August 15, 2023
10 mins read

አማራ ከራሱ አልፎ የሌሎችን ኢትዮጵያዊያን ነፃነት ያስከብራል ፣

362279578 877222194248616 8394952406458389026 n 1 1 1

ታሪክ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ሃገራችን በዘመናት መካከል በአራቱም መዕዘናት ግብፆች ፣ ቱርኮች ፣ የሱዳን ድርቡሾች ፣ ጣሊያኖች እንዲሁም የሱማሌ ወራሪ ኃይሎች ሊደፍሯት ቢሞክሩም ነፃነቷን ፣ ድንበሯን እና አድንቷን እስከብራ ትኖር ዘንድ ታላቁን ሚና የተጫወተው ፣ ደሙን ያፈሰሰው እና አጥቱን የከሰከሰው የአማራው ሕዝብ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

ከአፄ ቴዎድሮስ ፣ ከአፄ-ሚኒሊክ እና ከአፄ ኃይለስላሴ የኢትዮጵያ ሰላም ፣ የአንድነት እና የከፍታ ዲፕሎማሲ ቀንዲሎች ስርወ መንግስት  ወዲህ ግን  የአማራው የትግል ፍልሚያ እና የድል ውጤቶች እየተደናቀፉ ፣ እየተጨናገፉ እና ስልጣኑ በማይገባቸው እኩያን እና እቅመ ቢስ በሆኑ ሴረኞች እና ባንዳዎች እጅ እየወደቀ ኢትዮጵያዊያን ሆነ  የአማራው ሕዝብ ብዙ ዋጋ እንዳስከፈላቸው ታሪክ ያሳየናል።

የ1966ቱ የተማሪዎች ፣ የወታደሩ እና የመላ ሕዝቡ የእንቢ አልገዛም ባይነት እንቅስቃሴ ውጫዊው ይዘቱ የመላው ኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበት ቢሆንም የአማራው ወጣት ፣ ገበሬ ፣ ንዑስ ከበርቴው እና መላው የአማራ ሕዝብ የከፈለው መስዋዕትነትም የትየለሌ እንደሆነ ልብ ይሏል ።

የ1966ዓ.ም. የትግል እምርታ በጥቂት  ወታደራዊ ምልምል መኮንኖች ከመጨናገፉ ባሻገር በተለይ አማራው  በሻቢያ ፣ በወያኔ ፣ በሲአየ (CIA) እና በሞሳድ አቀነባባሪነት ኢዲዮ ፣ ኢሕአፖ ፣ ሰደድ ፣ ሚኤሶን ወ.ዘ.ተ. በሚል ፓርቲ እንዲከፋፈል ተደርጎ ኢትዮጵያዊያን እርስ በርሳቸው እንዲጋጩ ፣ ጦር እየተሳበቁ እንዲጨራረሱ በመደረጉ አያሌ ኢትዮጵያዊያን በአመዛኙ የአማራው ሕዝብ እንደ ቅጠል እንዲረግፍ ፣ ለስደት እንዲዳረግ እና በድህነት እንዲማቅቅ ምክንያት ሁኗል። ይህ ኩነት በአማራ ሕዝብ ህይወት እና ኑሮ ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ከማለፉ ባሻገር የትግሉ ግስጋሴ እምርታ እንዳያሳይ እና ፍሬ እንዳያፈራ ፣ ታላቅ ሰንክ እና አሚካላ ተጋርጦበት ለመክረም ምክንያት ሁኗል ።

መሰሬው ህወሃት ኢሕአፖ እና ኢዲዩን በአሻጥር ፣ በደባና በተንኮል ካፈራረሰ በኋላ በጅምሩ  “ኢዲህን” (የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቆ ) ፣ “ብአዲን” (ብሔራዊ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ) የሚባል ተለጣፊ ፖርዎችን አቋቁሞ እንደ ኦዲድ ( ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት) ያሉ ምርኮኛ የኦሮሞ ወታደሮችን አስርጎ በማስገባት እና በማጭበርበር ደርግን ገርስሶ ለስልጣን ቢበቃም የመላ ኢትዮጵያን ፣ የአማራውን ፣  የወልቃይትን ፣ የወሎ እና የራያን ሕዝብ ለውጥ የመሻት እምርታ ድምጥማጡን በማጥፋት ኢትዮጵያዊያንን ለ27 ዓመታት ረግጦ ለመግዛት በቅቷል።

ጠቅለል ብሎ ሲተነተን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን በተለይ አማራው ላለፉት አምሳ አመታት ያከናወነው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ፣ መስዋህትነት እና ፍልሚያ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ በሚቋምጡ ቡድኖች ፣ ሴረኞች ፣ ባንዳዎች ፣  የምዕራባዊያን አጎብዳጆች ፣ እነደ እነ  አብይ ያሉ መሰሪ መሰል አድርባይ እና ጨፍጫፊ መሪዎች የትግሉ ወላፈን ተጨናግፎ በምድሪቱ እልቂት ፣ ፍዳ ፣ አበሳ ከዛም በተለይ በወያኔ እና በብልፅግና የአገዛዝ ዘመናት ኢትዮጵያ እና አማራ ከምድረ ገፅ እዲጠፉ ያልተቆፈረ ጉድጓድ ፣ ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም። ይህ ስንኩል ዓላማ እና አካሄድ ግን በአማራው እንቢ ባይነት እና በተለያየ ስልታዊ የጋራ ትግሎች እየተመከተ አሁን ካልንበት ደረጃ ተደርሷል።

