የዘር ፍጅትን የማስቆም አስቸኳይ ጥሪ! በአዲስ አበባ የታፈኑ የአማራ ተወላጆችን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ !

Lisane Gufuan 1 1

የብልፅግና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጦርነትና የጅምላ ጭፍጨፋ ተከትሎ በአዲስ አበባና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ እስርና እንግልት እየተካሄደ እንደሆነ ይታወቃል።

ይህ ህገ-ወጥና ኢሰብዓዊ የሆነ የጅምላ እስርና ማሰቃየት በግንባር ቀደምትነት እየተመራ የሚገኘው 1ኛ. በኦሮሞ ብልፅግና ከፍተኛ የደህንነትና ወታደራዊ ባለስልጣናትና

2ኛ. በቅርቡ ወደ ቀደመ እኩይ ምግባራቸው በተመለሱ የትህነግ/ወያኔ የደህንነትና ወታደራዊ ሃላፊዎች ጥምር ቡድን መሆኑን አረጋግጠናል።

ቀደም ሲል የተጀመረውና የአማራ ተወላጆች ብቻ ለይቶ ሲፈፀም የቆየው ግፍና ሰቆቃ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ማግስት በትህነግ/ወያኔና በብልፅግና መንግስት መካከል ከሰፈነው ህገ-ወጥና መርህ-አልባ ግንኙነት ጋር ተያይዞ በእጅጉ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑ ይታወቃል። በተለይም በቅርቡ የጠ/ሚ አብይ ካቢኔ ባወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅና ከዚህም ጋር ተያይዞ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በኩል በአዲስ አበባ ብቻ ከ4000 በላይ ሰላማዊ ዜጎች ለእስር እንደተዳረጉና የሚገኙበትም ሁኔታ በግልፅ እንደማይታወቅ ለማወቅ ችለናል።

ይህ የጅምላ እስርና ማሰቃየት በዋናነት ያተኮረው በአማራ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የማኀበረሰብ አንቂዎች፣ ባለሃብቶችና ፖለቲከኞች ላይ ሲሆን ጥቃቱ በተለየ ሁኔታ በአማራ ወጣቶች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ይታወቃል።

 

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ከታማኝ ምንጮቹ በደረሰው መረጃ መሰረት እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ታፍነው ከተወሰዱ ከ4 ሺ በላይ ሰላማዊና ንፁሃን የአማራ ተወላጆች መካከል ከ 300 በላይ በጭካኔ ተረሽነዋል። እንዲሁም ከ 55 በላይ የሚሆኑት ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የደረሰን ምስጢራዊ መረጃ ያመለክታል። የጅምላ ፍጅቱ ያተኮረው በታዋቂ ሰዎች ላይ ሳይሆን በሚዲያም ሆነ በተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች አዘውትረን በማናያቸው ወጣትና ንቁ የአማራ ተወላጆ ች ላይ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

ከዚህም በመነሳት በአዲስ አበባና በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በጥብቅ ምስጢር እየተፈፀመ የሚገኝ የዘር ፍጅት /Genocide/ እየተካሄደ መሆኑ ድርጅታችንን ያሳስበዋል። ስለሆነም አሁን በአፈና ላይ ያሉትና በመታሰር ላይ የሚገኙትን የአማራ ተወላጆች አሁን በመካሄድ ላይ ያለው አማራን በጅምላ የመፍጅት ጥቃት ሰላባ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።

 

ስለሆነም፦

1ኛ. መላው የአዲስ አበባ ህዝብ ልጆቹ ከቤቱና ከስራ ገበታቸው በብልፅግና አፋኝ ቡድን ታፍነው መወሰዳቸውን እያወቅ እጁን አጣጥፎ ሊቀመጥ አይገባም ብለን እናምናለን። ስለሆነም ህዝባችን ልጆቹ የት እንደ ደረሱና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅና ማረጋገጥ ይኖርበታል። በዚህም ትግል ውስጥ ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ከህዝባችን ጎን በመሰለፍ የመሪነት ግዴታውንና ሃላፊነቱን እንደሚወጣ እናረጋግጣለን።

2ኛ. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባና በዙሪያው በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ የሚገኘውን የጅምላ እስርና እንግልት፣ ታሳሪዎቹ የሚገኙበትን ቦታና ሁኔታ፣ እንዲሁም እየተካሄደ የሚገኘውን የዘር ፍጅት እንዲመረምርና ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በፍጥነት በግልፅ እንዲያሳውቅ እንጠይቃልን!

3ኛ. ከብልፅግና መንግስት ጋር በመሆን የአማራ ክልልን በኮማንድ ፖስት እዝ ስር እንዲወድቅ የወሰኑና ያቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ለሚገኘውና ዘርን መሰረት ያደረገ የጀምላ እስርና ግድያ፣ እንዲሁም በመካሄድ ላይ ለሚገኘው ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ናቸው። በዚህም አጋጣሚ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ በጥብቅ እናሳስባለን!

4ኛ. አዲስ አበባን መቀመጫቸው ያደረጉ የውጭ ሀገር አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ የሚገኘውን እስር፣ ስቃይና፣ ግድያ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ጥሪ እናቀርባለን!

5ኛ. ሀገር በቀልና ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የብልፅግና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና የጅምላ እስርና ማሰቃየት ለዓለም ህብረተሰብ በማጋላጥ ወገኖቻችንን ከፈፅሞ መጥፋት እንዲታደጉ እንጠይቃለን!

6ኛ. በአማራ ህዝብ ላይ በድሮን፣ በታንክ፣ እንዲሁም በመድፍ የታገዘ ጭፍጨፋ እያካሄደ የሚገኘው የብልፅግና መንግስት በህዝባችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን አረመኔያዊ ድርጊትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ ማቆም ይኖረበታል። በአዲስ አበባና አካባቢው በጀምላ ያሰራቸውና መዳረሻቸው የማይታወቁ የአማራ ተወላጆች የሚገኙበትን ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለኢትዮጵያ ህዝብና፣ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በግልፅ እንዲያሳውቅ በአንክሮ እንጠይቃለን!

7ኛ. በመጨረሻም የብልፅግና መንግስት በአዲስ አበባና አካባቢው በአማራ ተወላጆች ላይ እያዳረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ የጅምላ እንግልት፣ እስርና፣ ግድያ በአስቸኳይ ካላቆመ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ለመጠቀም እንገደዳለን!

 

ድል ለአማራ ህዝብ!

 

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

ነሐሴ 4/2015 ዓ.ም

 

ግልባጭ

  1. ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
  2. ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህብረት አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
  3. ለአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ/ኢትዮጵ
  4. ለአውሮፓ ህብረት አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
  5. ለዓለም አቀፍ ኢምባሲዎች አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
  6. በተበባሩት የዓለም መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ጀኔቭ/ ሲዊዘርላንድ
  7. ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በያሉበት
  8. ለአማራ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት በያሉበት

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

184939
Previous Story

በአማራ ክልል የሽግግር መንግስት??? ውጊያው ቀጥሏል፥ ባህርዳር በማን እጅ ናት? የአዲስ አበባ አፈሳ፥ አርባምንጭና ዱራሜ

184947
Next Story

የአንድ ሳምንት የጦር ድል|ዶ/ር ይልቃል ትኬት ቆረጠ | ደመቀ አማላጅ ሆነ | ፋኖ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

Go toTop