ከዓለም አቀፍ የጠለምት ዓማራ ማንነት ድጋፍ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ግንቦት 11 2015

ህልውናችን በትግላችን

እንደሚታወቀው የጠለምት፣ ወልቃይት ጠገዴና የራያ ሕዝብ ላለፉት ሠላሳ ሁለት ዓመታት በትህነግ አገዛዝ ከፍተኛ በደል የደረሰበትና ታሪካዊ እርስቶቹን ተነጥቆ የዘር ማፅዳት(Genocide) ይርትርፈፀመበት ሕዝብ ነው። ይሁን እንጂ የዓማራ ሕዝብ ባደረገው ከፍተኛ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና መስዋእትነት ትህነግን ታግሎ የጣለ ቢሆንም የትህነግ የጡት ልጆች የሆኑተን የዖሮሙማ ተረኞች የዓማራን ሕዝብ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በጎንደር፣ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ፣ ማጀቴና አጠቃላይ በኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ መንግሥታዊ ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት ይገኛል። አገርን ከወራሪና ከጠላት መታደግ ትችሏል። በዚህ ጦርነት ወቅትም የአማራ ሕዝብ ከፍተኛ ስቃይና ለከፋ ጉስቁልና ተዳርጓል። በርካቶች በማንነታቸው ተለይተው ተጨፍጭፈዋል፣ እናቶች ተደፍረዋል፣ ሃብት ንብረታቸው ወድሟል፣ ለስደት ተዳርገዋል። ክጭፍጨፋው የተረፉትም ቢሆን በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ያለ በቂ ምግብና መጠጥ፣ አልባሳትና ህክምና በየመጠለያ ካምፖች ታጉረው ፍዳቸውን እያዩ ገኛሉ።

 

ይህ ሁሉ በደልና ግፍ በአማራው ላይ እየተፈፅፀመ ለአገር አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ለሕዝብ የጋራ እድገት በሚል በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና መከራ በመቻል አገርን እንደ አገር ለማስቀጠል ሲባል አሁን ካለው የኦሮሙማ መንግሥት ጋር በመሆን ወረራ የፈፅፀመዉን የትህነግ አረመኔ ቡድንን የአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖና ሚሊሺያ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን አገርን ከወራሪና ከጠላት መታደግ ትችሏል። በዚህ ጦርነት ወቅትም የአማራ ሕዝብ ከፍተኛ ስቃይና ለከፋ ጉስቁልና ተዳርጓል። በርካቶች በማንነታቸው ተለይተው ተጨፍጭፈዋል፣ እናቶች ተደፍረዋል፣ ሃብት ንብረታቸው ወድሟል፣ ለስደት ተዳርገዋል። ክጭፍጨፋው የተረፉትም ቢሆን በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ያለ በቂ ምግብና መጠጥ፣ አልባሳትና ህክምና በየመጠለያ ካምፖች ታጉረው ፍዳቸውን እያዩ ይገኛሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያውያን እናቶች እና ሴቶች የዕርቀ-ሰላም ጥሪ!!

 

ይህ ችግር ስደትና መፈናቀል ሳይሸርና መፍትሄ ሳይገኝለት የትግራይ ወራሪ/ተስፋፊ ሃይል ጠለምትን፣ ወልቃይት ጠገዴንና ራያን በአጠቃላይ የአማራዉን ሕዝብ ዛሬም ለአራተኛ ጊዜ ለመውረር እየተዘጋጀበት ባለበት ሁኔታ ትናንት የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትን ከመዋረድና ከመበተን ያዳነዉን ጀግናው የአማራን ሕዝብ በኦሮሙማ መራሹ መንግስት ከመቸዉም ጊዜ በበለጠና በተቀናጀ መልኩ ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል ሰበብ በመላው የአማራ ክልሎች ላይ ጦርነት ከፍቷል።

 

