December 6, 2022
22 mins read

በወለጋ ኦሮምያ ክልል በንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደው የዘር ጭፍጨፋ ከመቸውም በላይ አሳስቦናል

ህዳር 26፣ 2015 (December 5, 2022)

 

ለክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚ/ር

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

balege

ጉዳዩ፡ በኦሮምያ እና በቤንሻንጉል በንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ የሚካሄደውን የዘር ጭፍጨፋ ለማስቆም በቅድሚያ የችግሩን መኖር አምኖ መቀበልን ይጠይቃል!

የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትዎርክ ለማህበራዊ ድጋፍ (ኢክናስ) የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ሠላማዊ ህይወት ለመሸጋገር የሚያደርገውን ትግል እና የለውጥ ሂደት ለማገዝ ላለፉት 24 ወራት እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዘርፈ ብዙ ድጋፎቹ ውስጥ ለሕዳሴው ግድብ፣ ለኮቪድ-19 ፣ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በህወሃት ጦርነት ምክንያት የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም ያደረገው የገንዘብ እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም የውጭ እና የውስጥ ሃይሎች በአገራችን ላይ የሚያሰራጩትን የተዛባና የተሳሳተ አመለካከት ለማክሸፍ እና ተጨባጩን ሁኔታ በማስረጃ እያቀረበ ለዓለም ማሕበረሰብ በስፋት ማስተዋወቅ ይገኙበታል። በዚህም አስተዋፅዎው ምክንያት ኢክናስ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም ከፍተኛ አድናቆትና ክብር ተችሮታል።

ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም በመተከል፣ በወለጋ እና ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በንፁሃን ዜጎች ላይ በማንነታቸው ምክንያት ብቻ የሚደርስባቸው ጅምላ ግድያ እና መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም መግለጫዎችን በተደጋጋሚ በማውጣት እና ለአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደብዳቤ በመፃፍ እና ፊት-ለፊት ችግሩን በማስረዳት ሲያሳስብ እና ሲማፀን ቆይቷል።

የፖለቲካ ውግንና የሌለው ድርጅታችን ይህንን ሁሉ ሲያደርግ የቆየው በአንድ መርሕ ላይ ቆሞ ነው። ይሄውም የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለአገር የሚጠቅም ሥራ ሲሰሩ የማመስገን እና የማበረታት፤ አገራችንን እና ህዝባችንን የሚጎዳ እና ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ሲፈጽሙ ደግሞ የመተቸት እና የመቃወም ግዴታ አለብን የሚል ነው። ይህ ደግሞ ጤናም ብቻ ሳይሆን መገንባት ለምንፈልገው ዴሞክራሲ ትልቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ከሚል እምነት የመነጨ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘብው ይገባል።

ይሁን እንጂ አሁንም በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ወንጀል ተባብሶ መቀጠሉ ከመቸውም በላይ አሳስቦናል። በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተጨፍጭፈዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል። ዜጎች ከታፈኑ በኋላ ዘራቸው እየተመረጠ ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፤ ንብረታቸው ይዘረፋል ወይም ይወድማል። የወንጀሉም መጠን አድማሱን እያሰፋ ከወለጋ እና ከመተከል አልፎ በመሃል ኢትዮጵያም እየተፈፀመ ይገኛል። የፌደራሉም ሆነ የክልል መንግስታት በተደጋጋሚ የሚሰጡት መግለጫ “በኦነግ ሸኔ ላይ እርምጃ ተወሰደ”፣ “ኦነግ ሸኔ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠራርጎ ይጠፋል”፣ “ጥቃቱ በአንድ ዘር ላይ ብቻ ያተኮረ አይደለም”፣ ”ከወንጀሉ ጀርባ ህውሃት አለበት” ወ.ዘ .ተ የሚል ነው። እንዲህ ዓይነት ተጨባጭ ያልሆኑ መግለጫዎች ህዝብን የሚያዘናጉ እና ችግሩም ተድበስብሶ እንዲታለፍ ከማድረግ ውጭ ለችግሩ መፍትሄ አያስገኙም።

መንግሥት ብዙ ወገኖቻችን ካለቁ እና ኦነግ ሸኔም የመንግሥትን ባለሥልጣናት ጭምር መግደሉን በተግባር በማሳየቱ የመከላከያ ሃይል ፀጥታ ለማስከበር ጥረት ማድረጉን ብንገነዘብም ይህ ሙከራ እስካሁን ድረስ ውጤት አላስገኘም።

