March 31, 2023
5 mins read

የኢትዮጵያዊነታዊ  ድርጅቶች  የጋራ  መድረክ መግለጫ 

The Forum of Ethiopians Civic Organizations in the Diaspora
የኢትዮጵያዊነታዊ ድርጅቶች የጋራ መድረክ

በማርች 29፣ 2023 በሰሜን አሜሪካን የሚገኙ ስማቸዉ ከዚህ በታች የተመለከተዉ የሲቪክ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያዋን ተቆርቋሪ ስብስቦች በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው አካል በጋራ በመመስረት አገሪቱ ለገባችበት አደገኛ የስርዓት ቀውስ እና የህልውና አደጋ ተጠያቂ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ እና የሚያራምደው እኩይ የሆነ የአገዛዝ ስርዓትን በሰላማዊ ትግል  ለመታገልና ስርአታዊ ለዉጥን ግብ አድርጎ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሚሰራ የጋራ መድረክ መስርተዋል።

  1. እምቢልታ/አገር አድን ኅብረት
  2. ግሎባል አሊያንስ(GLOBAL ALLIANC FOR THE RIGHTS OF ETHIOPIAN
  3. የኢትዮጵያ የውይይት እና የመፍትሄ መድረክ(EDF)
  4. ቪዥን ኢትዮጵያ(VISION ETHIOPIA)
  5. የዲሲ ግብረ ሃይል
  6. የኢትዮጵያ ሴቶችመብት ማእከል(CREW)
  7. አለምአቀፍ የኢትዮጵያዉያን የሲቪክ ድርጅቶች ኔትዉርክ (WE CAN)
  8.     ልዩልዩ የኢትዮጵያዋን ተቆርቋሪ ስብስቦች (concerned Ethiopians)

ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ እየተከሰተ ያለውን የአገሪቱ ህልውናን አደጋ ላይ የጣለ ሁኔታን በመገምገም የኢትዮጵያ ህዝብ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ መብቶቹ እንዲከበሩለት ለመታገል በአራት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የጋራ ራዕይ በመንደፍ በሚከተሉት መሰረታዊ ችግሮች ላይ አብረው ለመስራት ስምምነታቸውን አስፍረዋል።

  1. 1. ኢትዮጵያ ብዙ ባህል ያለባት የአንድ ህዝብ አገር ስትሆን ለረጅም ዓመታት አገረ መንግስት የመስረተች ታሪካዊት እና ታላቅ የማትከፋፈል አገር ናት። ይህ አንድነታችን የማንደራደርበት ኣቋማችን ነው።
  2. የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ልኡላዊነት የማይደፈር መሆን አለበት።
  3. ሁሉም ኢትዮጵያውያን ነጻ ዜጎች ሆነው በአገሪቱ በማንኛውም ስፍራ በእኩልነት የመኖር መብት ሊኖራቸው ይገባል።
  4. 4.ኢትዮጵያ በታላቅ የህልውና ጥያቄ ላይ ገብታለች። አገረ መንግስቱ ለሰላሳ ዓመታት በጸረ ኢትዮጵያ ጠባብ ቡድኖች አመራር በመውደቁ የተነሳ በሙስና፣ በአድልዎ እና በፍትህ አልባ አሰራር በመበከሉ ታይቶ የማይታወቅ ኢሰብአዊ ግፍ በህዝቧ ላይ እየተፈጸመ ነው። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሰፍኖ ያለውየጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ መንግስትእና  ስርዓት አገሪቱን ወደ ሰላም ዲሞክራሲ እና ብልጽግና ሊወስዳት የማይችል በመሆኑ በምንም አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም። ለእነዚህ እኩይ አሰራሮች በዋናነት ተጠያቂ ስለሆነ ይህንን  የጥቂት  አምባገነኖች  መንግስት  የሚያራምደው ስርዓት  መእንዲያከትም ትኩረት በመስጠት የዲሞክራሲያዊ የስርዓት ሽግግር ላይ በጋራ በአቋቋሙት መድረክ አማካይነት ለመታገል ተስማምተዋል።

በማከልም  በእነዚህ አራት ነጥቦች ላይ የሚስማሙ የሲቪክ ድርጅቶች ሁሉ ይህንን ኅብረትና የጋራ መድረክ አባል እንዲሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።

The Forum of Ethiopianist Civic Organizations in the Diaspora

የኢትዮጵያዊነታዊ ድርጅቶች የጋራ መድረክ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop