ብረትን እንደ ጋለ፤ ነገርን እንደተጀመረ! – ከጎንደር ሕብረት የተሰጠ መግለጫ

www.gonderhibret.org
4126 Deerwood Trail, Eagan MN 55122 Tel 651 808 3300

ከጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ

የብልፅግና ፓርቲ የክልል ልዩ ኃይሎች በአስቸኳይ ትጥቅ መፍታት እንዳለባቸው በመወሰን፤ አተገባበሩንም ለአገር መከላከያ አመራሮች መሰጠቱንና ይህ ውሳኔ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ከክልል አመአራሮች እስከ ታችኛው የሥልጣን እርከን ድረስ በመመሪያ እየትላለፈ መሆንኑን አረጋግጠናል።

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት በመርህ ደረጃ በአንድ አገር ሊኖር የሚገባው አንድ ጠንካራ አገራዊ መከላከያ ሰራዊት ብቻ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል።

ሆኖም ግን አሁን የአማራ ሕዝብ እየደረሰበት ካለው የማሳደድ፤ የማፈናቀል፤ የመታገት እና የመገደል በአጠቃላይ ጭራሽ ህልውናው አደጋ ውስጥ በወደቀበት ሁኔታ በብልፅግና መራሹ መንግሥት የተወሰነው ከአብራኩ የወጡ አለኝታ ልጆቹን ትጥቅ የማስፍታት ውሳኔ፤ ወቅቱን ያልጠበቀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ውሳኔ ጀርባ አደገኛ ደም አፋሳሽ፤ ብሎም የኢትዮጵያን አገራዊ አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል የፖለቲካ ሴራ መኖሩን በተጨባጭ አገራችን ካለችበት የፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ አኳያ ለመረዳት ነብይ መሆንን የማይሻ እጅግ አስጊ ሁኔታ ላይ መሆናችንን እኛም ሆነ መላው ሕዝባችን እናምናለን።

ስለዚህ የጎንደር ሕብረት (ጎሕ)፦

1.በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሕወሓት ትጥቅ መፍታት ቀርቶ በአማራ ክልል ላይ ሌላ አራተኛ ወረራ ለመፈጸም በገፍ ወጣቱን በመመልመል ወደ ማሰልጠኛ እያጎረፈ ባለበት ሁኔታ፤

2.ለረዥም አመታት ብዙ የህይወት መስዋዕትነት የተከፈለባቸው የወልቃይት እና የጠገዴ፤ የጠለምት እና የራያ የማንነት ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ሳያገኙ፤

3.ከክልላቸው ውጭ ሐብትና ንብረት አፍርተው፤ ወልደውና ከብደው በኖሩ የአማራ ተወላጆች በዘራቸው ምክንያት ብቻ እንደ አውሬ እየታደኑ በሚጨፈጨፉበትና በሚሳደዱበት፤ መንግሥትም ህጋዊ ከለላ መሥጠት በተሳነው ወቅት፤ አለኝ የሚለውን የመከላከያ ተስፋውን ለማፍረስ መሞከር መንግሥትን ሊወጣ ከማይችለው፤ አገርም ልትሸከመው ከማትችለው ቀውስ ውስጥ የሚጨምር እሳት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቅዱስ ፓትርያርኩ የወለጋና ጋምቤላውን ጭፍጨፋ አወገዙ

4.መንግሥት በማንኛውም መዋቅሮቹ ህግና ሥርዓትን ተከትሎ መሥራትና የዜጎችን ህልውና ማስጠበቅ ባልቻለበት፤ የአገር አደጋ በተጋረጠበት ሰዓት ለችግሮቹ ምክንያት ያልሆነውን፤ ከመክላከያ ጎን ተሰልፎ ደሙን አፍሥሶ አገርን ከህልውና አደጋ የታደገን ልዩ ኃይል ተሯሩጦ ትጥቅ ይፍታ ማለት፤ በተለይም የአማራን ልዩ ኃይል ቀድሞ ትጥቅ እንዲፈታ መወሰን፤ ባማራው ህልውና ላይ የታወጀ ልዩ ጦርነት ነው ብለን እናምለንለን። በመሆኑም የአማራ ሕዝብ ሆይ!

“ለኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት” በሚል ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበውን መግለጫ በማር የተለወሰ መርዘኛ ሴራ መሆኑን ተረድተህ፤ በባህልህና በታሪክህ ለውንድ ልጅ መሳሪያውን ከትክሻው፤ ሚስቱን ከጎኑ የሚነጥቅን ጠላት ሲመጣ ቄጤማ ጎዝጉዘህ እጅህን ዘርግተህ እንደማትቀበል ሁሉ፤ እንደ ማንኛውም የአገራችን ክልሎች ማንነትህን ሊያስከብር በመንግሥት ይሁንታ የተመሰረተው ልዩ ኃይልህን፤ እየደረሰብህ ባለው አድሎአዊ የግፍ ሥርዓ ብሶት ምክንያት ከአብራክህ ወጥቶ የተደራጀውን የፋኖ ጀግኖችህን ጭምር ትጥቅ አስፈትተው የቤትህ ጓዳ ድረስ ዘልቀው ዘልቀው በመግባት ሊያርዱህ እየተዘጋጁ ነው።

ይህ ሴራ ደግሞ፤ በደምህና በአጥንትህ የአገርህን አንድነት በማስጠበቅህ ምክንያት ለረዥም ጊዜ ጥርሳቸው በነከሱ የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችህ ጭምር ተጎንጉኖ “መንጋው እንዲበተን፤ እረኛውን ምታው” እንዲሉ ኢትዮጵያ አገርህን ለማፍረስ ሥጋት ነው

ብለው ስላመኑብህ፤ ቀድመው ሊያጠፉህ ተልኮ በተሰጣቸው አገር እየመራን ነው በሚሉ የወያኔ ጉድፈቻ ልጆች ከግራ ከቀኝ፤ ከሰሜንና ከማህል አገር ተጠራርተው የጥፋት ጥሩምባቸውን እየነፉ ተነስተውብኃል።

በመሆኑም፤ መጭው ጊዜ ከአሁን በፊት ከነበሩብን የህልውና ፈተናዎች እጅግ የከፋ አደጋ ከፊታችን እየመጣ እንደሆነ ይታየናል። ህልውና ደግሞ ታሪክም አገርም ተደምረው ነውና ትርጉም የሚሰጡት፤ የምትመካበትና ከብዙ የጥፋት አደጋ የታደገህን ልዩ ኃይልና ፋኖን አይንህ እያየ ቆመህ ትጥቅ እንዲፈታ በቸልተኝነት መመልከትም መፍቀድም እንደማይኖርብህናይህን ደባ ለማክሸፍ በተገኘው መንገድ ሁሉ ተቃውሞህን እንድታሳይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የከሸፈውን የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስረታ ህዝብ እንዲቃወም የቀረበ ጥሪ

በእኛ እምነት፤ ይህ በአሁኑ ሰዓት የተወሰነው የልዩ ኃይልህን ትጥቅ የማስፈታት ውሳኔ፤ በወልቃይት፤ በጠለምትና በራያ ላይ ያሳየነው የተለሳለሰ ትግል በመሆኑ፤ “የነብርን ጅራት አይዙም፤ ከያዙም አይለቁም” ነውና፤ ትጥቅን ላለመፍታት ብቻ ሳይሆን፤ ብረትን እንደጋለ፤ ነገርን እንደተጀመረ ነውና፤ ለአመታት በግፈኛው በወያኔ ኢሕአዴግ ዘመን ጀምሮ፤ በቀጣይ የጉድፈቻ ወራሽ ልጆቹ ጭምር እንደሎሚ እየታሽ የቆየው ጥያቂያችን ምላሽ አግኝቶ ህልውናችን እንዲረጋገጥ አምርረን እስከ ወዲያኛው እንድንታገል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

መፍትሄም የሚሆነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ በዘር እንድትሸነሸን፤ ሰው ከተወለደበት ቀየው ውጭ እንዳያስብ ኋላ ቀር በሆነ አስተሳሰብ የትውልዱን ጭንቅላት ያሸወረረውን አገር አጥፊ የጎሳ ህገ መንግሥት አፍርሶ ጠንካራ አገራዊ አንድነትን ባማከለ፤ ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበትን፤ በህግ ፊት ቀርቦ ሰው በመሆኑና በሰራው ወንጀል ብቻ ፍርድ ፍትህ የሚያገኝበትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በጠንካራ አለት ላይ የሚገነባ ህገ መንግሥትን በመቅረጽ የዜግነት ዋስትናን በማረጋገጥ ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚቻል መሆኑን የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት በጽኑ ያምናል።

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

04/07/2023

1 Comment

  1. ፉከራሽን ጀመርሽ እዉነት መስሎሽ? ሌላዉ ይዋጋል አንቺ ግን ትፎክርያለሽ። ወያኔ በወልቃይት በኩል ስታስገባልሽ በደምብ ይበርድልሻልና ጠብቂ በሳምንታት ዉስጥ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share