በዚህ ረገድ ኢክናስ በተለይ በኦሮምያ የሚካሄደው የዘር ጭፍጨፋ እንዳይቆም ምክንያት የሆኑት የሚከተሉት ናችው ብሎ ያምናል፡

 

  • በንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደረገውን ዘርተኮር ጥቃት መካድ ወይም ማሳነስ

ት.ህ.ነ.ግ መራሹ የ ኢ.ህ.አ.ዲ.ግ መንግሥት ሥልጣን ከያዘበት 1983 ዓ.ም በፊትም ሆነ በኋላ ዜጎች ሃሳባቸውን በመግለፃቸው፤ ለነፃነታቸው እና ለሰብዓዊ መብታቸው በመታገላቸው ተሰቃይተዋል፣ ታስረዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ተገድለዋል።

 

  • ህ.አ ዲ ግ ሥልጣን ከያዘበት ወቅት በኋላም ይህ አሳዛኝ ድርጊት የቀጠለ ቢሆንም በብሄር ላይ የተመሰረተው የፖለቲካ ሥርዓት ከተተከለ ወዲህ ግን በብሄራቸው ማንነት ብቻ እየታደኑ የሚገደሉ ንፁሃን የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ናቸው። በዚህ ረገድ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና በሃገሪቱ የፖለቲካ የበላይነት ያላቸው የብሄር ፖለቲካ ድርጅቶች ኦነግ-ሸኔ አማሮችን ሲጨፈጭፍ “የሌላ ብሄር ተወላጆችም ተገድለዋል” የሚል መከራከሪያ በማቅረብ ችግሩን ሲያቃልሉት ይታያሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ መንግሥታት የግፍ ሥርዓቶች ቢፈራረቁበትም ህዝቡ ግን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ህይወቱ ተሳስሮ በጉርብትና በመኖሩ የሌሎች ብሄረሰቦች ተወላጅ የሆኑ ብዙ ወገኖቻችን በተለይም የኦሮሞ ተወላጆች በንፁሃን አማሮች ላይ የሚደረገውን ግድያ እና ወንጀል በመቃወማቸው ህይወታቸውን አጥተዋል። ከዛም በላይ ኦነግ-ሸኔ የመንግስትን እና የብልፅግና ፓርቲ ባለሥልጣናትን እንዲሁም የመንግሥት ፀጥታ ሃይል አባላት የሆኑ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን መግደሉ ይታወቃል። ይህ የሚያሳየው ኦነግ-ሸኔ ዘረኛ የሆነውን የፖለቲካ ዓላማውን ለማሳካት እታገልለታለሁ ለሚለው የኦሮሞ ህዝብ ጭምር የማይመለስ መሆኑን ቢሆንም በመሠረቱ ግን ድርጅቱ ዓላማውን ለማሳካት ጥቃቱን ያነጣጠረው በንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ መሆኑን ለመካድ አይቻልም።

 

 

  • የፖለቲካ ድርጅቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ዝምታ እና ድጋፍ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የተሰጣቸው እና “በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን”፤ ከዚያም በላይ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ያህል “ለሰብዓዊ መብት እንቆረቆራለን” የሚሉ በተለይ የብሄር ድርጅቶች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ከመካድ እና ከማሳነስ አልፈው ጭራሹኑ እየተጠቁ ያሉት የነሱ ብሄር ተወላጆች እንደሆኑ እና ጥቃቱንም የሚፈፅሙት አማሮች እንደሆኑ አድርገው ሲያቀርቡ ይደመጣሉ። ለዚህ አንዱ ምሣሌ በህጋዊነት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ነው። መንግሥት በኦሮሚያ የሚያደርገውን የፀጥታ ማስከበር እንቅስቃሴ “መንግሥት እና የአማራ ፋኖ ንፁሃን ኦሮሞዎችን ጨፈጨፉ” በማለት ሃቅን እያዛባ እና ህዝብን እያደናገረ ይገኛል። ህጋዊ የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባለሥልጣናት ትርክትም ከዚህ የተለየ አይደለም። በተመሳሳይ ሁኔታ ለሰብዓዊ መብት እና ለኢትዮጵያ ሠላም እንታገላለን የሚሉ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን መንግሥትን መምከር ወይም መተቸት መንግሥትን ማሳ’ጣት ስለሚመስላቸው፤ ወይም ደግሞ ለአማራ ተወላጆች መብት መከራከር የዘረኛነት ሥም ያሰጠናል በሚል ዝምታን መርጠዋል። ለነዚህ ወገኖች ያለን ጥያቄ፡ “ሰብዓዊ መብት አማራን አይጨምርም ወይ? መንግስትን መተቸትስ መንግሥትን መደገፍ አይደለም ወይ? ” የሚል ነው። የዚህ ዝምታም ሆነ የጥቃቱን ሰላባ ማንነት ለመናገር አለመፈለግ ውጤቱ መንግሥት

