በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ታሪክ እነሚያስተምረውና አያቶቻችን እንደነገሩን በአምስቱ ዘመን የነፃነት ታጋድሎ በዝምታ የሕዝብን እልቂትና ባርነት የሚደግፍ ብዙም አልነበረም፡፡ ሕዝቡ በአንድ በኩል በሆዱ ለፋሽሽት ተገዝቶ ሰላይ፣ መንገድ መሪ፣ እንቁላል ቀቃይና አቃጣሪ በነበረው ወራዳ ባንዳና በሌላ በኩል ደግሞ በፋኖዎችና ፋኖዎችን በተለያዬ መንገድ በደጀንነት በሚደግፈው ጀግና አርበኛ የተከፈለ ነበረ፡፡ በዝምታ የፋሽሽትን ግፍ የደገፈ ብዙም ወስላታ አልነበረም፡፡
ተፋሽሽቶች የወረራ አላማ አንዱ ሕዝቡን በዘር ከፋፍሎ እርስ በርሱ እያባላ እስከ ዳግም ምጣት ለመግዛት ነበር፡፡ ገድል ሰርተው ባለፉት አርበኞችና በደጀኑ ሕዝብ ተጋድሎ ያ ተንኮሉ ሳይሳካ ቀረ፡፡ ተሞት የሚያመልጥ ስለሌለ ሕዝባቸውን ከድተው ፋሽሽትን ያገለገሉ እርጉም ባንዳዎችም በበሽታም በእርጅናም ሞተው በከረፋ የታሪክ ከፈን ተከፍነው ተቀበሩ፡፡ ዳሩ ግን አንሺ እንዳጣ የውሻ አስከሬን ተሚጠነባው ታሪካቸው ጋር ባንዳ ዲቃላዎቻቸውን ተክተው አለፉ፡፡ እነዚህ ዲቃላዎቻቸው ፋሽሽቶች ደጋግመው ሞክረው ያልተሳካላቸውን ሕዝብን በዘር ከፋፍሎ አገርን የማጥፋት ሳጥናኤላዊ ግብር በእጅ አዙር ቀኝ ገዥዎችና በታሪካዊ የአገር ጠላቶች እየታገዙ ተገብሩ፡፡
የዚህ ሕዝብን በዘር ከፋፍሎ አገር የማጣፍት ሰይጣናዊ ተልዕኮ ተዋናውያን በዝቅተኝነት መንፈስ ናላቸው ሲከረፋ የኖረ ጭራቆች ናቸው፡፡ እነዚህ ጭራቆች አማራዎች ዘራቸው እየተለዬ እርጉዝን ሆዷ እንድትቀደድ፣ ሕፃንና አሮጊት ከቤተክርስትያንና መስጊዲድ እንዲታረዱና እንዲቃጠሉ፣ የታረዱትም ተዘቅዝቀው እንዲሰቀሉ ወይም በጎዳና እንዲጎተቱ ትዕዛዝ የሚሰጡ አረመኔዎች (barbarians) ሆኑ፡፡
ሕዝብ ሆይ! ዘር አጥፊ ጭራቆች ነጭ ቆዳ ስላለበሱ ከአድዋው ወይም ከአምስቱ ዘመን ወረራ ለይቶ የማየት አባዜ የሆዳምና የዘመኑ ባንዳ ከንቱ ሰበብ ነው፡፡ ይህ የዘር ፍጅት ዘመን ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ከተደረጉት ወረራዎችና እልቂቶች ዘመን ሁሉ የከፋና የከረፋ ነው፡፡ ሞሶሎኒም ሆነ ግራዚያኒ በዚህ ዘመን የተደረገውን የሚመስል ወይም የሚያህል የጭራቆች ሥራ አልሰሩም፡፡ ሴት ልጆችን ጠልፈው እያጠፉ ወላጆች በእንባ ተነክረው እንዲሞቱ አላደረጉም፡፡ ቤተክርስትያንና መስጊድ ዘግተው ሕፃናትንና አሩግን በመደዳ አላረዱም ወይም አላቃጠሉም፡፡ እሬሳ ተምድር እየጎተቱ አልተሳለቁም፡፡ አይን እያዬ አይን ቆፍረው አላወጡም፡፡ ብልት አልሰለቡም ወይም አልቆረጡም፡፡ የሰው ኩላሊት ተሆድ እየፈነቀሉ አልበሉም፡፡ እርጉዝ በሰቀቀን ተቤቷ ወጥታ ተጫካ ወይም ተመንገድ ዳር ብቻዋን አምጣ እንድትወልድ አላስገደዱም፡፡ የዘር ማጥፊያው መንገድ ዝርዝር ማለቂያ የለውም፡፡
እግዚአብሔርንም ሆነ ታሪክና መጭውን ትውልድ የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ አውሬ በአውሬ ላይ የማፈጥመው ግፍ እየተፈጠመ አብዛኛው ሕዝብ ይኸንን ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በዝምታ መደገፉ ነው፡፡ የጋን ጠጅ በተኮለኛ ተገፍቶ ሲደፋና ሲፈስ ዝምብሎ የሚመለከት ሰው ከደፊው ተንኮለኛ ብዙም የማይሻል ከንቱ ነው፡፡ ሕዝቡ ዘሩ እየተመረጠ በሚታረድበት ሰዓት በጥቅም እየተገዛ ወይም የተለያየ ሰበብ እየደረደረ ተአራጆች ጋር ተደምሮ ዝም የሚል ሰው ከአራጆች ያላነሰ አረመኔ ነው፡፡ ሕዝብ መርጦ ባልተፈጠረበት ዘሩ ተገዛ አገሩ በሚታረድበት ሰዓት ተገዳይና አሰገዳይዎች ጋር የሚሰለፍ ወይም ድምጡን አጥፍቶ ቅሪላውን ሲሞላ ኖሮ ለማለፍ የሚጥር በፋሽሽት ዘመን ተነበሩት ባንዳዎችም የከፋ አረመኔ ነው፡፡ ጭራቆች የሚፈጥሙትን የዘር ፍጅት የማይቃወምና የማይታገል በዝምታ ፍጅቱን እንደ ደገፈ ታሪክና ትውልድ ሲዘግበውና ሲረግመው የሚኖር ነው!
ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.