ከአለም አቀፍ የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ድጋፍ ኮሚቴ የተሰጠ የአቛም መግለጫ

ነሓሴ 21 ቀን 2015 አ/ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር የሆኑት  አብርሐም በላይ (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ የአሸንዳን ባእል ምክኒያት በማድርግ ለትግራይ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገባ ብሄራቸውን ማዕከል ያደረገ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት በአዋረደ መልኩ ያስተላለፉት መልዕክት ከአንድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስተር ነኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ፤ ሃላፊነት የጎደለው፤ የያዙትን ሀላፊነት የማይመጥንና አሳፋሪ መልዕክት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

“የአከባቢው የማንነት እና ወሰን ጥያቄ በተመለከተ ጥያቄ አለኝ የሚል አካል ካለ በህግ እና በህገ መንግስቱ መሠረት እንዲመለስ እየተሰራ ይገኛል” ፤ በማለት የተገለፀዉ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ራያ ህዝብ ከ4 አስርት አመታት በላይ ያካሄደው ትግል የካደ በመሰረቱ ትህነጋዊ የሆነ አስተሳሰብ ነው፡፡

– “የተፈናቀለ ህዝባችን’’ የሚለው አገላለፅ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ማህበረ-ሰብ ያፈናቀለው ህዝብ የለም፡፡ ይልቁንስ የጠለምት ፤ ወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አማራ በመሆኑ ብቻ በትህነጋዊ በጅምላ ሲገደል፣ ሲፈናቀል እና ሲሳደድ በአጭሩ ማንነትን የማፅዳት ዐለምአቀፍ ወንጀል የተካሄደበት፤ በማንነቱ ምክንያት ግፍ እና መከራ ሲቀበል የኖረ ህዝብ ነው፡፡ በቅርቡ በጠለምት፤በማይካድራና በራያ ሕዝብ የተፈፀመው የጦር ወንጀል/war crime and crime against humanity/መጥቀስ ብቻ በቂ  ነው፡፡

– ሪፈረንደምን በተመለከተ በእርሱ አባባል ትግራይ የሚገኘው “የተፈናቀለ ህዝብ”  ወደ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት በመሄድ በህዝበ ውሳኔው ተሳታፊ እንዲሆንና ውሳኔው ወያኔ በሚፈልገው መልክ እንዲጠናቀቅ በማስብ ነው፡፡ የማንነት ጥያቄው የአማራ ህዝብ አካል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ጥያቄ እንጂ ከትግራይ ክልል የምጣ ተፈናቃይ ለምን ሪፈረንደም ይሳተፋል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአርማጭሆ ተኩስ ተከፈተ/የትህነግ በሁሉም ወረራ ዝግጅት /አብይን እንጂ ህዝብን አንዋጋም-ታጣቂዎቹ (አሻራ)

-የጠለምት ህዝብ ከ1983 በትህነግ ከተወረረበት ጊዜ ጀምሮ ለፌደረሺን ምክር ቤትና ለአማራ ክልል መስተዳደር ያለ ማንነታችን እና ያለ ፍላጎታችን በትግራይ ክልል ተካልለናል፤ ማንነታችን አማራ ነው በማለት ህጋዊ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ስለዚህ የማንነት ጥያቄ በሚመለስባቸው አግባብ መሰረት በአስቸኳይ ፌደሬሽን ምክር ቤት ህዝቡን በማነጋገር እና ጥናት በማድረግ ምላሽ መስጠት ይገበዋል፡፡

-ባለጉዳይ እና ባለቤት ነኝ የሚል አካል በማለት የተገለፀው አባባል ሰፊውን የአማራ ህዝብ አይመጥንም፡፡ የአማራ ህዝብ የወሰን እና ማንነት ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ ምላሽ እንዲሰጠው እየጠየቀ  እንዳለ ይታወቃል። ስለሆነም ምንስቴሩ ሁለቱም ክልሎች በእኩልነት እና ፍትኃዊነት መመልከት ሲገባቸዉ፤ ለተመደቡበት ክብር እና ፕሮቶኮል በማይመጥን መልኩ የወሰን እና ማንነት ጥያቄዎች ባለባቸው አካባቢዋች ያሉ የአስተዳደር መዋቅሮች መፍረስ አለበት በማለት የተገለፀዉ፤ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ውድ መስዋዕትነት እና ዋጋ በመክፈል በደሙ ያገኝውን ነዖነት የሚክድ ነው፡፡

በመሆኑም ሚንስቴሩ የተሰጣቸውን ስልጣን እና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለግል ፍላጎታቸው እና ለህውኃት መቆማቸው ያስመሰከሩበት መግለጫ ነው፡፡ ይህንን በመገንዘብ አስቸኳይ የአማራን ህዝብ ታላቅ ይቅርታ እንዲጠይቁና ለንግግራችው እርምት እንዲወስዱ  በአንክሮ እንጠይቃለን፡፡ የጠለምት፤ የወልቃይት ጠገዴና የራያ ሕዝብ የማንነትና የወሰን ጥያቄ በሪፈረንደም ሳይሆን የሚፈታው በፖለቲካና በህጋዊ መንገድ በመሆኑ መንግስት ለተጠየቀው ጥያቄ ፖለቲካዊና ህጋዊ መንገድ ምላሽ እንዲስጥበት በአጵንኦት
እንጠይቃለን።

በመጨረሻም የጠለምት የማንነትና የወሰን ጥያቄ መንግስት እንደሚለው በ ሕዝበ-ውሳኔ መሆን እንዳለበትና ተጠማኝን በድምጽ መስጠት ባለእርስት ለማድረግ  ማንነት በደም፤ በትውልድ፤ የሚወረስ የማይቀየር የማይናወጥ ሆኖ እያለ ሕዝባችንን የሌለ ማንነት በድምጵ ብልጫ/በኮሮጆ በሚሰበሰበው ብጥስጣሽ ወረቀቶች ለማጭበርበርና ሕዝባችንን ለዳግም ባርነትና ስደት፤ እርስታችን ለወራሪና ለመጤ አሳልፈው ለመስጠት ውስጥ ለውስጥ የሚሰሩ አንዳንድ ተቛማትና ሙሁራን ነን ባዮች የጠለ ተወላጆች በጥቅማ ጥቅምና በስልጣን ተደልለው  ሕዝብን እያወናበዱ እንዳሉ በተጨባጭ የደረስንበት በመሆኑ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡና ሳይረፍድ ከሕዝባቸው ጎን እንዲቆሙ ለማስጠንቀቅ እንወዳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የህሊና እስረኛ መሪዎቻችን ላይ በሐሰት መፍረድ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ መፍረድ ነው" - ድምጻችን ይሰማ

አማራ ነን አልን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም።
ህልውናችን በትግላችን
ከአለም አቀፍ የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ድጋፍ ኮሚቴ

 

1 Comment

  1. የጠለምት የወልቃይትና የራያ ጉዳይ የሪፈረንደም ጉዳይ አይደለም። ሪፈረንደም ሲደረግ፤ በግፍ በ “የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር” ነኝ ባይ ቡድን ለተጨፈጨፉት መልሱ ምን ሆነና ነው! እኒህ በአስርት ሺዎች የሚቆጠሩ በጠራራ ፀሐይ የታረዱ አማራዎች ድርሻቸው ምንድን ነው! አማራ ያስከበረውን መኖሪያውን፤ ምንም የአማራ ብልፅግና አሽከር ሆኖ ለአዲሶቹ ገዥዎች ቢያጎበድድም፤ በትግሉ የያዘውን መልሶ አይሠጥም!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share