 

በቁርጠኝነት ይህንን ችግር ያስወግድ ዘንድ ጫና እንዳይደረግበት ማድረጉ እና የኢትዮጵያን ህዝብም ለሃሳብ መከፋፈል እና መደናገር(State of confusion) ማጋለጡ ነው።

 

  • የባለሥልጣናት ተጠያቂነት እና ግልፅነት አለመኖር

መንግሥት በተደጋጋሚ በኦነግ-ሸኔ ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ቢልም ውጤት ያላመጣው ድርጅቱን የሚደግፉ የመንግሥት እና የፓርቲ ባለሥልጣናት ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድረስ ባለው መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው በመገኘታቸው መሆኑን የጥቃቱ ሰለባዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት እና የፓርላማ ባለሥልጣናት ጭምር የመሰከሩት ጉዳይ ነው። በዚህ ረገድ መንግሥት እነዚህን ባለሥልጣናት ተጠያቂ ሲያደርግ፣ ከሥልጣን ሲያባርር እና እርምጃ ሲወስድ አለመታየቱ እና ወስዶም ከሆነ በግልፅነትና በማስረጃ ማንነታቸውን ለህዝብ በማሳየት አለማረጋገጡ “መንግሥት ራሱ ተባባሪ ነው” የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ በህዝብ ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል።

 

  • የሰሜኑ ጦርነት የመንግሥትን እና የህዝብን ትኩረት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ
  • ወ ሃ ት በሰሜን ጦርነት ሲከፍት ግዙፍ የመከላከያ ሃይል ገንብቶ፣የአገሪቱን የጦር መሣሪያ ዘርፎ፣ በሥልጣን ዘመኑ የገነባውን የፕሮፓጋንዳ እና ኢኮኖሚ አቅም ይዞ እና ተገዶ የለቀቀውን የመንግሥት ሥልጣን መልሶ ለመያዝ መጠነ-ሰፊ እንቅስቃሴ አድርጎ ነው። በዚህም የተነሳ ወረራውን ለመመከት የመንግሥትን እና የህዝብን ሙሉ ትኩረት እና ዝግጅት ጠይቋል። በአንፃሩ ኦነግ-ሸኔ የፖለቲካ ዓላማውን ለማሳካት የመረጠው ታክቲክ በኦሮምያ ክልል ያሉ ንፁሃን አማሮችን መግደል፣ ማፈናቀል እና ለፍተው ያፈሩትን ሃብት መዝረፍ እና ማውደም እንጂ ከመከላከያ ሃይል ጋር ፊት-ለፊት በመዋጋት እና አካባቢዎችን በመቆጣጠር ባለመሆኑ በመንግሥት በኩል ኦነግ-ሸኔ ለሥልጣንም ሆነ ለአገር ደህንነት አደጋ ይሆናል የሚል ተመሣሣይ ትኩረት ሊያገኝ አልቻለም።

 

መንግሥት ለኦነግ-ሸኔ የሰላም እጁን የዘረጋ መሆኑን ኢክናስ ቢገነዘብም ኦነግ-ሸኔ ግን ዘግናኝ ወንጀል መፈፀሙን ቀጥሎበታል። ማንኛውንም ዓይነት የፖለቲካ ጥያቄን ለማሳካት ንፁሃንን የጦስ ዶሮ አድርጎ የዘር ማፅዳት ዘመቻ ማድረግ ከወንጀሎች ሁሉ የላቀ ወንጀል ስለሆነ ችላ ሊባል አይገባም። ይህንን ወንጀል ለማስቆም መንግሥት ሃላፊነቱን ካልተወጣ በታሪክ ተጠያቂ ይሆናል። ስለዚህ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች አምኖ በመቀበል በእቅድ እና በቁርጠኝነት አስፈላጊ የሆነውን የፀጥታ ማስከበር እና ንፁሃንን የማዳን እርምጃ መውሰድ ይገባዋል። የሚመለከታቸው የፖለቲካ ድርጅቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያንም ይህ የመንግሥት እርምጃ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ድጋፍ እና ጫና ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

 

በዚህ ረገድ የፌደራሉ እና የክልል መንግሥታት የሚከተሉትን እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን፦

 

  1. በተሳሳተ የብሄር ፖለቲካ ትርክት ምክንያት የአማራ ብሄር ተወላጆች የኦነግ-ሸኔ እና የሌሎችም ዘረኛ ድርጅቶች ሰለባ እንዲሆኑ መደረጋቸውን በማመን መንግሥት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታውን በቁርጠኝነት እና በብቃት እንዲወጣ፤ ንጹሃንን የሚገድሉ እና ህዝብን የሚያፈናቅሉ ወንጀለኛ ቡድኖች እና ግለሰቦች ያለምንም ማመንታት በቁጥጥር ስር ውለው ለህግ እንዲቀርቡ፤

 

  1. በኦሮምያ እና በቤንሻንጉል የሚደርሱ የዘር-ተኮር ጥቃቶችን በሚመለከት የክልሎቹ መሪዎች እና የሚመለከታቸው የፌደራል መንግሥት ሃላፊዎች እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን ዕውነታውን ለህዝብ እንዲያስረዱ፣ የተጎዱ ዜጎችን እንዲጎበኙ፣እንዲያፅናኑ እና አስፈላጊውን ዕርዳታ ሁሉ እንዲያቀርቡ ፤

 

  1. በብሄርም ሆነ በህብረ-ብሄር ደረጃ የተቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን የዘርተኮር ጥቃትን በሥሙ በመጥራት መንግሥት ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጫና እንዲያደርጉ

 

  1. ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድርስ በተዘረጋው አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ሃላፊነታቸውን መወጣት ያልቻሉ ወይም የወንጀሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የፀጥታ ሃላፊዎች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ እና ለፈፀሙት ወንጀል በህግ እና በግልፅ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣

 

  1. መንግሥት ለሰሜኑ ጦርነት ከሰጠው ትኩረት ባልተናነሰ ደረጃ በቂ የመከላከያ ሠራዊት እና ትጥቅ በማደራጀት ተደጋጋሚ የሆነ ጥቃት በሚፈፀምባቸው ቦታዎች እንዲያሰማራ እና የአካባቢዎቹ ፀጥታ እስኪረጋገጥ ድረስ በቋሚነት እንዲሰፍር እና ህዝብን እንዲያረጋጋ መመሪያ እንዲሰጥ፤

 

  1. በኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ ሠላም ለማረጋገጥ፣ ዜጎች ሁሉ በነፃነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የመኖር እና ሃብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር፣ እንዲሁም ሁሉም በእኩልነት የሚስተናገዱባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚቻለው አገሪቱ የተከተለችው ቋንቋን እና መሬትን ያስተሳሰረው የፖለቲካ ሥርዐት እና ህገ-መንግሥት ዕርምት ሲደረግበት ብቻ ስለሆነ መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት እና የሲቪል ተቋማት ሁሉ ለዚህ ሥኬት አገራዊ ምክክር በአስቸኳይ እንዲጀምሩ እና ኢትዮጵያን ከማያባራ ግጭት እና ጦርነት እንዲታደጉ።

 

 

ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና ጥንካሬ ህልውናዋ ይጠበቃል!

የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ (ኢክናስ)

 

ግልባጭ፦

  1. ክቡር አቶ ደመቀ መኮነን-የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ ጠ/ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
  2. ክቡር አቶ ታገሠ ጫፎ- የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ
  3. ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር- የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ
  4. ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ- የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት
  5. ክቡር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ- የአማራ ክልል ፕሬዚደንት
  6. ክቡር አቶ አሻድሊ ሐሰን-የቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ፕሬዚደንት
  7. ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ-የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ ሠራዊት ጠ/አዛዥ
  8. ክቡር አቶ ፍፁም አረጋ- በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር

ETHIO CANADIAN NETWORK FOR ADVOCACY AND SUPPORT

ኢትዮ-ካናዳውያን ኔትዎርክ ለማህበራዊ ድጋፍ ETHIO-CANADIAN NETWORK FOR ADVOCACY AND SUPPORT

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop