#image_title

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን) #March8 በሙያቸው የመጀመሪያ በመሆን በግንባር ቀደምትነት የተመዘገቡ ሴት ኢትጵያውያን

#image_title
1. ልዕልት ፀሀይ ኃይለስላሴ — የመጀመሪያው የነርሲንግ ሞያ ያጠናችና ለመጀመሪያ ጊዜ በሬድዮ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ
2. ዶ/ር ወዳድ ኪ/ማርያም — የመጀመሪያው ሴት ሀኪም
3. አውሮኘላን አብራሪ ወ/ሮ ሙሉ እመቤት እምሩ ሲሆኑ ለብቻቸው አውሮፕላን ያበረሩት ደግሞ ወ/ሮ አሰገደች አሰፋ ናቸው።
4. ወ/ሮ ብርነሽ አስፋው — የመጀመሪያዋ ሴት መሃዲስ
5. ወ/ሮ ሮማንወርቅ ካሳሁን — የመጀመሪያዋ ሴት የሬድዮ ጋዜጠኛ የሴቶች ፕሮግራም አዘጋጅ
6. እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ –የፒያኖ ለስላሳ ሙዚቃ በሸክላ ያስቀረፁ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ
7. ወ/ሮ አፀደወይን ተክሌ — የመጀመሪያዋ ሴት ዳኛ
8. ዶ/ር አዳነች ኪ/ማርያም እና ወ/ሮ መንበረ አለማየሁ – የመጀመሪያዎች ሴት ሚኒስትሮች
9. ዩዲት እምሩ — የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር
10. ሠላማዊት ገ/ስላሴ — የመጀመሪያዋ ሴት ተዋናይ
11. ስንዱ ገብሩ — የመጀመሪያዋ ሴት ፓርላማ አባል
12. ወ/ሮ ፀሀይ መላኩ — የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት የረጅም ልብወለድ ደራሲ (ቋሳ)
13. ወ/ሮ የዝና ወርቁ– የመጀመሪያዋ ሴት አጭር ልብወለድ ደራሲ (የተሸጠው ሰይጣን)
14. ፋንታዬ ተሰማ የመጀመሪያዋ ሴት ማሲንቆ ተጨዋች
15. ሜሪ አርምዴ የመጀመሪያዋ የውጪ ፀጉር አስተካካይ (ፍሪዘር)ተመራቂ
16. እቴጌ ጣይቱ ብጡል የመጀመሪያዋ ሴት ብስክሌት የነዱ
17. አልማዝ እሸቴ የመጀመሪያዋ ሴት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር
18. አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ ሴት የኦሎምፒክ ባለወርቅ ተሸላሚ
19. ሞዴል የሀረርወርቅ ጋሻው በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት (International Black Actress)
20. ወ/ሮ ባዩሽ ታደሰና ወ/ሮ ብርቱኳን በቀለ የመጀመሪያዎቹ ሴት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች
21.እማማ ፂዮን ሚካኤል የመጀመሪያዋ ሴት የልብስ ዲዚያነር
#ታሪክን_ወደኋላ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከታሪክ ማህደር: ሦስተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ - አቡነ ተክለሃይማኖት

9 Comments

 1. በሴቶች ትግል ምንም እንኳ በጎሳ ፖለቲከኞች ወደጠማም መንገድ ቢገባም የዚያ ትውልድ ድንቅ የሴት ታጋዮችን መዘከር ተገቢ ነው:: ማርታ መብራቱ አባቷ ጄንራል መብራቱ ከማረፋቸው በፊት ልጄ ማርታ ለሴቶች መብት ባለመቆሜ የነቀፈችኝ ልክ ነበር ያሉላት ሌላዋ ከማጀት እስከአደባብይ ትንታግ ጋዜጠኛ ገነት በርሄ የጎህ ድንቅ የትግል ብእረኛ መዘገብ ነሽ አባያን መርሳት አይቻልም::

  • ደጎኔ እንዴት ነው ጉዳይህ እየመረጥክ የምታጀግናቸው ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎችን ነው በጤና ነው? ወይስ የprosperity ክንፍ ነህ? ካልሆንክ ይቅርታ አገሩን የተነጠቀ ዜጋ ይህን ቢል አይፈረድበትም።

   • ያንዱ ወዳጅ የሌላው ጠላት ነው:: ከሰው በታች የሚቆጠሩ ህዝቦችና ሴቶችን ነጻ ለማውጣት ክቡር ህይወታቸውን የሰጡ ጀግና ሰማእታት ለገባ ህዝቦችና ለተገፉ ሴቶች ድንቅ ሰማእታት ሲሆኑ ለበዝባዥ ልጆች የአጼው ናፋቂዎች ጠላት ናቸው:: ይህን ሃቅ መቀየር አይቻልም:: ማርትዬና መሰሎችዋ ዘላለም እንደኮከብ በኢትዮፒያ ሴቶች ታሪክ ደምቀው ይዘከራሉ:: ሃቀኛ ምስክር ዲጎኔ ሞረቴው ከግፈኛው ፊታውራሪ ሞገሴ መቃብር ማዶ ከህያውን የገባሮቹ ልጆች

    https://www.eurasiareview.com/01122011-the-martha-manifesto-an-ethiopian-womans-dream-oped/

 2. የመጀመሪያዋ ሴት ንግሥት፦ ከንግሥተ ሳባ (ማከዳ፣ አዜብ) ቢጀምር መልካም ነው።
  ታሪክ ነውና የመጀመሪያዋ አውሮፕላን ጠላፊ ሴት ማርታ መብራቱ ብትካተት መልካም ነው።
  እኔ የታየኝን ብያለሁ ሌሎች ደግሞ የተረሱ ካሉ ቢጠቁሟቸውና ቢዳብር በጣም ጥሩ ሠነድ ይወጣዋል።
  ለማንኛውም ለአቀረቡት ወገኖች ምስጋናዬ የላቀ ነው።

 3. ይህን ሠነድ ላጋራችሁን ምስጋና እያቀረብኩ

  ንግሥተ ስባ (ማክዳ፣ አዜብ)፦ የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ንግሥት
  ማርታ መብራቱ፦ የመጀመሪያዋ ሴት አይሮፕላን ጠላፊ (ታሪክ ነውና)
  ፎቶአቸው ያልተሟላውን ያላቸው ቢልኩ
  ሌሎች ያልተካተቱ ካሉ የሚያውቁ ቢያሟሉት
  በቁጥሩ አኳያ ፎታቸውም ላይ ስማቸው ቢኖር
  የተሟላ መረጃ ያደርገዋል።

  • ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው
   ወይ ታምራት ላይኔ ወይም ቄስ ግርማ ሊሆን ይችላል ሳያስበው የተሰራበት ነገር ፈንቅሎ ይወጣና ወደ ተራማጅ ተራጋጭ ትንታኔ ውስጥ ይገባል ፡፡ጭቆና ተጨቋኝ አድሃሪ ተስፈንጣሪ እያለ ዘመን በሻረው መዝገበ ቃላት ትውልዱን ያሳክራል፡፡ ወዳጄ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተመችቶት የኖረ ባንተ ዘመን ማለት ነው አንድም የለም፡፡ ባለመሬቱ ከሃብታም ገበሬ ይበደር ነበር ከዶ/ር ምናሴ ሃይሌ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ፈልገህ አንብበው አለበለዚያ ዘመን ተሻግሮ ያልበረደው ተራማጅነትህ በንክኪ ባይሆንም በሳይበሩ አለም ብዙ ጥፋት ሊያመጣ ይችላል፡፡ አሁን አሁን ከሩሲያ ሚሳየል ያንተው የሳይበር ሚሳየል እያሰጋ መጥቷል፡፡ ባንድ ወቅት ከፍቾ ነኝ ስትል ነበር ፈልገህ ከፍቾ ላልሆንክበት ምን አስጨነቀህ ?ከከፍቾ ስንት ድንቅ ኢትዮጵያውያን ተፈጥረዋል አንተም ባህር ማዶ ሳትማር እንዴት መጣህ የትህነግን ዘመን ያየ ሌላውን ማማት አያምርበትም፡፡ አባጅፋር ከፍቾዎችን ሲሸጣቸው እኝህ መከረኛ ምንሊክ ናቸው ተው ትጣላኛለህ አትሽጣቸው እንደእኔ እና እንዳንተ በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠሩ ናቸው ብለው ያስቆሙት ዛሬ ላይ አንተ እንዳትሸጥ ያደረገህን ንጉስ በጠላትነት ፈርጀሃል፡፡ ጽሁፍህ ጥሩ ነው አስተማሪም ነው ብቻ ይሄ ኢሃፓ አጠገብ አትድረሱ የምትለው ነገር እያስፈራን መጥቷል ማርታ የምትባለውን ሴትዮ በፍቅር ነው የምታስባት፡፡ ይሄ ነገር አይሆንም ወዳጄ ከሃገር አሳቢዎችም ጋር አንዳንዴ ስትላተም አያለሁ ነገር ማብረድና የሰው ምክር መስማትም ጥሩ ነው፡፡ባለፈው እዚህ አንድ ጎረቤቴ የነበረ ትግሬ በጠና ታምሞ አምቡላንስ ሊወስደው ቢል ሙቼ እገኛለሁ አለ ጉዳዩን የጠረጠረ ፖሊስ ቤቱን ሲፈትሽ የተገኘው ነገር ሲታይ ኢትዮጵያ ምኗ ተርፏል ብሎ ጭንቅላት አስይዞ ያስጮሃል 3 ኬሻ ዶላር ስርቶ ከማያውቅ ትግሬ ቤት ሲወጣ ምን ይባላል? ጉዳዩ ሲጣራ ስብሃት ነጋ በወር አንዴ ይጎበኘው ነበር ተባለ በሌብነት የተገኘ ሃብት በረከት የለውም ዲሲ ፖሊስ ለመንግስት ገቢ አደረገው፡፡ ገንዘቡን ጠብቅልኝ ቢለኝ ለትግሬ የጦር ቁስለኞች አርቲፊሻል እግር መስሪያ አዉለው ነበር

  • ያ የጥፋት ትውልድ ማርታ መብርሃቱ የመጀመሪያዋ የኤርትራ አውሮፕላን ጠላፊ እንጅ የኢትዮጵያ አውሮፕላን ጠላፊ ልትሆን አትችልም እንዲሃ አይነቱ ስራ ታሪክ ውስጥ ካካተተ አዜብ መስፍንን የኢሳይያስ አፈወርቅን ሚስትን የሃይለማርያም ደሳለኝ ሚስተን የስብሃት ነጋን ሚስት እና የቀሩ አጋንንት ሴቶችን ጨምሪበት፡፡ እንደው እፍረት ቀረ ማለት ነው በኢትዮጵያ ምድር?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እንኳን ደስ ያለሽ! (ለጋዜጠኛ መዐዛ መሐመድ)

Next Story

በአሁናዊ ተራማጅ አስተሳሰቦች እየተመሩ ፍትሃዊ ለውጦችን  በማስመዝገብ እንጅ ታሪክ ላይ የቸንክሮ  በመቆዘምና በመኮፈስ ኢትዮጵያን ማበልፀግ ቀርቶ ማስቀጠል አይቻልም!!!

Latest from ከታሪክ ማህደር

ስለ ዐድዋው ጦርነት እና ድል በኢትዮጵያ ቤ/ክ አባቶች/ሊቃውንቶች አስቀድሞ ትንቢት መነገሩን እናውቅ ይሆን?! የዐድዋ ድልን፤ ያለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ማስብ ፈጽሞ የማይቻል ነው!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) በኢ.ኦ.ተ. ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ማኅበረ ቅዱሳን የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኛ የሆነችው፤ እኅታችን መስከረም

Share