አማራው ለኢትዮጵያ ነፃነት ሲፋለም ፣ ሲዋደቅ እና ደሙን ሲከሰክስ የውጊያ ወል ስሙ “ፋኖ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በዚህ ስያሜው ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያን ፣ የወያኔን እና የደርግ ገዳይ ቡድንን ይህን ስያሜውን አንግቦ ታግሏል ፣ አሁን ደግሞ ወንበዴውን ብልፅግና የፋኖን የትግል ስልት አርማ ይዞ እየተፋለመው ይገኛል።

የአማራው ሕዝብ ይህን ከአምሳ ዓመታት በላይ የሞላውን የትግል ልምድ እና የድል ነጣቂ ሴረኞችን አካሄድ ወደ ኋላ ብሎ በማጤን እና በመገምገም በአዲስ መንፈስ እና እልህ ከዚህ በፊት ያጋጥሙትን መሰናክሎች እና ሰንኮች እንዳይደገሙ በመምከር  “የፋኖን መንፈስ” አንግቦ ተነስቷል ። መላው የአማራ ሕዝብ እንደ ድር እና ማግ ሆኖ በመጣመር ነፃነቱን ለመጎናፀፍ በድል እየገሰገሰ ይገኛል።

ይህ በዚህ እንዳለ ይህን ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ችግሮች መፍትሄ ፈላጊ እና አምራጭ የሆነውን የአማራ እና የፋኖ ትግል በጉልበት ለማንበርከክ መሞከር “ሰማይን በርግጫ ለመምታት እንደማሰብ” ወይም “ውቂያኖስን በጭልፋ ጨልፎ በመቅዳት ለማድረቅ እንደመሞከር እና ማሰብ” ማለት መሆኑን የአማራ ፋኖ ተፃራሬ ኃይሎች ሊገነዘቡ ይገባል እንላለን።

በታሪክ እንዳየነው እና እዳስተማረን አማራ ሆነ ፋኖ ምንም ሆነ ምን “ላይጨርስ አይጀምርምና” ሳንዘናጋ ሙያ ያለው በሙያው ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ እና ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ድጋፉን በመስጠት የድሉ ቀን እንዲፋጠን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ እንዲነሳ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።

በበታችነት ስሜት የተወጠሩት እነ ብልፅግና ድሮን ፣ ጀት እና አሉ የተባሉ መሳሪያዎችን ቢያንጋጉም  “የእጅ አዙር ቀኝ ገዥዎችን ዓላማ እስፈፃሚዎች” ፣ ኢትዮጵያ እና አማራ ጠል የሆኑት በበታችነት የተወጠረው የብልፅግና ቡድን ልበ ሙሉውን እና የጥበብ መዕልቅ የሆነውን ከስልሳ ሚሊዮን (60,000,000) በላይ የሆነውን የአማራ ሕዝብ እና አጋር የሆኑትን ሕዝቦች በ21ኛው ክፍለ ዘመን በኃይል ጨፍልቆ ለመግዛት መሞከር ድንቁርና ፣ ኋላቀርነትና አጉራ ዘለልነት ነው እንላለን።

“ቀስቅስው ቀስቅሰው

ይተኛውን በሬ

አላሳርፍ አሉት

አደረጉት አውሬ”  እንዲሉ ከእንግዲህ አማራን በራሱ በሆነችው ሃገሩ ኢትዮጵያ ስም ማጭበርበር ፣ ማወናበድ እና ማደናገር በቅቷል ። በፋኖ ልጆቹ የአማራን ሕዝብ ነፃነት ፣ ድንበሩን ፣ ግዛቱን እና ዐፅመ እርስቶቹን ወልቃይትን ፣ ጠገዴን ፣ ጠለምትን ራያን ከዛም አልፎ  መተከልን በስሩ በማድረግ መፃሃ ሃገረ ኢትዮጵያን በፀና አለት የተገነባች እንድትሆን ያደርጋታል ፣ ጥርጥር የለውም።

የአለም ታሪክ እንደዘገበው ምንግዜም ቢሆን ፍትህን አንግቦ የተነሳ ኃይል ሆነ ቡድን ኢ-ፍታሃዊ የሆነን ስብስብ ማሸነፉ የማይቀር ነው ።

 

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

 

 

 

 

 

 

 

1 Comment

  1. ወንድሜ ሆይ፣
    በቀድሞ ዘመናት ትግሉ ያተኮረው በባላባታዊ ሥርዓትና በፋሺስት ወታደራዊ አምባገነን ሥርዓት ላይ እንጂ በህዝባችን መካከል ችግር አልነበረም።
    በቅርቡ የታየው እጅግ አሳዛኝ ክስተት ግን የውሸት ትርክት እየፈበረኩ ህዝብን ከህዝብ ማጋጨታቸው ነው። ከፋፍለው ለመግዛት እንዲያ መች መርዛማ ሕገ መንግሥት መዘርጋታቸው ነው። ህዝብን እርስ በርስ ለማጋጨት አገሪቷን ለአስተዳደር ሳይሆን በጎሳ ሰየሙት። በውዲቷ አገራችን ህዝብ ከህዝብ፣ ኃይማኖት ከኃይማኖት ግር ምንም ችግር አልነበራቸውም።
    አንድ በጣም የሚከነክነኝ ጥያቄ ግን የ60ዎቹን ባንድ ላይ መጨፍለቁ ነው። ለምሣሌ ኢሕአፖ መንግሥትም የመንግሥት ካድሬም አልነበረም። ለታሪክ ብዬ ነው።
    አሁን ተባብረን ሰላም እናውርድ፣ በእግዚአብሔር ኃይል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

F3fISstWkAAKDat 2 1
Previous Story

ጭራቅ  አሕመድ  ሲንድሮም እና የዳንኤል ክብረት እየሱስ

F3Ap9heWoAEU9uw 1
Next Story

የመከራ መንስዔ (ኢህአዴግ ) ለመፍትሄ አይሆንም ?

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop