January 19, 2023
23 mins read

ፍትህ ለክቡር ታዲዮስ ታንቱ፡፡ እውቀት ይስፋ ድንቁርና ይጥፋ ይህን ይላል የኢትዮጵያ ተስፋ (ቀ ሃ ስ)

br 556ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የዛሬው ባለጉዳያችን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከላይ በፎቶው እንደምትመለከቱት በመለስ ዜናዊ የጽልመት ዘመን  ከስርአቱ ጋር ተጣብቆ ሲኖር ትንሽ ቀረብኩ ብሎ ሲዳፈር ደግሞ እስር ቤት ተልኮ በምህረት ወደ ባህር ማዶ ያቀና ሰው ነው፡፡ በእስር ቆይታውም ብዙም እንዳይከፋው ላፕቶፕ፤የሙዚቃ መሳሪያዎችና ፤ስፖንጅ ፍራሽ  ገብቶለት እስርን ወደ መዝናኛነት የቀየረ በኢትዮጵያ የእስር ታሪክ የመጀመሪያው ታሳሪ ነበር፡፡  ከዚሁ ተንደላቆ ከተቀመጠበት እስር ቤትም  መጽሃፍ ጻፈ ተብሎ ረቂቁ ወደ ባህር ማዶ  ተልኮ ተሰራጭቶም  ነበር ይላሉ ደጋፊዎቹ፡፡ የዚህ መጽሃፍ ደራሲም አንዳርጋቸው ይሁን ወይም ብርሃኑ ጊዜ የሚፈታው ቢሆንም መጽሃፉን በተመለከተ ግን የፕሮፌሰር መስፍን አስተያየት በበቂ ሁኔታ ገልጾታል፡፡

ብርሃኑ ነጋ  በአብይ አህመድ ዘመንም ሰልፋን አስተካክሎ እንደ ዘመናውያን ቋንቋ ተከርብቶ ኦሮሙማ አሻጋሪያችን ነው በማለት የኢዜማ መስራቾቹን በተለመደው ጥልፍልፍ ስራው ገለባብጦ አድር ባይ አባሎቹን በመያዝ ለብልጽግና አድሮ ሚኒስቴር ሁኖ ተሹሟል፡፡  በተካነበት ጥልፍልፍ ስራውም አንዱ አለም አራጌን አስወግዶ የኢዜማ መሪም ሁኗል፡፡  አንዱ አለም አራጌ ምንም እንኳን በሳል የፖለቲካ ሰውና ለኢትዮጵያ ብዙ ዋጋ የከፈለ ታላቅ ፖለቲከኛ ቢሆንም የነ ብርሃኑን ሴራ  ጠንቅቆ ባለመረዳቱ ኢሳት በጠራው ቃለ መጠይቅ ከብርሃኑ ጋር አብሮ ባለመቅረቡ  የዋህ ሰው መሆኑን በግልጽ አሳይቶ ቁማሩንም በግልጽ ተበልቷል፡፡ በመሰረቱ ለአንድ የመሪነት ቦታ የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች በተመሳሳይ  ቦታ በተመሳሳይ ጥያቄ ወገናዊነት በሌለው ጋዜጠኛ ሊጠየቁ ሲገባ  አንዱ አለም አራጌ ግን በየዋህነትና ባለመጠርጠር ከምርጫው በፊት በብርሃኑ ጋዜጠኛ ብቻውን  በመጠይቁ ሰተት ብሎ ብርሃኑ ወጥመድ ውስጥ ወቋል፡፡ ይህ አድር ባይ የብርሃኑ ጋዜጠኛ አንዷለምን ካዋረደ በኋላ ምርጫው ሲያልቅ ሚዛን ለማስጠበቅ በሚመስል መልኩ ብርሃኑን በግልጽ የሚወደውን ጥያቄ ጠይቆታል፡፡

 

ብርሃኑ ነጋ ለእንዲህ አይነት ሴራ አዲስ አይደለም፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከማንም በላይ መስዋእትነት የከፈለውን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩን /ር ታየ ወ/ሰማእት ግምቦት 7 በተባለው የብርሃኑ/አንዳርጋቸው ካምፓኒና ኢሳት በሚባለው ጸረ ኢትዮጵያ ሚዲያው ከጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር  በእሩምታ ተኩስ ከጣሉት በኋላ ብዙ ሊያበረክት የሚችለው ወንድማችንን ከወገኖቹ ተገልሎ ጥጉን ይዞ ሲቀመጥ  ብርሃኑና መሰሎቹ የፖለቲካ ሜዳውን ለጥቂት ጊዜ ተቆጣጥረውት ነበር፡፡ በዚህ ሳያበቃ የዲሲ ግብረ ሃይል የተባለው የብርሃኑ የሽብር ቡድን (አሁን እንኳን ተጸጽተው አንዳንድ ሚዲያ ላይ መሳሳታቸውን ቢገልጹም) ከብርሃኑ ፖለቲካ ጋር አይጣጣምም ያሉትን ሁሉ በማዋረድ መሪያቸው ብርሃኑን ለዛሬው ስልጣን እንዲደርስ በእጅጉ ረድተዋል፡፡

 

እንደ አንዱ አለም አራጌ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሲል እንደ ጥጃ ሲታሰርና ሲፈታ የኖረው ቤተሰቡን በትኖ ለሃገሩ ሲዋደቅ የነበረውን እስክንድር  ነጋን  ብርሃኑ ለብልጽግና ታማኝነቱን  ለማሳየት በየጊዜው ምን ያህል ያንጓጥጠው ይተቸው እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው እንደ ዶር ታየ ወ/ሰማአት ሁሉ እስክንድርም ይድላህ ብሎ ሜዳውን ጥሎለ ተሰውሯል፡፡

abir and shimeles

ዶር አብይ በመጻፉ እንደገለጸው ደካማና መርህ የሌላቸውን  ግለሰቦች የሚፈልጉትን ሰጥተህ ጋልባቸው  የሚል የፖለቲካ ፍልስፍና ቢኖረውም አንዴ ከሾማቸው በኋላ  ለርሱ እስካደሩ ድረስ ስራቸውን ተከታትሎና ገምግሞ በጊዜ ስራውን ብቃት ላለው ዜጋ የመስጠት ፍላጎት አይታይበትም፡፡ እንዲህ ያለውን ድክመት በወቅቱ ተከታትሎ  እርምት ባለመውሰዱ የመንግስቱን ስልጣን  የያዙት ተሿሚዎች ብቃት የሌላቸው በመሆኑ ስራውን ብልሽትሽት አድርገውት ዛሬ መላቅጡ ጠፍቶት የሚያደርገውን አጥቶ መለኮታዊ መፍትሄን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ 130 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት አገር እውነተኛ ምሁር ባልጠፋበት ልምድ ያላቸው ዜጎች በተትረፉበት አገር ሰው በ ሌንጮ ለታ/ባቲ፤ሺመልስ አብዲሳ፤አዳነች አቤቤ፤ታከለ ኡማ፤ዳግማዊት ሞገስ፤አረጋዊ በርሄ፤አባዱላ ገመዳ፤አብረሃም በላይ፤አርከበ እቁባይ፤አባዱላ ገመዳ፤ዲማ ነገዎ፤ብርሃኑ ነጋ፤አገኘሁ  ተሻገርን በመሳሰሉ ሰዎች ተከቦ ይቀመጣል? እንደ አንድ ጤናማ መሪ ሹመኞችን በዘር መስፈርት ሳይሆን በችሎታቸው ቢሾማቸው እሱም ዛሬ የገባበት ማጥ ውስጥ ባልተዘፈቀ ነበር፡፡

አምባሳደር ተብለው የሚሾሙት ብቃት የሌላቸው በመሆናቸው የህወአት አክቲቪስቶች በነጻው የዲፕሎማቲክ ሜዳ በከባዱ ስለዘረሩዋቸው በፕሪቶሪያውና በናይሮቢ ስምምነት ትግሬዎች የአብይን መንግስትና ተደራዳሪውን ሬዱዋን ሁሲንን  አፍንጫ ይዘው ወደ መንግስቱ በአሸናፊነት ተመልሰዋል ፤የጠየቁትም በሙሉ ይፈጸምላቸዋል፤ በሰሩት ወንጀልም  አይጠየቁም፡፡  ለኦሮሙማው የአብይ መንግስት ወንጀለኞች ተራ ጋዜጠኞች ሃሳባቸውን በነጻ የሚገልጹ ዜጎች፤ሃገር በተወረረችበት ጊዜ ቤተ ሰብ በትነው ህይወታቸውን   ለሃገራቸው የሰጡ ፋኖዎችና  እንደ መሳፍንት ጥጋቡ እንደ ክቡር ታዲዮስ ታንቱ  ያሉ ምስኪን ዜጎች ናቸው፡፡ እነ ጁዋርንማ ማን ቀና ብሎ ሊያይ? እንዲህ ያለ ተዋራጅ መንግስት  በታሪካችን ገጥሞን አያዉቅም ህግን ለማስከበርም የሞራል ብቃትና ቁርጠኝነትም አልታየበትም የህግ ስርአቱ ሲበለሻሽ ሞዴል መአዛ አሸናፊ አንድም መግለጫ ሳይሰጡ ወንጀልን ደግፈው በሚያስብል ሁኔታ ሲበቃቸው የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተገልጿል ፡፡ የዶር አብይ መንግስት መከላከያውን ያረዱትን የህወአት ጄነራሎች ዳግም ወደ መከላከያው እንዲደባለቁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል፡፡ እዚህ ላይ ዲፕሎማቶችን ካነሳን ዘንዳ አምባሳደር ታየ አስቀ ስላሴ፤አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ አምባሳደር ይልቃል አእምሮ፤አምባሳደር ሄኖክ ሻውልን ሳናመስግን አናልፍም አገራችዉ በውርደት ላይ በነበረችበት ጊዜ ያቅማችውን ሞክረዋልና፡፡ የአክሊሉ ሃብተወልድ፤የከተማ ይፍሩ፤የጎሹ ወልዴ ሃገር… እንዲህ በዲፕሎማሲ ድርቅ ስትመታ ማየት ልብ ያደማል፡፡

 

ዳግም ወደ ዶር ብርሃኑ ስንመለስ ለሚኒስቴርነት ሹመት ሲቀርብ በፓርላማ ውስጥ የነበረውን ውዝግብ አንባቢ መለስ ብሎ ቢመለከተው መልካም ይሆናል፡  አንዳንድ ወጣት ፓርላሜንቴሪያን ይህ ሰው ለቦታው ብቃት የለውም፤ስራም ያበላሻል፤  ሃገር ላይ መቀለድም ይሆናል፤ ኪሳራም ያመጣል ብለው ቢቃወሙም ዶር አብይ ግን አገልግሎኛል የት ልጣለው በሚል እሳቤ እውቀት፤ልምድ፤ሃላፊነት፤ ሃገር ወዳድነትን በሚጠይቀው ታላቅ ተቋም ላይ ዶር ብርሃኑ ልምድ እንዲያካብት  ሚኒስቴር አድርጎታል፡፡ እግዚሃር ያሳያችሁ ኮለኔል ጎሹ የያዘውን ተቋም መሆኑ ነው ይህ ሰው የተቀመጠበት፡፡

እስቲ ዶክተሩ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ያደረሰውን ጥፋት በመጠኑ እንመልከት

13000 የአማራ ወጣቶችን የወደፊት ህይወት ማጨለም ቅድሚያ የሰጠው ስራው ነው፡፡ የአማራ ክልል ወጣቶች ፈተና ተስርቋል ብለው ጥርጣሪያቸውን በመግለጽ ላለመፈተን ስላንገራገሩ ብቻ የብርሃኑ ፍላጻ ያለ ርህራሄ አርፎባቸዋል፡፡ ይህ ክስተት በባለጊዜዎቹ ኦሮምያ ክልል ቢሆን ብርሃኑ አይሞክረውም ነበር፡፡ ብርሃኑ በትምህርት ቤት በነበረበት ዘመን ድንጋይ ሲወረውር ትምህርት ሲሰለቸው ሲያድምና ሲያሳድም የአጼ ሃይለ ስላሴ መንግስት መብቱ ነው ብሎ ከመመልከት ባሻገር በቤተ ዘመድና በሽማግሌዎች አስለምኖ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመልሳል እንጅ የ13000 ወጣቶች ህይወትን የሚያበላሽ ስራ ሲሰራ በታሪክ ተመዝግቦ አላየንም፡፡  እነዚህ 13000 ወጣቶች የብርሃኑ ተጠቂዎች በትምህርት ጎልብተው አገራቸውን ካላገለገሉ የወደፊት እድላቸው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ እነዚህ የብርሃኑ የጥቃት ሰለባዎች ወደፊት  ለብርሃኑ የፖለቲካ ጉዞ ጋሬጣ እንደሚሆኑ ብርሃኑ አሻግሮ መመልከት አልቻለም፡፡ የብርሃኑ ኢዜማም ደፍሮ ካሁን በኋላ ወደነዚህ ወጣቶች ክልል እግሩን እንደማያነሳ አስረግጦ መናገር ይቻላል፡፡ እንግዲህ ብርሃኑ የትኛውን ኮንስቲትዎሲ ይዞ  የሚያልመውን የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነትን ቦታ እንደሚይዝ ጊዜው ሲደርስ የምናየው ይሆናል፡፡ ግለሰቡ የሞራል ችግር ስለሌለበት ኢዜማን አፍርሼ ብልጽግና ሁኛለሁ ቢለን ሊገርመን አይገባም ምክንያቱም ግማሽ ጉራጌ ግማሽ ኦሮሞ ነኝ ማለት ከጀመረም ቆይቷልና፡፡

በቅርቡ አዳነች አቤቤ፤ሽመልስ አብዲሳ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ታከለ ኡማ….. ተማሪዎች በኦሮምኛ መማር አለባቸው ብለው አገር ምድሩን ሲያምሱት እንደ መሪው ሁሉ ብርሃኑም አንገቱን አሸዋ ውስጥ ቀብሮ ድምጹን አጥፍቶ አላየሁም አልሰማሁም ብሏል ፡፡ ብርሃኑ ከጊዜው የዘር ሹማምንት ጋር የሚያላትመውን አጥብቆ ይጠላል ወደ ፊት ነገር ሲበላሽ ግን ቀድሞ ተቃዋሚ ይሆናል በዚህ ተክኖበታል፡፡ በቅንጅት 97 ዘመን ብርሃኑ በጠራው ሰልፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአጋዚው በትግሬ ፋሽስቶች ሲታጨዱ ብርሃኑ ነጋ ሌሊቱን ገስግሶ እንድብር መመሸጉን በወቅቱ ወዳጁ የነበረው በረከት ስሞን በመጽሃፉ ገልጾታል፡፡

ብርሃኑ  በተከፋዮቹ አብዘቶ ከተጮኸለት ስራው ፈተና መሰረቁን ማስቆሙ ነበር፡፡ጎበዝ ፈተና ሲጀመር መሰረቅ ነበረበት ወይ? በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ፈተና መሰረቅ የተጀመረው ጁዋር መሃመድ አሰርቆ ለኦሮምያ ተማሪዎች ሲያስተላልፍ ነው፡፡  ሲጀመር ፈተና መሰረቅ የለበትም ይህንን ማስቆም የሚኒስተሩ ሳይሆን የአንድ ንኡስ ባለስልጣን ትንሽ የስራ ድርሻ መሆን በተገባ ነበር ብርሃኑ ግን በትምህርት ላይ ጠቃሚ የሆነ አስተዋጾ ማበርከት ባለመቻሉ ይህ ሊሆን የማይገባውን ስርቆት ማስቀረቱን ትልቅ የስራው ስኬት አድርጎ ይቆጥረዋል፡፡ ይገርማል፡፡

ብርሃኑ ነጋ በዚህ ሳያበቃ በሚያገኙት ገቢ መኖር ያቃታቸውን የዩኒቨርስቲ መምህራንን ማስፈራራቱን ተያይዞታል እናባርራለን የሚል ዛቻም እየሰነዘረ ነው፡፡አንባቢ ወደ ኋላ መለስ ብሎ የዚህን ሰው ታሪክ ቢመረምር በመለስ ዜናዊ ዘመንም ለስርአቱ አይመቹም ተብለው የተባረሩትን ምርጥ መምህራን ተክቶ በመስራቱ ዛሬም ለምሁራኑ ክብር የማይሰጥ ሚኒስቴር መሆኑን በድጋሚ አሳይቷል፡፡  የምሁር ፍራቻ (phobia) ሳይኖርበትም አይቀርም ይባላል  ብርሃኑ ነጋ አሉ ከሚባሉ ከበርቴዎች አንዱ በመሆኑ  የመምህራኑን   ችግር መገንዘብ አይችልም፡፡ መምህራኑም ከተራው ዜጋ በተሻለ የማገናዝብ ደረጃ ላይ በመሆናቸው ይህንን ሹመት አጥብቀው መቃወም በተገባቸው ነበር፡፡

ዶር ብርሃኑ አብዝቶ የሚኮፈሰበትና ጋሻ ጃግሬዎቹ ከባጥ በላይ የሚያስጮሁለት ፕሮፌሰርነቱንና ኢኮኖሚስት መሆኑን ነው፡፡ ዶር ብርሃኑ የኢኮኖሚክስ ትምህርት መማሩ ይወራል የትኛውን ኢኮኖሚክስ ዘርፍ እንደሆነ ግልጽ መረጃ አልተገኘም፡፡ ይህንና በኢኮኖሚክስ ስልጠናው ያበረከተውን ለማጣራት ብንጎግልም ግልጽ ያለ የተሟላ መረጃ አላገኘንም በኢኮኖሚክስ መስክም ያሳተመው ጥናትም ሆነ  ወረቀትም አልተገኘም፡፡ አስተማርኩት ባለው ትምህርት ቤትም የቆየው ለሶስት አመት ብቻ ነው፡

እንደሚታወቀው  የሶሻል ሳይንስ ትምህርት በየጊዜው ካልተካበ ዋጋው በእጅጉ እየቀነስ የሚሄድ የትምህርት ዘርፍ በመሆኑ ባሉበት ማእረግ ለመቆየት ተያያዥ ስራዎችን መስራት ስለ ሙያው የሚወጡትን ጽሁፎች መከታተልና የራስን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቃል( እንደ ኤርምያስ አመልጋ ማለት ነው) ያ ካልሆነ ግን እድሜ ልኩን እንደ ቀኛዝማች ግራዝማች ፊልድ ማርሻል ተብሎ ሲጠራበት ሊኖር አይችልም፡፡ እስቲ ስም ማጥፋት እንዳይሆንብን አዲስ ዲያሎግ ከሚል ድህረ ገጽ የተገኘውን የፕሮፌሰሩን ቃለ መጠይቅ እንመለከት፡፡ በብዙ ቃለ መጠይቅ እንደሚያደርገው የጋዜጠኛውን ሳይሆን የራሱን የሚመቸውን ጥያቄ ጠይቆ ነበር  የሚመልሰው በዚህ ላይ የሃሳብና የቋንቋውን ጥራት ተመልካች ይፍረደው፡፡  ADDIS DIALOGUE-Prof. Berhanu Nega on Economy|etv – YouTube   እዚህ ላይ ጠያቂውም ሆነ ተጠያቂው ብርሃኑ ነጋ ሃሳባቸውን  በብቃት መግለጽ በማይችሉበት ቋንቋ መመላለስ ለምንስ አስፈለጋቸው?

#Ethiopia “የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የተደበቀው 4ኛው ቢሆንስ❓❗️ Professor Berhanu Nega | Abiy Ahmed|EZEMA Oct-03-2022 – YouTube

በመጨረሻም ጸሃፊው ዶ / ር ብርሃኑ ነጋን በግል አያውቀውም የሃገሩ ጉዳይ እንደሚከነክነው ዜጋ ግን ሃላፊነት የጎደላቸው ፖለቲከኞች ሃላፊነት በጎደለው መልኩ ሃገሩን እንደ ግል ካምፓኒያቸው ያሻቸውን ሲያተረማምሱት ቆሞ ለመመልከትም ሆነ  ለመታገስ አይሆንለትመ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ካንሰር የሆኑ ከነሱ በስተቀር ኢትዮጵያ ቁማ የማትሄድ የሚመስላቸው አዛውንት ፖለቲከኞች ነገር ከሚያሳክሩ መድረኩን በሰላም ለቅቀው አገሪቱ በአዲስ አስተሳሰብ  ከነዚህ አዛውንቶች ካንሰር አስተሳሰብ ተላቅቃ በሰላም እንደትኖር ማድረግ ግድ ይላል፡፡ በመሰረቱ መራራ ጉዲና፤ሌንጮ ለታ/ባቲ፤ዳውድ ኢብሳ፤አንዳርጋቸው ጽጌ፤አገኘሁ ተሻገር፤በቀለ ገርባ፤ ብርሃኑ ነጋ፤አባዱላ ገመዳ፤ዲማ ነገዎ፤የመሳሰሉ ቁሞ ቀር ፖለቲከኞች በቃችሁ ካልተባሉ የሃገራችን ችግር ይበልጥ ወደ ማጡ እንደሚወርድም ልዩ ምርምር አያስፈልገውም የነሱ ሃሳብ ቢሰራ ኑሮ ዛሬ አገራችን የአፍሪካ ጃፓን በሆነች ነበር፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሰመረ አለሙ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop