April 10, 2013
6 mins read

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አማሮቹን ያፈናቀልነው በስህተት ነው አሉ

በዘሪሁን ሙሉጌታ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አህመድ ናስር
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አማሮቹን ያፈናቀልነው በስህተት ነው አሉ 1

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው በጎጃም ፍኖተሰላም አካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረገው በስህተት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የተፈናቀሉት በሙሉ ቀደም ሲል ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑንም አስታወቁ።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰሞኑን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በሙሉ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀዋል።
በክልሉ ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኦሮምያ ከመሬት ጥበት፣ ከአፈር ምርታማነት ማጣት ጋር በተያያዘ የተሻለ መሬት ፍለጋ ሰዎች ወደ ክልሉ እንደሚገቡ የገለፁት አቶ አህመድ ነገር ግን ሰፈራው በሕገ-ወጥ መንገድ ሲፈፀም መቆየቱን አስታውሰዋል።
“እኛ የምንቃወመው በሕገ-ወጥ መንገድ በደን ውስጥ እየገቡ ደን እየመነጠሩ ሰፈራ ማስፋፋቱን ነው። ይህ ደግሞ ለክልሉ ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገርም አደጋ አለው” ያሉት አቶ አህመድ “በሕገ-መንግስታችን መሠረት ማንኛውም ሰው ለስራ ቢዘዋወር ችግር የለውም” ብለዋል።
ነገር ግን አሁን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት ለምን እንደሆነ ርዕሰ መስተዳደሩ ተጠይቀው ከታች ያለው አስተዳደር ስህተት በመፈፀሙ ነው ሲሉ አምነዋል። አስተዳዳሪዎቹ ሕዝቡን ያፈናቀሉት ሕገ-ወጥ ሰፈራውን ከነባሩ የመለየት ስራ ላይ ተናቦ የመስራት ችግር በማጋጠሙ ነው ብለዋል።
“አስተዳደራችን አካባቢ ስህተት ተፈፅሟል። መፈፀም ግን አልነበረበትም። ነገር ግን እንደ ክልል መንግስት በሕገ-ወጥ መንገድ የሰፈሩትን መቆጣጠር አለብን። ኅብረተሰቡ በፈለገው ጊዜና ወቅት እየተነሳ ደን እየመነጠረ መስፈር አስቸጋሪ ስለሆነ ስርዓት መያዝ አለበት የሚል አቋም አለን” ያሉት አቶ አህመድ ስህተት የፈፀሙ የአስተደደር አካላት ላይም ግምገማ በማካሄድ ማስተካከያ እናደርጋለን ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር ምክክር መደረጉንም ያስታወሱት አቶ አህመድ ችግሩ በድጋሚ ሊፈጠር የማይችልባቸውን ቀዳዳዎች ለመድፈን ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ወደ 1 ሺህ 346 አባወራዎች ከ3 ሺህ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲፈናቀሉ መደረጉን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ችግሩ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ጋር የተያያዘ መሆኑንም አስረድተዋል።
“በክልላችን አንዳንድ ቦታዎች ሰዎቹን ወደ አካባቢው ካስገቡአቸው በኋላ የሚታይ ችግር አለ። በተለይ ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ችግር አለብን። በየጊዜው እናጣራለን፤ እንጠርጋለን፣ እንገመግማለን ችግሩን ግን ሙሉ በሙሉ ማፅዳት አልተቻለም” ሲሉ ተናግረዋል።
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ክልሉ መግባትና መውጣት የሚያስችል ሕገ-መንግስታዊ መብቱ የተከበረ መሆኑን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም ከአማራ ክልል ወደ ክልላችን ለስራ በሚገቡበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ የክልሉ ደን እንዳይወድምና ጥበቃ እንዲደረግ ከአማራ ክልል ጋር ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
በትናንትናው ዕለት በፍኖተ ሰላም ከተማ ተፈናቃዮችን ወደመጡበት አካባቢ ለመመለስ 11 መኪኖች መዘጋጀታቸውንና ተፈናቃዮቹን የሚያጅቡ የፌዴራል ልዩ የፖሊስ ኃይል መታጀባቸውን የዓይን ምስክሮች ገልፀዋል።

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop