August 15, 2023
12 mins read

የመከራ መንስዔ (ኢህአዴግ ) ለመፍትሄ አይሆንም ?

መፅሀፍ ቅድዱስ ነገር በሁለት ይፀናል እንዲል ነሀሴ ስምንት ሁለት ተመሳሳይነት እና አንድነት ያላቸዉ መሰረታዊ እና መሪ ንግግሮች በታላቅ መሪዎች ሲነገሩ ሰምተናል ፡፡

መቸም ዕዉነት እንዳለመናገር የሰማንዉን ዕዉነት መካድ አንችልም ፡፡ ባንናገረዉ ዕዉነትነቱን አንቀይረዉማ ፡፡

ይህም ንግግር የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎችን ልዑላዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ታሪካዊ እና አመክኗዊ ንግግሮች በሁለት ኢትዮጵያዉያን በዘመናችን ዕዉነቱን እና የወቅቱን የኢትዮጵያ መዳኛ ታሪካዊ ንግግር ማድረጋቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለዉ አድርባይነት እና ወላዋይነት ባህል እና ልምድ የሚገመት ባይሆንም ከታላቅነት እና ለአዋቂነት ሚዛን ሲቃኝ የሚጠበቅ ነበር  ፡፡

አነዘሂህን ታላቅ ሰዎች እኛ ብንክዳቸዉ እንደ ኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን እና የመከራ ቀንበር ተሸክመዉ ዘመናቸዉን የሚገፉትን ኢትዮጵያን በተለይም ኢትዮጵያዊነት የማርያም ጠላት ተብሎ የዘመናት ፍትህ ፣ዕኩልነት እና ነፃነት በራሱ ለራሱ የነፈገዉን ሠፊዉን የዓማራ ህዝብ የነበረበትን እና ያለበት  ሁኔታ መካድ ነዉ ፡፡

እነኝህ የክ/ዘመኑ ጀግኖች ዕዉነተኛ  ህዝባዊ እና ብሄራዊ የሕዝብ ልጆች ስለመሆናቸዉ በሠዉነታቸዉ ብቻ ለግል ጥቅም እና ክብር ሳይጨነቁ ዕዉነት በመናገር እና በመመስከር ታሪክ በቀለመወርቅ እንዲመዘግባቸዉ እና ትዉልድ ዝንት ዓለም እንዲዘክራቸዉ የሚያስችል  በታሪካዊ ንግግራቸዉ ታሪክ ሠርተዋል ፤ፅፈዋል ፡፡

ከዕነሱም አንደኛዉ  ታላቁ እና ጉምቱ የታሪክ ሊቅ ክቡር አየለ በከሬ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ላይ ዕየሆነ ያለዉ የሶስት አሰርተ ዓመታት በፊት በዓማራ ህዝብ ላይ አስቀድሞ የተጫነበት የጭቆና ቀንበር  ከማላላት  ለማጥበቅ መጣደፍ  ይህ ህዝብ ለማንነቱ እና ለነፃነቱ ጥያቄ ማቅረብ ጥፋተኛ በማለት ለአገረ መንግስት ግንባታ ያደረገዉን ዉለታ እና የከፈለዉን ዋጋ ማሳነስ እና ታሪካዊ ክህደት ነዉ ብለዋል ፡፡ ልባዊ  ክብር ፤ምስጋና እና የተሟላ ዕድሜ ከጤና ጋር ዓምላክ ይስጥልን ከማለት በላይ ምን ይባላል፡፡

ዕዉነት ተናጋሪ  እና የመከራ ወጥመድ አሻጋሪ ባጣች  መካን ኢትዮጵያ በዚህ ጭንቅ ጊዜ ታሪክን በታሪክነቱ በዕዉነት እና ድፍረት መመስከር ከሊቅ በላይ ሊቅ መሆናቸዉ የሊቅነትን መገለጫ ዕዉነትን መስክረዋል  የሚሰማ የሚያሰማ ካለ ፡፡

ዛሬ ለሁላችንም ሆና እንድንኖርባት የተሰጠችን አንዲት አገር ስማቸዉን መጥራት አይደለም መስማት የማንፈልገዉ  ብርቱ እና ልበ ብርኃን አያት ቅድመ አያቶቻችን በደም እና በአጥንት የመሰረቷት እና የገነቧት የጥንታዊት ፣ታሪካዊት እና ታላቋ ኢትዮጵያ አብራክ  ዉጤት የሆነች የዛሬዋ ታናሽ ሆነን በምኞታችን እና በአቅማችን ልክ አሳንሰን የምንኖርባት አገር የታሪክ እና የትዉልድ አሻራ መሆኗን ስንክድ አደራ በል ትዉልድ መሆናችንን ያመሳጥራል ፡፡

ሌላዉ በህዝብ እንደራሲዎች ዉይይት  ክቡር ገዱ አንዳርጋቸዉ በኢትዮጵያ በተለይም የዓማራ ህዝብ ለዘመናት የመከራ እና ጭቆና ቀንበር የተሸከመዉ የ30 ዓመታት ባርነት በቃኝ ማለቱን እና የኃይል ዕመቃ የላቀ ኃይል እንጂ ሌላ አይጠበቅም ብለዋል  ፡፡

የተከበሩ የህዝብ ተወካይ ዛሬ በዓማራ ህዝብ ላይ የምንመኛዉ  የጥፋት ሲቃ መላ ኢትዮጵያን የማዳከም ጉዞ ለአገርም ለእኛም አይበጂም ብለዋል ፡፡

ይህን ሲሉ ለወከሉት ህዝብ ዉለታ ለማስመዝገብ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን እያጥላላን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ወክለን ለክፋት እና ጥፋት ሩጫ መቀልበስ ራሱን ከድክመቱ እና ጥፋቱ መማር የማይቻል መሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል ፡፡ ሰሚ እና አስማሚ ጠፋ እንጂ ዕርሳቸዉስ እንኳን ለተሰጣቸዉ ህዝባዊ እና ብሄራዊ አደራ ቀርቶ እየናደ ለሚክበዉ ኢህአዴግ ባለዉለታነታቸዉን ከታሪክ እና ከርሳቸዉ በላይ የሚናገር ባይኖርም ጥቂት ከምንዳዉ መጥቀስ አለመፈለግ ግን ክፋት ነዉ ፡፡

እርሳቸዉ የነበሩበት የጥንቱ ኢህዴን የዛሬዉ ብአዴን መሰረቱም ጣራዉም የዓማራ ህዝብ ነዉ ፡፡ የዓማራ ህዝብ የነበረዉን የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት (ቅድመ 1983 ዓ.ም) ቅራኔ ከጫካ አስከ የካ ያሽቀነጠረ ህዝብ ስለመሆኑ ከትህነግ እና ከኢሠፓ መጠየቅ ለነፍስም ለስጋም ይሆናል፡፡

ትህነግ ከደደቢት ዋሻ ወጥቶ ፀሃይ እንዲሞቅ በህዝብ እንዲታወቅ ያደረገዉ  አቶ ገዱ የነበሩበት ኃይል ነዉ ፡፡ መቸም በአዴን በህዝብ ዋጋ የራሱን  ጥቅም ከዋጀ  የአገር እና የህዝብ ነገር አይገደዉም ነበር እና በ1982  ዓ.ም ኢህአዴግ እንዲቆቋም ሲደረግ  ብልጧ ትህነግ የበሬን ዉለታ  እንዲሉ መሪነቱን ሁሉን ወስዳ ብአዴንን በርግጫ አለች …..ቀጠለ ፡፡ ከዚያም የክልሉን ዕዉነተኛ የህዝብ ልጂ እና የመጀመሪያዉን ርዕሰ መስተዳደር ሙሉዓለም አበበን …….አስወገደች ፡፡ በቃ የመጀመሪያም የመጨረሻም እኛ የሚለዉ የክፋት እና የዕብሪት ሴራ ከዚያ ጀምሮ በይፋ ሆነ ፡፡

የዚህ የዓመታት በኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት የጫነዉ የጥፋት እና ዕልቂት ደባ ቀጥሎ ህዝባዊ ዕምቢተኝነቱ ገንፍሎ መጋቢት 2010 ዓ.ም እንዲሁ ኢህአዴግ ልብስ ቀይሮ ፣አንደበት እና ስም አሳምሮ የዓማራዉን ህዝብ እና የክቡር አቶ ገዱን የለዉጥ አጋርነት እና ፊዉታራሪነት ወደ ኋላ ብሎ ብአዴን የህዝቡን የዘመናት ትግል እና የተከፈለ ዋጋ በአድርባይነት እና በወላዋይነት አሳልፎ ሰጠ ካደ ፡፡

እናም የተከበሩ እነደራሴ ዛሬም ቢሆን ለኢትዮጵያ ፣ ህዝቧ እና ለተወከሉበት ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለራሱ አገሪቷን ለዕስር እና ህዝቧን ለአሳር እየዳረገ መቀጠል ለሚፈለገዉ ኢህአዴግ የሰጡት መመከርም መማር አለመቻል በራስ ላይ ፋስ መሰንዘር ነዉ ማለታቸዉ ዛሬም ለኢህአዴግ እና ለሚሰማ ዘመን ተሸጋሪ ታላቅ እና ማተዋል ያለበት  ትንቢት ያለበት ምክር ነዉ ፡፡

ዕንደ ሠዉ የሰዉን  ችግር እና ዕረሮ ለመስማት አለመቻል ሠዉነትን መርሳት በሀጢያት እና ጥፋት ጉዞ በጭፍን መራመድ አገር እና ትዉልድ የሚያሽመደምድ ወጥመድ እያዩ እንደ መግባት ነዉ ፡፡

ኢህአዴግ ከዚያ አስከዚህ በዓለም ላይ ያልነበር ችግር እና ስቃይ በአገሪቷ እና በህዝቧ ለመድረሱ መነስዔ እንጂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል መሳያወች ከበቂ በላይ የግማሽ ክ/ዘመን  ብሄራዊ ድቀት እና ዉድቀት ምልክቶችን ለሚይ ማብራሪያም ማመሳከሪያም አያስፈልግም ፡፡

በየትኛዉም ጊዜ እና ቦታ በታሪክ የችግር አካል የችግር መፍቻ ቁልፍ ሊሆን ቸይችልም ፤ሆኖ አይታወቅም ፡፡ ክቡር እና አይተኬዉ የሰዉ ልጂ ህይወት እንደዋዛ ሲቀጠፍ እና ሲገረደፍ ኃላፊነት የማይሰማዉ ስለ ግዑዝ ነገር ማዉራት ከዚህ ዓለም ተጠያቂነት ቢታለፍም በትዉልድ እና በታሪክ ግን ከወቀሳ እና ከሰሳ እንደማያድን ታዉቆ የኢትዮጵያ መዳኛ የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን አዉቆ ዳኝነቱን ለህዝብ መተዉ ከጥፋትም ከሞትም የሚታደግ ነዉ ፡፡

“ክርስቲን ባይኖር ደፍቶ መካርን ሀሰት ባይላቸዉ ፣

ገዱ ደረሰ  የዕዉነትን ኮሶ ጠምቆ ጋታቸዉ  ፡፡”

“ለኢትዮጵያ አንድነት ሆነ ለዜጎች ሉዓላዊነት ኢትዮጵያዊነት እና ዐማራነት ዉጭ ኢትዮጵያ ንብ አልባ ቀፎ ነዉ ፡፡ ”

“ዛሬም እኛ ኢትዮጵያ የምናዝነዉ ዞትር ህዝብን ከፊት ዕያሰለፈ ከኋላ ሆኖ ዕንደምስጥ ህዝብን እና አገርን ለዕሳት ለሚማግዱ ብአዴኖች በድን ሆነዉ ለምንም በጎ ነገር አለመትጋታቸዉ ነዉ ፡፡”

“አንድነት ኃይል ነዉ !”

Allen Z Amber!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop