ የኮትዲቯርን ጠንካራ ስብስብ አሳማኝ በሆነ ጨዋታ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ካሸነፉ በኋላ ነው ከባድ ፉክክር የገጠማቸው። ይህም ፉክክር ከዋልያዎቹ ጋር ያደረጉት ጨዋታ እንደሆነ ነው የተነገረው።

ናይጄሪያ ዋልያዎቹን መግጠማቸው እራሳቸውን እንዲፈትሹ አድርጓቸዋል ማለት ይቻላል።ለእዚህም ቡድናቸው ውስጥ የነበሩ ክፍተቶች ከዋልያዎቹ ጋር ካደረጉት ጨዋታ በኋላ አስተካክለው የማይበገሩ እየሆኑ መምጣታቸውን መካድ አይቻልም።

ናይጄሪያ ከዋልያዎቹ ጨዋታ በኋላ የነበረባትን ድክመቶች አርማ እዚህ መድረሷ ዋልያዎቹ ምንያህል ጠንካራ እንደሆኑ ያሳያል።ይህ ማለት ግን ዋልያዎቹ ድክመት የለባቸውም ማለት ሳይሆን ዋልያዎቹ ቀጥ አርገው ያቆሙት ቡድን ኮትዲቯርን የመሰለ ብሔራዊ ቡድን አሳማኝ በሆነ መልኩ ማሸነፉ ሲታይ ዋልያዎቹን ማድነቅ ተገቢነት ይኖረዋል።

ሰኢዶ ኬታን የመሳሰሉ በአውሮፓ ሊጎች ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር የቻሉ ተጫዋቾችን ያሰባሰበው የማሊ ብሔራዊ ቡድን በናይጄሪያ አራት ግብ ሲገባበት ማየትም ዋልያዎቹን የሚያስመሰግን ነው።ዋልያዎቹ በናይጄሪያ የተሸነፉት አሳማኝ በሆነ ጨዋታ እንዳልነበረ ታይቷል።

ከትናንት በስቲያ በተጠናቀቀው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ናይጄሪያ በማሊ ላይ ፍፁም የበላይነት አሳይታለች ማለት ይቻላል።ማሊ ከኢትዮጵያ አንፃር በእግር ኳስ የተሻለ ደረጃ ላይ የደረሰች ሀገር ብትሆንም ዋልያዎቹ ያቆሙት ቡድን አራት ለአንድ በሆነ ውጤት አሳምኖ ሲያሸንፋት ማየት ዋልያዎቹን ለማድነቅ ያስችላል።

ናይጄሪያ ከአስራ ስምንት ዓመት በፊት የነበራትን የሻምፒዮናነት ክብር ለማግኘት የሚቀራት እሁድ ቡርኪናፋሶን መርታት ነው።አሰልጣኝ ስቴፈን ኬሺም ናይጄሪያ የመጨረሻ የአፍሪካ ዋንጫን ስታነሳ በአምበልነት የሰሩትን ታሪክ አሁን በአሰ ልጣኝነት የመድገም እድል አጋጥሟቸዋል።

አሰልጣኝ ኬሺ ዋንጫውን ለማንሳት ግምት ማግኘት የጀመሩት ኮትዲቯርን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነው።ከማሊ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በፍፁም የበላይነት ማሸነፋቸው ደግሞ የስፖርት ቤተሰቡ ከጨዋታው በፊት ዋንጫ ይገባቸዋል የሚል አስተያየት እንዲጎርፍላቸው አድርጓል።

አሰልጣኝ ኬሺ ማሊን በአሳማኝ ጨዋታ ካሸነፉ በኋላ «ማሊ ጥሩ ቡድን ነው፤ሰኢዶ ኬታን የመሳሰሉ ታላላቅ ተጫዋቾችን አካትቷል፤በተከላካይ ክፍላቸው ላይ የነበረውን ክፍተት ተጠቅመን ማሸነፍ ችለናል »በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።

የማሊው አሰልጣኝ ፓትሪስ ካትሮን በበኩላቸው አሁንም በተጫዋቾቻቸው እንደማያፍሩ ገልጸዋል። «በተጫዋቾቼ አላፍርም፤ ለዋንጫ ለማለፍ ጥረት አድርገናል፤ ከእዚህ በኋላም ጥረታችን ለደረጃ ጨዋታው ይቀጥላል » በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።

ከምድብ ሦስት ወደ ፍፃሜ ያለፈችው ቡርኪናፋሶም በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ያልተጠበቀች ክስተት ሆናለች።ቡርኪናፋሶ በአፍሪካ ዋንጫ ለፍፃሜ ስትደርስ ይህ የመጀመሪያዋ ነው።ከእዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችላለች።

በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሞት ምድብ የተባለው በምድብ አራት ኮትዲቯር፤ ቶጎና የሰሜን አፍሪካዎቹ ሀገሮች ቱኒዚያና አልጄሪያ የተደለደሉበት ነበር።ይሁን እንጂ ከእዚሀ ምድብ እንኳን ለፍፃሜ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰ አንድም ሀገር የለም።

በተቃራኒው በምድብ ሦስት ከዋልያዎቹ ጋር ተደልድለው የነበሩት ቡርኪናፋሶዎችና ናይጄሪያዎች ማንም ሳያስባቸው ከአንድ ምድብ ለፍፃሜ ቀርበዋል።ይህም የሁለቱን ቡድኖች ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን ማራኪ ጨዋታ በማሳየት ጥሩ ተፎካካሪ የነበሩትን ዋልያዎቹን ሌላ ምድብ ውስጥ ተደልድለው ቢሆን ኖሮ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ያስመሰከረ ነው።

ቡርኪናፋሶ ከኮትዲቯር ቀጥሎ ትልቅ ግምት የተሰጣትን ጋናን አሸንፋ ነው ወደ ፍፃሜ ያለፈችው።ጋና በአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ስም ቢኖራትም ለፍፃሜ አልፋ በማታውቀው ቡርኪናፋሶ ከፍፃሜ መቅረቷ አስገራሚ ሆኗል።

ቡርኪናፋሶ የአራት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኗን ጋናን ባሸነፈችበት ጨዋታ በዳኛ በደል ደርሶባታል ማለት ይቻላል።ጋና የተሰጣት ፍፁም ቅጣት ምትና ፒትሮፓ በቀይ ካርድ የወጣበት አጋጣሚ ለበርካታ ተመልካቾች አሳማኝ ሆኖ አልተገኘም።

ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን አለን ትራዮሬን በጉዳት፤ፒትሮፓን በቅጣት በፍፃሜው ጨዋታ የማያሰልፉት አሰልጣኝ ፖል ፑት በበኩላቸው ወሳኞቹ ተጫዋቾቻቸውን ማጣታቸው እንደማያሳስባቸውና ናይጄሪያን አሸንፈው ሻምፒዮን እንደሚሆኑ እርግጠኛ ሆነዋል።

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop

Don't Miss

የሶዶ ፖሊስ ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጸመ

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ‹‹ስቴት ፈንድ›› በሚል በየወሩ የሚሰጣቸው 340
colesterol

health: ስለኮሌስትሮል ሊያውቁ የሚገባዎት 6 ነገሮች

6. ኮሌስትሮልን በጥቂቱ ኮሌስትሮል የሁሉም እንስሳት ህዋሳት አካል የሆነ የማይሟሟ