December 12, 2022
6 mins read

ምክር ቢጤ ለውድ እህቴ ለመስከረም አበራ

ጠላትህ ሲጀምር ራሱን ማጋለጥ፣ እስኪጨርስ ድረስ ታዘበው ብለህ ጸጥ

(Never interfer with your enemy while he is destroying himself, Napoleon Bonapart)

Meskerem Abera 1

ውድ እህቴ መስከረም አበራ፣ ፀራማሮች ከተለያዩ አቅጣጫወች የተለያዩ ጦሮችን ለምን እንደሚወረውሩብሽ አንቺው ራስሽ በደንብ ስለምታውቂ በዚህ ረገድ መካሪ እንደማያሻሽ አውቃለሁ፡፡  ይችን ምክር ቢጤ ለመክተብ የተነሳሁትም አንቺን ለመምከር ሳይሆን፣ ላንቺ ያለኝን አክብሮትና ድጋፍ ለመግለጽ ያህል ነው፡፡  ለጦቢያ አምላክ የምጸልየውም፣ የአማራ ሕዝብ ወያኔንና ኦነግን በማያዳግም ሁኔታ ድል አድርጎ ሕልውናውን ለዘለቄታው እስከሚያረጋግጥ ድረስ በያዝሽው መንገድ እንድትቀጥይ እንዲረዳሽ ነው፡፡  አንቺም ብትሆኝ ለምታመልኪው አምላክ አጥብቀሽ መጸለይ ያለብሽ፣ ከመንገድሽ መዳረሻ ሳትደርሽ በፊት፣ ባንድ ወቅት ጉምቱ ይባሉ እንደነበሩት የተለያዩ ግለሰቦች በተለያዩ ምክኒያቶች ተሰናክለሽ እንዳትቀሪና፣ እየደከምሽና እየተጎሳቆልሽ፣ እየተወረፍሽና እየተዘለፍሽ፣ እየታሰርሽና እየተፈታሽ የጣርሽውን ጥረት ሁሉ ውሃ እንዳይበላው ነው፡፡  የነብርን ጅራት አይዙም፣ ከያዙም አይለቁም፡፡

ደረጀ ዘለቀ የሚባለው ላፉ ለከት የሌለው፣ መረን የለቀቀ ስድ ግለሰብ፣ አንቺን የሚሳደብ እየመሰለው ራሱን በራሱ እየተሳደበ ከፍ ዝቅ አድርጎ ሊያዋርድሽ ሲሞክር ሰምቸዋለሁ፡፡  በዚህ ድርጊቱ በግልጽ ያስመሰከረው ደግሞ ግለሰቡ ጥራዝ ነጠቅ የእንግሊዘኛ ቃሎችንና ሐረጎችን እዚህም እዚያም እያስገባ ጉራማይሌ በመናገር ምሁር ለመምሰል የሚሞክር፣ ምሁርነት ሲያልፍም ያልነካው ተራ ካድሬ መሆኑን ብቻ ነው፡፡

ቀድሞውንም ቢሆን፣ ታላላቅ የአማራ ምሁሮችን ስልጣን በያዘ ማግስት ካዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በብጣሽ ወረቀት ያባረረው የወያኔ መንግስት፣ የወያኔን ፀራማራ አጀንዳ የማያራምድ ካልሆነ በስተቀር በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያስተምር ቀርቶ ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ዝር እንዲል እንደማይፈቅድለት የታወቀ ነው፡፡  የወያኔ አለቃ መለስ ዜናዊ በግልጽ እንደተናገረው፣ የወያኔ የሥራ መስፈርት የወያኔን አጀንዳ ማራመድ መቻል እንጅ ትምህርት አይደለም፡፡  የወያኔን አጀንዳ አራማጅ እስከሆነ ድረስ፣ ማንም ሰው በማናቸውም ቦታ ይቀመጣል፡፡  ቦታው ላይ ለመቀመጥ ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር መባል የሚበጅ ከሆነ ደግሞ ዶክተርነቱና ፕሮፌሰርነቱ ከሚመጣበት እንዲመጣ ይደረጋል፡፡

አፍ ሲከፈት ይታያል ማንነት እንዲሉ፣ የደረጀ ዘለቀ አፍ የሚያመለክተው ደግሞ ተራ ካድሬ ብቻ ሳይሆን ተራ ዱርየ መሆኑንና ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር ቀርቶ አቶ መባልም እንደሚበዛበት ነው፡፡  ለዚህ ነው አቶ ልለውም ያልፈለኩት፡፡  ለዚህ ደግሞ አንባቢን ይቀርታ እጠይቃለሁ፡፡

ደረጀ ዘለቀ በራሱ አንደበት እንደተናገረው፣ ምንም ያላደረጉትን፣ ከነመፈጠሩም የማያውቁትን አላፊ አግዳሚ መንገደኞ ከፍ ዝቅ አድርጎ እየተሳደበ አበሳጭቶ ማወራጨት ከልጅነቱ ጀምሮ የተካነበት፣ በሰፈሩ ልጆች የሚደነቅበት፣ አለቅጥ የሚኮራበት ልዩ ችሎታው ነው፡፡  ይህ ደግሞ የአሳማ ባሕሪ ነው፡፡  አሳማ ሲባል አረንቋ ውስጥ መጨማለቅ ስለሚወድና ከፍተኛ እርካታ ስለሚሰጠው፣ ዋና ምኞቱ ተጨማልቆ ማጨማለቅ ነው፡፡

ስለዚህም ውድ እህቴ መስከረም አበራ፣  ምንም ረብ የሌለው እንቶ ፈንቶ ጉራማይሌ ከዚህም ከዚያም እየለቃቀመ በፍየል ምላሱ ከመፈንተት በቀር ምንም ካልተከረ፣ በማናቸውም ረገድ ያንቺ ቢጤ ካልሆነ፣ የጨምላቃ አሳማ ባሕሪ ከተጠናወተው ከዚህ ከወረደ ግለሰብ ጋር ወደታች ወርደሽ፣ እሰጥ አገባ ገጥመሽ ተጨማልቆ እንዳያጨማልቅሽ በትህትና እመክርሻለሁ፡፡  ደረጀ ዘለቀ ስድ አፉን በመክፈት እውነተኛ ማንነቱን እሱ ራሱ እያሳየ፣ አንቺን የሰደበ ቢመስለውም እሱን ራሱን እየሰደበ ስለሆነ፣ ንቀሽ ተይው፡፡  መልስ እንዳትሰጭው፡፡

 

ካልተውት በስተቀር ንቀው ብለው ቀላል

ትንሽ ሰው ትንሽ ነው አንሶ ያሳንሳል፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
Go toTop