ታምረኛዋ ፎቅ! ጎንደር ላይ የተፈጠረች ክስተት!!!

August 10, 2023

363951442 834002631845113 2827185688034266638 nይች ፎቅ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 1 ብልኮ አካባቢ ወደ ጎሃ ሆቴል መሄጃ መንገድ ዳር ያለች ፎቅ ናት።ጎሃ ሆቴል ላይ ደግሞ የፋሽስቱ አብይ አህመድ አንድ ሻለቃ ኮማንዶ በእነ ብርጋዴር ጀኔራል ዋኜው አለሜና ኮሚሽነር ዋኜው አዘዘው እየተመራ አጉሊ መነፀር እየተጠቀመ የጎንደርን ከተማ እየቃኘ በዲሽቃ ንፁሃንን ይጨፈጭፍ ነበር።

ይህ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ከዚች ፎቅ ስር ከፎቁ ዳርና ዳር ካሉት ቱቦዎች ስር ደግሞ እስናይፐርና ብሬን የታጠቁት በአርበኛ መሳፍንት ተስፉ ልጆች የሚመራው የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት ፋኖ ከመሬቱ ጋር ተመሳስሎ ጠላቱን ይጠባበቃል።

አገር ሰላም ነው ብሎ ደርቱን የነፋና ጡንቻውን ያሳበጠ ኮማንዶ ከጎሃ ሆቴል ወደ ታች 10 ሆኖ ሲመጣ አርብኞቹ በእስናይፐር 10ሩንም ያነጥፉታል። ከዚያም ግራ የገባው ጀኔራል ዋኘው ከየት ሆነው ነው ልጆችን የመቷቸው ይልና ተጨማሪ 8 ኮማንዶ ይልካል። አሁንም 8ቱንም በእስናይፐር ያረግፉታል። ከዚያ በኋላ ይህ ነገር ከዚህ ፎቆ አናት ያሉ አልሞ ተኳሾች ናቸው ብለው ፎቁን በእሩምታ ተኩስ ቢያርከፈክፉ ምንም ጠብ የሚል ነገር የለም።

ከዚያ በኋላ ብረት ለበስ እንላክ ብለው ብረት ለበስ ሲልኩ ፋኖዎቹ በረት ለበሱን የሚመቱበት ላውንቸር ስለሌላቸው አውቀው ዝም ብለው ተኝተው ያሳልፉታል።ከዚያ በኋላ አገር ሰላም ብሎ ብረት ለበሱ ከሄደ በሗላ ተጨማሪ ከ15 በላይ ኮማንዶ ቀስ እያለ ይጠጋል። ይህንንም ቡከን ድባቅ መተውት ከቱቦው ስር ወጥተው እራሳቸውን እየተከላከሉ ወደ ታች ተዳፋቱን ይዘው በመሽሺ አርበኞቹ ከ30 በላይ ደረቱን የነፋ ጎመን ጭቃ አድርገውታል።

ተኩሱ ካበቃ በኋላ ከ100 በላይ ኮማንዶ ዞ ሆቴሉን ወሮ ሲፈትሽ የተገኘው አንሶላና ብርድ ልብስ ብቻ ነበር።

Veronica Melaku

Leave a Reply

Your email address will not be published.

184916
Previous Story

በዋሽንግተን ዲሲ የፋኖ እና የአማራ ህዝብን ለመደገፍ የተደረገ የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሰልፍ

the voice of amhara daily new
Next Story

የአማራ ድምጽ ዜና | The Voice of Amhara Daily News

Go toTop