August 11, 2023
7 mins read

ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር የተሰጠ መግለጫ!

366583856 752525980010332 2485368492844070666 n 1 1

ለመላው የአማራ ህዝብ ና ለባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች

366583856 752525980010332 2485368492844070666 n 1 1የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ላለፉት ቀናት በባህር ዳር ከተማና በዙሪያው ባሉት ወረዳዎች ከፋሺስታዊውና ዘረኛው የብልፅግና ጦር ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም ተጋድሎ በክልል መንግስትነት ስም ተቀምጦ የነበረው ፋሺስቱና ዘረኛው የብልፅግና አገዛዝ ከባህር ዳር ሸሽቶ እንዲወጣ ማድረግ ችለናል። ይህንን ተከትሎ ከፍተኛ ሽንፈት የተከናነበው አገዛዝ በህዝብ ማመላለሻ አይሮፕላኖች ጭምር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነፍሰገዳይና ከባድ መሳሪያዎች በግፍ በማስገባት የባህር ዳር ከተማን በከባድ መሳሪያዎች ደብድቧል። በመሆኑም ፋሺስታዊው አገዛዝ በበቀል ስሜት ከተማዋን ለማውደም መነሳቱን በመገንዘብ በሰላማዊ ህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በሚል የትግል ስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ ከባህር ዳር ከተማ የመውጣት ውሳኔ አሳልፈናል።

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ላለፉት 50 አመታት በሀሰተኛ ትርክት በጠላትነት ተፈርጆ በገዛ ሀገሩ ተሳዳጅና ባይተዋር ሁኗል። ባለፉት 5 የብልጽግና የአገዛዝ ዘመናት ደግሞ በአማራ ላይ የሚደርሰው ግፍ ተባብሶ በጅምላ እየተገደለ እየተፈናቀለ እና እየተሳደደ ይገኛል። ይህ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለ ሰቆቃና በደል እንዲቆም በሰላማዊ መንገድ ትግል ቢደረግም አገዛዙ በሰላማዊ ህዝባችን ላይ የሀይል እርምጃ መውሰዱን አላቋረጠም። የግፍ ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱና ህዝባችን ከዚህ በላይ ይህንን አገዛዝ ተሸክሞ መቀጠል ባለመቻሉ በተለያዩ ከተማዎች ህዝባዊ እምቢተኝነት ውስጥ ገብቷል። ህዝባዊ አመፁን ተከትሎ አገዛዙ በንፁሃን አማራዎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ መግደልና መጨፍጨፍ ሲጀምር ህዝባችንን ከአገዛዙ ጥቃት ለመከላከል ነፍጥ አንስተን በመታገል ላይ እንገኛለን።

በዚህም ተጋድሎ የብልፅግና የሞግዚት አገዛዝ ከባህር ዳር ሸሽቶ ወደ ጌቶቹ እንዲሄድ ማድረግ ችለናል። በጢስ አባይ ከተማ የብልፅግና መዋቅርን አፍርሰን የህዝብ አስተዳደር መስርተናል። በጢስ አባይ የሀይል ማመንጫ ጣቢያ ከነበሩ የብልፅግና ወታደሮች መካከል ከ50 የሚበልጡትን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከናቸዋል።

በገንጅ ሰባትአሚት በተደረገ ተጋድሎ በአገዛዙ በግፍ ታስረው የነበሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞችን ማስለቀቅ ችለናል። በባህር ዳር ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ውስጥ የነበሩ ፖሊስ ጣቢያዎችን በመቆጣጠር አገዛዙ ህዝብን ለመግደል ይጠቀምባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን ማርከናል።

የባህር ዳር ከተማና የዙሪያ ወረዳው ህዝብ ከጫፍ ጫፍ በመንቀሳቀስ በህዝባዊ አመፅ ስርአቱን በመቃወም ለአማራ ፋኖ ያለውን ድጋፍ አሳይቷል።

በመሆኑም:-

1.በፋሽስቱ አገዛዝ በአረመኒያዊ መንገድ ሂወታችሁ ለተቀጠፈ የከተማችን ነዋሪዎችና ቤተሰቦች የተሰማንን ሀዝን እንገልፃለን።

  1. የምንታገልለትን ህዝብ ነፃ እስክናወጣ ድረስ ይህንን ስርዓት ለማስወገድ ምንም አይነት ሃይል ሊያስቆመን አይችልምና ሁሉም የአማራ ህዝብ በቻለዉ መንገድ ትግላችንን ይደግፍ።
  2. ለመላዉ የአማራ ወጣትና ለባህርዳር ህዝብ ትግላችንን እድትቀላቀሉ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን።
  3. ህዝቡን ለገዳዩ አገዛዝ ጨፍጭፉልን ብለዉ የወጡ ከክልል ጀምሮ እስከ ከተማችን ድረስ ያሉ አመራሮች ያስጨፈጨፉትን ህዝብ ዳግም እናስተዳደራለን ብለዉ ወደ ክልሉና ከተማችን ለመመለስ እንደማያስቡ በሙሉ እምነት እያመንን የከተማችን ነዋሪዎች ከወዲሁ አስተዳደራችሁን እንድትመርጡ ስንል እናሳዉቃለን።
  4. ከዚህ በሁዋላ ህዝባችንን ለጨፈጨፈው ስርዓት አገልጋይ የሚሆን ማንኛውም ሰው የህዝባችን ደም በእጁ ላይ እንዳለ አውቆ ለሚወሰድበት እርምጃ ራሱ ሀላፊነት ይወስዳል ።
  5. ለትግሉ አስፈላጊ ሁኖ ከተገኘ በማንኛውም ግዜና ሰአት ወደ ባህር ዳር ከተማ ተመልሰን መግባት እንችላለን።

በስተመጨረሻ:- በዚህ ተጋድሎ የተመዘገቡ ድሎች እንደተጠበቁ ሁነው አገዛዙ በንፁሃን የከተማችን ህዝብ ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅሟል። ይህ ፋሺስታዊ ቡድን ምንም አይነት የመንግስትነት ባህሪ እንደሌለው ዋና ማሳያው በድባንቄ የሚገኘውን የውሃ ማከፋፈያ በመቆጣጠር ለከተማችን ህዝብ የሚሰራጨውን ውሃ በማቋረጥ ህዝባችንን በውሃ ጥም በማሰቃየት ላይ መሆኑ ነው። ከዚህ የምንረዳው ይህ አረመኔያዊ ቡድን ሙሉ በሙሉ እስካልተወገደ ድረስ ህዝባችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እረፍት አግኝቶ በሰላም ሊኖር እንደማይችል ነው። በመሆኑም ከከተማ የመውጣት ውሳኔ ብናሳልፍም ትግላችን በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላል ።

የአማራ ፋኖ በባህርዳር

ነሐሴ 5/2015ዓ.ም

ባህርዳር

https://youtu.be/bilzA-JcIKw

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

184947
Previous Story

የአንድ ሳምንት የጦር ድል|ዶ/ር ይልቃል ትኬት ቆረጠ | ደመቀ አማላጅ ሆነ | ፋኖ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

Mamo Mihretu 1 2 1
Next Story

የማሞ ምህረቱ የማስመሰል ጩሀት (እውነቱ ቢሆን)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop