· አምስት የወንጀል ሪከርዶች አሉበት ተብሏል
በአሸናፊ ደምሴ
በቀድሞ ባለቤቱ ላይ በቂም በቀል ተነሳስቶ በስለት የታገዘ የግድያ ሙከራ ፈፅሟል በሚል ዐቃቤ ህግ ክስ የመሰረተበት ግለሰብ በ15 ሺህ ብር የዋስትና መብቱ እንዲከበር መፈቀዱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው የክስ ዝርዝር ውስጥ እንዳስረዳው ተከሳሽ ነጂብ አብደላ ሰውን ለመግደል አስቦ በመጋቢት 11 ቀን 2005 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9፡30 ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታው ቦሌ መድሃኒአለም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ሬድዋን ህንፃ 1ኛ ፎቅ ውስጥ፤ የግል ተበዳይና የቀድሞ ባለቤቱ የነበረችውን ማሪያ የኑስ በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት በሃይማኖታቸው መሰረት በስምምነት የተፋቱ ሆኖ ሳለ፤ ለመግደል አስቦ ቢለዋ እና አርቴፊሻል ሽጉጥ በማዘጋጀት በተበዳይ ስም የተዘጋጀ ቼክ መኖሩን በመግለፅ ቢሮው ድረስ መጥታ እንድትወስድ በማግባባት ወንጀሉን ለመፈፀም ስለመሰናዳቱ ያትታል።
ወንጀሉ በተፈፀመበት እለትም ከተከሳሽ ጋር አብራ ትሰራ የነበረች ፀሐፊ “ዛሬ የቤተሰብ ጉዳይ አለ” በሚል ሰበብ ወደቤቷ እንድትሄድ በማድረግ፤ የግል ተበዳይ ወደቢሮው ስትገባ በሩን በመቆለፍ እና በሲጃራ መተርኮሻ ሁለት ጊዜ ጭንቅላቷን በመምታት እንዲሁም በአርቴፊሻሉ ሽጉጥ በማስፈራራት “የኔን ህይወት አበላሽተሸ አትኖሪም” የሚል ሀይለ ቃል መናገሩ በክስ ዝርዝር ውስጥ ሰፍሯል።
በወቅቱም የተበዳይን አይን ለማጥፋት አዘጋጅቶት የነበረውን ስለት ወደአይኗ ቢሰነዝርም ራሷን ለመከላከል ባደረገችው ጥረት የፊት ቆዳ መሰንጠቅና አራት ቦታዎች ላይ በመውጋት ደም እንዲፈሳት ቢያደርግም፤ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የፖሊስ ሃይል ጠርተው በሩን በጉልበት በመክፈት ህይወቷ የተረፈ ሲሆን፤ ተከሳሹም በከባድ የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ የተመሰረተበት መሆኑን ይገልፃል።
ዐቃቤ ህግ በፖሊስ የምርመራ ስብስብ ላይ በመንተራስ ክስ የመሰረተ ቢሆንም ሂደት ላይ እያለ ተከሳሽ ያቀረበውን የዋስትና መብት ጥያቄ የተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት የተከሳሹን የዋስትና ጥያቄ በመቀበል በ15ሺ ብር ዋስትና ከማረሚያ ቤት ወጥቶ ጉዳዩን እንዲከታተል ሰሞኑን ወስኗል።
ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት እና በቦሌ ፍትህ ጽ/ቤት የፌዴራል አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ እምሽታው ተሰማ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አምስት ወንጀሎች ሪከርድ ያለበት በመሆኑ በዋስ ቢለቀቅ ወደፍርድ ቤት ቀርቦ ይከራከራል የሚል እምነት የለኝም በማለት አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሹ ለፖሊስ በሰጠው ቃል ተበዳይን አጥፍቶ እራሱንም የመግደል ሀሳብ የነበረው መሆኑን በመጥቀስ ምናልባትም ከማረሚያ ቤት ከወጣ የከፋ ወንጀል ሊፈፅም ይችላል ብለዋል።
ይህንና መሰል ስጋቶችን በመዘርዘር ቅሬታ እንዳላቸው የጠቀሱት ዐቃቤ ህጉ በተሰጠው የዋስትና መብት ላይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቃቸውንም አስታውቀዋል።
(ምንጭ ፡-ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 396 ረቡዕ ሚያዝያ 02/2005)
በአሰቃቂ ሁኔታ የቀድሞ ባለቤቱ የግድያ ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ የዋስትና መከበር አነጋጋሪ ሆኗል
Latest from Blog
ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::
የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር
እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?
ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው
በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ
January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ
አህጉራችን እና እኛ
ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