September 21, 2022
25 mins read

የሎንደኖቹ ጥቂት የዲያስፖራ ይሁዳዎችና ዘራፊዎች ቅሌት!! (ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ)

እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም አምላክን የምናምን ፣ ፍሪሃ እግዚአብሔር የተላበስን  በአምሳሉ ለፈጠረው የሰው ልጅ ክብር ያለን ፣ ለሰባዊ ፍጡር ደህንነት በፅሞና የምንፀለይ ፣ አምላክ በአምሳሉ የፈጠረውን በሃሰት ወንጀለን  ለበልአ-ስብ አሳልፈን የማንሰጥ ኩሩ ሕዝቦች ነን።

ከአምላክ ጋር የሚያላትም ስራ የሚፈፅሙት (የእናት ሆድ ዥጉርጉ) እንዲሉ እንጨት አምላኪዎች፣ ባዕድ አምልኮ የተጠናወታቸው የሰይጣን ቁራጮች ፣ ወፍ ዘራሾች፣ መነሻችውንና መድረሻችውን የማያውቁ ጥቂት የሰው ሃገር ጥዮፍ ባህል የተጠናዎታቸው ሳጥናኤሎች  ግን አይጠፉም “ከስንዴ መሃል እንክርዳድ “ አይጠፋምና።

ለዚህ ነው የምንገስፃችሁ፣ የምንመክራችሁ። “ እነ ታጥቦ ጭቃዎች” እሁንም ሰው ሁኑ” እንላችኋለን።

እንደ እናንተ ያለውን በሱልጡኑ ዓለም እየኖራችሁ ያልሠለጠናችሁ ነፍሰ በላዎች አሥርቱን የአምላክ ትዕዛዛት ጥሳችሁ፣  ወድሞቻቸሁንና እህቶቻቸሁን  አሳልፋችሀ የምትሰጡ ደናቁርቶችን፣ የአራጆች ልጆች ለማስተማር መጰጰስ፣ መቀሰስና ክህነት መውሰድ የግድ ላይለን ይችላል።

ስማ /ስሚ/ ጌታ እየሱስ በጌተሰማኔ ፣ በእየሩሳሌም ወዘተ እየተዘዋወረ ባስተማረ፣ በፈወሰ፣ ዓላዛርን ከሞት ባስነሳ ወዘተ የዘሩ ክፋይ የሆነው ይሁዳ በሰላሳ ዲናር አሳልፎ ሰጠው።

በምራዕቡ ዓለም የተደነጎራችሁ አንዳንድ “የቀን ድቡሽቶች”  ፍልፈሎች ፣ ገንዘብ ህይወታችውና ህልውናችሁ የሆነ ዘራፊዎች “ የምድር ዓሳማዎች” ፣ “በልቶ ለበይ አትስጡን ፣ ሰው በቁመናው እየፈረሰ ፣ የፈረሰ ትምህርት ቤት ልናሰራ ነው ማለቱ ወቅታዊ አይደለም ፣ “አጢያቱን እንደ ጺላጦስ ታጥቦ አዲስ አበባ ከተሞ ለተወሸገ ባለስልጣን  መልእክተኛ አትሁኑ ፣ አታሽቃብጡ”።

ዳንኤልን ከአንበሳ ምንጋጋ ያወጣ አምላክ ንፁሃንን ይታደጋልና ፣ ለማየት ይብቃችሁ ይሄ ትንቢት ነው “በንፁሃን እግር እናንት ትቀፈደዳላችሁ፣ ሌቦችና ዘራፊዎች፣ አዘራፊዎች  ናችሁና።

እንቅልፍ አተኙም፣ በደላችሁ ማታ ማታ ያቃዣችኋል። ለነገሩ ጤነኛ መሆናችሁም ያጠራጥራል።

“ የባሰ አለ ሃገርህን አትልቀቅ” እንዲሉ አንዳንድ በዲያስፖራ የከተሙ ዕምነተ ቢሶች ፣ ማተብ የቆረጡና ተኩላዎች ቀለም የቆጠረውን ፣ አማኙን ፣ በስደት ናላው የናወዘውንና ግራ የገባውን ስደተኛ እንደ ሕፃን ልጅ “ ኩኩ መለኮቴ፣ መሃረሜን ፣ ያያችሁ፣ አላየንም እባካችሁ” እያለ እንዲጫወትላችው የሚዳዳቸውና ዐይናችሁን ሸፍነን እንዝረፋችሁ የሚል እሳቤ ያላችው ባጅባጆች በሰፊውና በገፍ ተሰማርተዋል።

እነዚህ የእንግዲህ ልጆች ሃገር ቤት ቅጥ ያጣውን ዘረፋ ፣ ጉቦኝነትና ሙስና ተላምደውት ፣ ተምረውት ፣ተክነውበትና ገልብጠውት በዲያስፖራ ደግሞ “ከምን ጋር የዋለች ምን ተምራ ትመጣለች “ እንዲሉ ስርቆትን ፣ ቅሚያውን ፣ ዝርፊያውንና ማታለሉን ዘመናዊ በሆነ መልኩ ይህ ጥዩፍ ተግባር እርም በሆነበት በምዕራቡ ዓለም  አንቴናቸውን ገትረው መዝረፉንና ማዘረፉን ተያይዘውታል።

የሚገርመው ደግሞ ልዝርፊያና ለዘራፊ ቡድን ገንዘቡን ለመሰብሰብ የሚያሳዮት የፈሪ ድላ በማስፈራራትና በቅጡ ከማያውቋትና በስማ በለው “የእኛ ናት” ከሚሏት አዲስ አበባ ጊዜ አግኝተው የተሰየሙ ውስን ግብስብስ  ባለስልጣኖች እና በየ ዓለሙ ከተወዘፉ ሆድ አደር የኢምባሲ ተሿሚወች ጋር ገጥመው ፣ ጋሻ ጃግሬ ሁነው ና እየተላላሱ ነው።

እኛ ኢትዮጵያዊያን አሁን የምንመክራችሁ ፣ ይህ አካሄድ ግን “ ከሩቅ ወዳጅ ፣ የጎረቤት ባህድ ይገደለኝ ፣ ስታመም ጠያቂየ፣ ስሞት ቀባሪየ ነው” እንዲሉ ለወያኔም አልበጀም እንላችኋለን። አስቡበት።

እኛ ኢትዮጵያዊያንና የሰው ልጅን በእኩል ዐይን የምናይ ፣ ከሌላ ምድር ቦረናን አቋርጦ የመጣውን ሳይቀር ሰው ፣ ሰው እንዲሸት ያደረግን ስልጡን ሕዝቦች ነን።

ነገር ግን አማራ ስለተጎዳ ፣ ትምህርት ቤቱና ተቋማቱ ፈረሰበት ብላችህ  ስማችን ለማርከስ ፣ ከከፍታችን ዝቅ ለማድረግና የሌለ ታፔላ ለመለጥፍ የምትሞክሩና የምታክሩ የማንም ስድ አደጎች በማንነታችን አድትነግዱ አንፈቅድም ፣ አይሆንምም ።

አስፈላጊ ከሆነ ሰላም ሲወርድ እኛው አማሮችና አፋሮች መልሶ ለመንገንባት “አቅሙ አለን” “እንላችኋለን፣ የአዞ ዕንባችሁንና ቅቤ እንጓችነታችሁን ለማያውቃችሁ አዠቅዥቁት።

በጎን ከመኖሪያ ቤታችሁና ከድርጅታችሁ ምድር ቤት እየተሰበሰባችሁ ከኦነግ ሸኔና ኦነግ ጋር  እየተማከራችሁ አማራን እያስፈጃችሁ “የአማሮችንና የአፋሮችን ት/ቤት ልናሰራ ነው ገንዘብ አዋጡ” ማለት የፌዝም ፣ ፌዝ ነው። እያንዳንድሽ እስከ ዘር ማንዘርሽ ኦነግ ፣ የዳቦ ስም የተሰጠው የሸኔ አባላትና አቀንቃኝ መሆናችሁን እናውቃለን። “ኧረ አታስቁን”።

“ሆድ ሲያውቅ ደሮ ማታ” እንዲሉ ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ዲያስፓራውን ወደ ሃገር ቤት እንዲገባ ሲጠሩ ብዙዎቻችሁ ተግተልትላችሁ የሄዳችሁ መሆናችሁን እናውቃለን።

ከዚያም አልፎ “ እቅምን አውቆ መኖር መልካም ነው፣ ታላቅ ችሎታ ነው “ ብሎ ዘፋኙ የዘፈነውን እረስታችሁና ወደጎን ብላችሁ “ ትምህርት ቤት እናሰራለን ፣ ኢንቨስት እናረጋለን ፣ ሃገረ ኢትዮጵያን ከድህነት መንግለን እንወጣለን ፣ በህግ ማስከበር ጦርነቱ ወላጃቸውን ላጡ ሕፃናት ማሳደጊያ የበጎ አድራጎት ሕንፃ እንገነባለን ” ወዘተ ብላችሁ፣ ቱሪናፋ ነፋታችሁ መመለሳችሁ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ይህ አካሄድ በጅላንፎው ወያኔ ጊዜ የለመዳችሁት ስለሆነ፣ በጅላጅሉም ብልፅግና ከቀጠለ ይቅናችሁ።

መቸም “የእውሸት ቋት” ናችሁና ፣ በምትኖሩበት ሃገር ቤተሰባችሁን በቅጡ  መምራት አቅቷችሁ የምትንገዳገዱ ፣  ከጊዜ ጊዜ ፣ ከዚያ ከዚህ እየዘለላችሁ፣ እንደ አለሌ አህያ ባገኛችሁት ላይ የምትጠላጠሉ መሆናችሀን አገር ምድሩ ያውቀዋል።

“ለማያውቅሽ ታጠኝ እኛስ ፣ እናውቅሻለን” እንዲሉ ውጭ ያለውን ዲያስፖራ ግራ አጋብታችሁ፣ ግራ የገባውን  የኢትዮጵያ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣን ተብየ አደናግራችሁ የኢንዱስትሪ መገምቢያ መሬት ፣ የበጎ አድራጎት ማቋቋሚያ መሬት ፣ ለየግላችሁ የመኖሪያ ቤት መገንቢያና ኮዶሚኒየምም ሳይቀር ከአዲስ አበባዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤና በየክልሉ  እደተቀበላችሁ ሹክ ተብለናል።

ተመልሳችሁ ወደ ጎራችሁ የስደት ዛኒጋባ ስትዘልቁ ፣ ሳት ጎርሶ ፣ ሳት ልብሶ  ዲያስፓራው አንገታችሁን ይዞ ፣ ገርቦ ለጉርቦ ተናንቆ “የዘረፋችሁትን ገንዘብ አወራርዱ!!” እያላችሁ ነው።

ለአዳነች አበቤና ለባለስልጣናቱ በቅዥት ቃል የገባችሁትን ቱሪናፋ ገንዘብ ሰባስባችሁ ተግባራዊ ለማድረግ ዳገት ሲሆንባችሁ ፣ መቸም “ተኩላ አንዴ ከበላ ጦም ማደር አይቻለውምና” የረቀቀ ዘዴ ዘየዳችሁ።

እሱም በሕወሃት ትግራይ ጠብ ጫሪነት ህይወታቸውን ባጡ ፣  በደሙት ፣ በተፈናቀሉት፣ በተደፈሩት፣ እንደ ራሄል የፅንስ ሽል አፈር ጋር የተቀላቀሉትንና  ‘ዋይ ፣ ዋይ’ ባሉት ሕፃናት ደምና ስም ለመነገድ ቋመጣችሁ፣ እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሀ።

ለዚህ አረመኒያዊ ስራችሁ ተሰባስባችሁ ዘየዳችሁ ፣ አማራውን በኤርትራ በርሃ መና አርጎና አስረሽኖ ስልጣን ላይ ጉብ ያለውና ሰሞኑን ደግሞ “የግዕዝ ቁጥር የመጣው ከግሪክ ነው”  ብሎ በሃገረ ኢትዮጵያ ተሳልቆ በስርዓተ ትምህርት አስፍሮ የረጨውን የቀድሞውን የቅንጅት ፣ ግንቦት-7፣ ቀስተ ደመና ፣ ኢድሃቅና አዜማ ሊቀመንበር አለቃችሁንና ዘመዳችሁን “ብርሃኑ ቦንገርን’ በመጋበዝ ሌላ ዓለም ያልተደረገ የእውሸት ድራማ ሰርታችሁ የዲያስፖራውን ሆድ እንዲቦጫቦጭ በመሞከር የማዘረፍና የመዝረፍ ከንቱ ስልታችሁን ዘረጋችሁ።

የድራማውን ህሳቤ እውነት ለማስመሰልና ለማጭበርበር ደህና ፣ ተቀባይነት ያለው የአማራ ወዳጅ መሰል ገፀ ባህርያት ብትጠቀሙ ባልከፋ።

“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” እንዲሉ በዚህ ኮሚቴ ከተካተቱት ቁንጮዎቹ አንዳንዶቹ ከተራ ተከታይ ጅራቶቻቸሁ በስተቀር የእንግሊዝ መንግስት ባወጣው ህግ መሠረት  የዕድር ፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና መሰል ተቋማትን የምትመሩ መሆናችሁ ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህ አካሄዳችሁ ከእንግሊዝ መንግስት ሕግጋት ጋር እንደሚጣረዝና በህግም እንደሚያስጠይቃችሁ መቸም እኛ ሩሩሆች ነነን “ተጠንቀቁ” እንላለን

“ዐይኔ እባክህ አትሳቅ ፣ ጥርሴስ ልማዱ ነው” እንዲሉ ደግሞ ከዚህ በፊት በአማራ ክልል በቅማንት የህወሃት ተላላኪ አማፂ ቡድን ጠብ ጫሪነት በአማራ ክልል የተፈናቀሉትን ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ ከሎንዶን ኢምባሲ ጋር በመተባበር የእሳት ሚዲያ ሪፖርትር ፣ የኢትዮጵያ ጉምቱ ባለሃብቶች ማለትም አቶ ወርቁ አይተነውና አቶ በላይነህ ክንዴ በሎንዶን ዮናይትድ ኪንግደም በተገኙበት ተካሂዶ ነበር። በእለቱም ከ48 ,000/አርባ ስምንት ሺህ ፓውንድ/ በላይ ጥሬ ገንዘብ ፣ ጉዳት በደረሰበት አካባቢ ትምህርት ቤት ለማሰራት ወዘተ ባለፀጋዎች ቃል ገብተው ፣ እኛም በወቅቱ መስሎን ተፍ ተፍ ብለን ነበር።

ገንዘቡ ለታቀደው ጉዳይ ይዋል ፣ አይዋል ፣ ሃብታሞቹ ቃል የገቡትን ገንዘብና መሰል ችሮታቸውን መስጠታቸው አለመስጠታቸውን ብንጠይቅም የተሰጠው የማይረባ ምላሽ ነው። ለዚህ ጥያቄ መልስ እንጠብቃለን።

ከማንከትከት አልፎ የሚያስቀው ግን ከነዚህ አዘጋጆች መካከል ጥቂቶቹ  ከኢምባሲ ጋር በመተባበር “በሕግ ማስከበሩ ወቅት ወላጃቸውን ላጡ ሕፃናት በአማራና በአፋር ክልል የማሳደጊያ የበጎ አድራጎት ተቋም ግንባታ” በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ በቅርቡ ሊያዘጋጁ ተፍ ተፍ እያሉ ነው ።

ጉድ በል ጎንደር “ዐይንን በጨው አጥቦ” ዘረፋ ይሉሃል ይሄ ነው። አንዱን ሳያወራርዱ ወይም ከዚህ በፊት ባከናወኑት የገቢ ማሰባሰቢያ ወቅት የተዋጣውን ወይም ቃል የተገባውን ገንዘብ ዕልባት ሳያገኝና ሳያወራርዱ ሌላ ፍሬ ፈርስኪ ። ዘይገርም ነው። የሚገርመው ይህን ሰናይ የሆነ የተግባር ዕቅድ  የነደፉት ማለትም “በሕግ ማስከበሩ ጉዳይ ወላጆቻቸውን ያጡትን ህፃናት ለመርዳት በጋራ የታቀደ ሲሆን በግለሰብ ስም ያውም ፣ ስም እየቀያየሩና በዚህ ሃገር እውቅና የሌለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ሰይሞ በድድብና መወራጨቱ ምን የሚሉት ዐይን አውጣነትና ስምን ከላይ ጉብ ለማድረግ መታተር ነው ። ኧረ ቅጥ አጣን ወገኖች።

l554

“ያልተነካ ግልግል ያውቃል” እንዲሉ የአማራና የአፋር ሕዝባችን በግፍ እየተገደለ ፣ ሕፃናት እየተደፈሩ፣ እየተፈናቀሉ ፣ በቤታቸው ጣራ ፣ በጆራቸውና በፊት ለፊታቸው የጥይት ሩምታ እየትርከፈከፈ ፣ የድሽቃ ዶፍና የታንክ እሩምታ በላያቸው እየወረደ በአማራና በአፋር ስም መነገዳችሁ  አልበቃ ብሎ በውጭ ሃገር ንዋሪ የሆኑትን ሃዘን ላይ የተቀመጡ  ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአማራ ልጆችን ሃገር ቤት ላለው አንዳንድ ተረኛ ነፍሰ በላወች እየጠቆማችሁ የሚወዷትን አገራቸውን እንዳይረግጡ ከዛም አልፎ ግፍ እንዲሰራባቸው እየታተራችሁ ፣ ሽንጣቸሁን ገትራችሁ እየተውተረተራችሁ መሆኑን ከውስጥ አዋቂ  መረጃው ደርሶናል።

ከዚያው ልማደኞቹ በወያኔ አገዛዝ በኢምባሲ ተወዝፈው እነግንቦቴዎችን ወንጅለው ስም ያስተላለፉ የነበሩ ፣ በሌሉበት ሞት ያስፈረድባቸው ፣ ሲያሳድዳቸውና ቂጣቸውን በቆመጥ ይገርፏቸው የነበሩት አማራ መሰል ጉማሬዎች ታማኞቻችሁ የእንግሊዝ  ጊነስ ቢራ አቅመሰን ሲጃጁ ጉዳችሁን  ሹክ ብለውናል ።

እኛ በውጭ ሃገር የተበተን የአማራ ልጆች በግፍ ተጎሳቁለን ፣ የመከራ ገፈት ተግተን ፣ የግፍ እስር ፣ እንግልትና ጠብመንጃ ተደቅኖብን ፣ ከጥይት ዕራትነት ተርፈንና የትግል ጓደኞቻችን በመስዋት አጠተንና አምላክ ትረፉ ሲለን ለጊዜው የመቆያ ታዛ አግኝተን በባዕድ ሃገር ኖርን እንጂ ልባችንም ሆነ ነፍሳችን እምየ ኢትዮጵያ ነው ያለው።

ሃገርና ወገን ጥሪ ካቀረበልን እንደ እናንተ ማቃጠርና የፊዲስትነት ሰራ መስራት እርማችን ነው ። ነገር ግን “ ፋኖ የፋኖ ልጅ ፣ የበርሃው ዳኛ ፣  ጠላትን ጎመደው ትንፋሽ  ሳያሰማ” እንዲሉ  ጥይት ፣ ዝናር  ታጥቀንና መሳሪያ አንግበን መፋለሙንና መዝለቁን እናውቅበታለን ፣ “ልንገርሽ እሺ ፣ አማራ “የሺ” ሰው ግምት ነው ፣ “ዘለዓለሙን” ፈርቶ አያውቅም ፣ ፍርሃት እርሙ ነው” ።

በትግል ተፈትነን የመጣን እንጂ ሃገራችን ክደን እንደ እናንተ ማንነታችን ቀይረን የሱማሌ ፣ የሱዳንና ከወዳጅ ሃገራችን ጋር አታነካኩን የሌላ ሃገር ዜግነት ይዘን እራሳችን እንደ እንቁራሪት ቀብረን፣ ማንነታችን ደብቀን በሰው ሃገር ተሳቀን የምኖር አይደለንም ። ዘራፊዎች ፣ አለቅላቂዎች ፣ ነፍሰ በላወችና እግዚአብሔር በፈጠረው ነፍስ ፈራጆችና አስገዳዮች  አይደለንም።

እንዲህ በማቃጠር ፣ በመጠቆም ፣ በመዝረፍ ፣ እርስ በእርስ ወገንን በማናቆርና በማመስ የተካናችሁ እናንተ የአባቶቻችሁ ልጆች ናችሁ ፣ በደንብ እንተዋወቃለን። አንዳንድ ከዚህ በፊት አማራ ነን ሲሉ የነበሩ በአማራ ደም የነገዱና በዕድሜ የገፉ ኢምባሲ ውስጥ ከከተተው የኦነግና የኦነግ ሸኔ ጋር ሲቀላቀሉ ትንሽ አቀመሷቸው መሰል ብሄራቸውን ሳይቀር ቀየሩ “በባሌ ኦሮሞ ፣ የልጀ ባል፣/ሚስት/ ኦሮሞ ነች “ እያሉ ከባለጊዜዎች ረድፍ ለመሰለፍ እነሱነታቸውን ቀይረዋል። “እበስኩ ገበርኩ” ይላል የሃገሬ ሰው።

ዘርፋችሁትም ሆነ በግፍ ባገኛችሀት ገንዘብ የባንክ ብድር /ሞርጌጅ/ ወስዳችሁ፣ በልጆቻችሁ ስም ሳይቀር ቤት እየገዛችሁ ፣ ቤት ፣ ከቤት እያገላበጣችሁ እምታጭበረብሩ(fraudster)  ናችሁ።

 

የሃገሬ ሰው “በላ ልበልሃ” ይላል ። ፍርድ ፊት ቀርቦ መከራከር ሲሳናችሁ ፣ የሃሳብ ፣ የዕውቀት ፣ የመርህ ፣ አብሮ የመኖር ትብእል   የምክንያታዊነት ፣ የክርክር ፣ የኢትዮጵያዊነት ዘየና ቀኖና ድሃዎች ፣ አልቦዎችና መረኖች በመሆናችሁ ይህን ፈር የለቀቀ ፣ ከኢትዮጵያ ባህሪያት የራቀ ተግባራት  ብትፈፅሙ አንደነቅም።

አንድ የምንነግራችሁና የምንመክራችሁ ነገር ቢኖር እንኳን ሰው ሰራሹ መንግስት ፣ እግዚአብሄር በአምሳሉ የፈጠረው ሰው አላፊ ነው። ለሚያልፈው ዓለም ፣  ይሄ ክፉ ዓለም የፈጠራችሁ ግሳግሶች ሁሉም አላፊ ፣ እናንተም ሟች መሆናችሁን አውቃችሁ መልካም ስራ ስሩ፣ አትቅጠፉ፣ የባልጀራችሁን አትመኙ፣ አትስረቁ ወዘተ እንላችኋለን።

ያዋጣናል የምትሉትን ሁሉ ማድረግ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ነገ እውነት ፣ እውሸትን አሸንፋ ስትወጣ፣ ቋሚ ነገር የለምና ነገሮች ሲለዋወጡ መግቢያ ይጠፋባችኋል።

ያለፉት ገዳይ ፣ አሰገዳይ፣ ጠቋሚ አስጠቋሚ፣ ነፍሰ በላዎች ፣ የቀይ ሽብር ተዋናኝ ዘመዶቻችሁ ልጆች ስለ ሆናችሁ “ዘር ከልጓም ይስባልና” ከእናንተ እንደዚህ ያለ ወራዳ ስራ እንጅ ሌላ መጠበቁ ለአሳር ነው።

ማነህ ሆይ ትላንት ለሕውሃት ሲያደሸድሽ የነበረው ሁሉ ዛሬ ጉሽጉሻና ጉራጉር ውስጥ ገብቷል ፣ እናንተ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ ቅምጫና ፣ ጫት ስር ፣ እንስራ ውስጥና ጉረና ውስጥ ትወሸቃላችሁ።

 

ሁሉንም አምላክ ያሳየን!!

ኢትዮጵያ ከልብ የሚወዳትን ታውቃለችና ፣ በአምላክ ተራዳይነት እውነተኛ ልጆቿን ትጠብቃለች።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop