August 29, 2023
3 mins read

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ 183 ሰዎች መሞታቸውን ተመድ አስታወቀ

ETHIOPIA SECURITY 1 1

ETHIOPIA SECURITY 1 1

በሰሜን ኢትዮጵያ፣ አማራ ክልል፣ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በትንሹ 183 ሰዎች መሞታቸውን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የመብት ጥሰት ተመራማሪዎቹን ጠቅሶ አስታውቋል። ግድያ፣ ጥቃት እና የመብት ጥሰት እንዲቆምም ጠይቋል።

uhhheየመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ቢሮ ቃል አቀባይ ማርታ ሁርታዶ ጄኔቫ ለሚገኙት ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በክልሉ እያሽቆለቆለ ያለው ሰብዓዊ መብት እንደሚያሳስባቸው ተናረዋል።

“በኢትዮጵያ አንዳንድ ክልሎች እያሽቆለቆለ ያለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳስቦናል። በአማራ ክልል፣ በኢትዮጵያ ጦር እና በክልሉ ፋኖ ሚሊሻዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት እና፣ ሐምሌ 28 የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ሁኔታው በጣም ተባብሷል። መስሪያ ቤታችን መሰብሰብ በቻለው መረጃ መሰረት፣ ግጭቱ ሐምሌ ወር ላይ ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ ቢያንስ 183 ሰዎች ተገድለዋል።”

አዋጁ ለባለሥልጣናት፣ ተጠርጣሪዎችን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመያዝ፣ ሰዓት እላፊ ገደብ ለመጣል እና ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ለመከልከል ሰፊ ሥልጣን እንደሰጣቸው የሰብዓዊ መብት ቢሮው ቃል አቀባይ ሁርታዶ ገልፀዋል።

ሁርታዶ በዚህ አዋጅ ስር ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሳቸው ገልፀው “ከታሰሩት ውስጥ አብዛኞቹ የፋኖ ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ወጣቶች ናቸው” ሲሉ አብራርተዋል።

አክለውም “ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በጅምላ የቤት ለቤት ፍተሻ እየተካሄደ ነው። በመሆኑም ባለሥልጣንቱ የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣ ማንኛውም ነፃነት የመንፈግ ተግባር በፍርድ ቤት እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩት እንዲፈቱ እንጠይቃለን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

VOA

1 Comment

  1. ተመድ እና እነ CNN በወያኔ ጦርነት ጊዜ እንዲህ አይነት ዜና ሲሰሩ “ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን” ተብለው ይፈረጁ ነበር። አሁን ደግሞ ለምሰክርንት ዋቢ እየተደረጉ ነው። ቀጥሎስ? “ተመድ ያጣራልን” ይባላል። ይሁና አሉ እትዬ ባፈና፡፡
    ሰላማችን ይብዛ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

369647808 715460857266245 7244258926934520547 n
Previous Story

በሕዝባችን ላይ የማያባራ ሁኔታ የሚፈፀመውን ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የዘር ማፅዳት የዘር ፍጅት ግድያና ጅምላ ማፈናቀል

185589
Next Story

የግንባር ዜና! በሄሊኮፍተር ሲወርዲ ቀለሟቸው! ደብረ ማርቆስ፣ አዴት!| የአማራ ድምጽ ዜና

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop