በሕዝባችን ላይ የማያባራ ሁኔታ የሚፈፀመውን ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የዘር ማፅዳት የዘር ፍጅት ግድያና ጅምላ ማፈናቀል

August 29, 2023

ለኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስትር

አዲስ አበባ

ጉዳዩ:- የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን ይመለከታል

እኛ ስማችን ከዚህ ማመልከቻ ጋር አባሪ የተደረገው ቁጥራችን 34 የሆንን አማሮች በሕዝባችን ላይ የማያባራ ሁኔታ የሚፈፀመውን ማንነት ተኮር

ጭፍጨፋ የዘር ማፅዳት የዘር ፍጅት ግድያና ጅምላ ማፈናቀል እንዲሁም መንግሥታዊ አቅሞችን በመጠቀም ጭምር የሚፈፀሙ ዘር ተኮር መዋቅራዊና

ሥርአታዊ ሁሉን አቀፍ ጥቃቶችን በመቃወማችን የሕግ የሞራልና የተፈጥሮ ኃላፊነታችንን በመወጣታችንምክንያት ተደራራቢ የሆኑ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች

ጥሰቶች እየተፈፀመብን ይገኛል::

፩: ያለምንም ወንጀል አማራነታችን እንደወንጀል ተቆጥሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሕግን ባልተከተለ መንገድ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ታፍነን በጅምላ ታግተን እንገኛለን::

፪: በፀጥታ ኃይሎች እገታ በተፈፀመብን ወቅት ከፍተኛ ድብደባ አማራነታችን እየተጠቀሰ አዋራጅ ዘለፋ ስድብና ዛቻ ተፈጽሞብናል::

፫: በፌድራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከታገትንበት ጊዜ ጀምሮ ብሔር ተኮር ዘለፋ ማስፈራራት የግድያ ዛቻ እንዲሁም በጨለማ ክፍል ማሰርን ጨምሮ ቤተሰብ ማንገላታትና ዛቻ የዕለት ተዕለት ሰቆቃ ሆነውብናል::

ከዚህ በከፋ መልኩ መሳሪያ የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች በሕይዎት የመኖር መብታችንን ለመንጠቅ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የከፋ ተጋላጭ አድርጎናል::

፬: ፍርድ ቤት የመቅረብ የሕግ ጠበቃ የማማከር የሃይማኖት አባት የማግኘት እንዲሁም በቤተሰብና ጎብኝዎች የመጠየቅ ሰብአዊ መብቶቻችን ሙሉ

በሙሉ ተገድበው ይገኛሉ::

በመሆኑም የፍትህ ሚኒስቴር ከላይ በዝርዝር ያስቀመጥናቸውን እጅግ አስከፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ባስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ አቤቱታ በግልባጭ የተደረገላችሁ ሀገራዊአህጉራዊና አለማቀፋዊተቁአማት የኢትዮጵያ መንግሥት አለማቀፍ የሰብአዊ መብት መርሆችን አክብሮ እንዲንቀሳቀስና በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን ማንነት ተኮር ጥቃት እና ጭፍጨፋ እንዲያቆም ታሪካዊ ኃላፊነታችሁንትወጡ ዘንድ እንጠይቃለን::

ከሠላምታ ጋር

የማይነበብ ፊርማ

ግልባጭ:

ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ለኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

ለኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቁአም

ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን

ለአውሮፓ ህብረት

ለተመድ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት

ለብሪታኒያ መንግሥት

369647808 715460857266245 7244258926934520547 n

369579884 715460900599574 8358943059858009957 n

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

185576
Previous Story

የድል ዜና! ጀነራሉ እና ኮረኔሉ ተማረኩ! ማርቆስ፣ ጂጋ፣ ሆዳንሽ!| የአማራ ድምጽ ዜና

ETHIOPIA SECURITY 1 1
Next Story

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ 183 ሰዎች መሞታቸውን ተመድ አስታወቀ

Go toTop