ላለፉት ሦስት አሰርት ዓመታት በተደጋጋሚ ወገናቸዉንና አገራቸዉን ከድተው በአደርባይነት የሚያገለግሉት የኦሮሞ ብልፅግና ተላላኪዎችና ምስለኔ በአዴኖች እየገደለ የአብይ መንግሥት እንደገና መፈንቅለ መንግስት ተካሄደብኝ በማለት የአማራዉን ሃይል ለማዳከም ለብዙ ጊዜ ያዘጋጀዉን ኦነጋዊ እቅዱን ማስፈፅሚያ ብልሃት አድርጎ የያዘዉን የአብይ አህመድ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ተዋጊና በከባድ መሳሪያ የተደራጀ የጦር ሃይል በአማራ ክልል አሰማርቶ የክልሉን ልዩ ሃይል ትጥቅ እያስፈታ ሲያስጨፈጭፈው ፋኖን ሲያሳድድ ስንብቶ የጠቅላላ ፍጅቱን እቅድ ለመፈፅም መግቢያ መውጫዉን ዘግቶ በሚቆጣጠረው አከባቢ ያስገደለው ባለመዋሉን ግርማ የሺጥላን የሸዋ ፋኖ ገደለው የሚል ወሬ በተከፋይ ሎሌዎች በኩል በማህበራዊ መገናኛ አሰራጭቷል።

 

የአማራ ክልልን መከላከያ አቅም አሳጥቶ መቆጣጣር አማራን ለአገር አልባነትና ለዘላለማዊ ባርነት ለመዳረግ ወሳኝ እርምጃ ያደረገው አብይ አህመድ በአዴን የሚያዘዉን ልዩ ሃይል በፋኖ ላይ አዘምቶ የአማራዉን ወጣት እርስ በእርስ ለማፋጀት ያወጣዉን እቅድ በህዝባዊ እምቢተኝነትና በልዩ ሃይል አባላት ተቃዉሞ አለመሳካቱን ሲረዱ በአገር መከላከያ ሰራዊት ስም ባዘመተው ጦር በቅድሚያ ልዪ ሃይልን ትጥቅ ለማስፈታት በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ፋኖ፣ ልዩ ሃይልና ህዝባዊ ሚሊሺያው በኦሮሙማው ምንግሥት የተከፈተበትን የዘር ማጥፋት ጦርነት ለመቀልበስ፣ ህልዉናዉንና ማንነቱን ለማስከበር እየተፋለመ ይገኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አስቸኳይ ሕዝባዊ ጥሪ ወልቃይትን እና ራያን ለህዝበ-ውሳኔ (ሬፈራንደም) ማቅረብ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የታቀደ አደገኛ ሴራ ነው!

 

በመላው ዓለም የምንገኝ አማራዎችም “ህልውናችን በትግላችን” በሚል መርህ መሰረት መስውአት እየከፈለ ላለው ወገናችን አጋርነታችንን ማሳየት ይጠበቅብናል። መላው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የአማራው ሕዝባዊ ትግል የፍትህ፣የማንነትና የአገር አድን መሆኑን በመገንዘብ ማን ነው ባለሳምንት እያለ በየቤቱ በአማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና ሰቆቋ በራሱ ላይ እስኪደርስበት ከመጠበቅና በተናጥል ከመመታት ሁሉም ዜጋ በመተባበር ይህን አስከፊና ዘረኛ መንግሥት እስከነ ግንሳንግሱ በማስወገድ ዜጎች በእኩልነት፣ ተከባብረው፣ ተዋደው፣ አንድነቷ፣ ዳር ድምበሯ ተከብራና ታፍራ የምትኖር ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለአንዳች ማመንታት ቆራጥ ትግል ሊያክሂድ ግድ ነው።

 

በመጨረሻም ዓለም አቀፍ የጠለምት አማራ ማንነት ድጋፍ ኮሚቴ አለም አቀፍ የአማራ ማሕበርና ፋኖ ያወጣቸውን ወቅቱን የጠበቁ ባለ ስምንት ነጥብ አቋም ሙሉ በሙሉ የምንደግፍ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

 

ህልውናችን በትግላችን!

የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ይኑር!!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share