“there is no avoiding war,it can only be postponed to the advantage of your enemy . ” Niccolo machiaveli
” ጦርነትን ማስቀረት ባይቻልም ማራዘም ይቻላል ። እያጠቃህ ፣ ጦርነትን ካቆምክ ፤ አትራፊው ፣ ጠላትህ እንደሚሆን ፣ ከወዲሁ ተገንዘብ ። “በምንም ዓይነት መንገድ ጦርነትን በድል መደምደም አለብህ ። ጦርነትን ማስተላለፍ የሚጠቅመው ለጠላትህ ብቻ ነውና !
ሠላምን በጦርነት ድል ነስተህ ፤ አልያም በድርድር ታገኛለህ ። ሠላምን ለማይሻ ጠላትህ ግን ለሰከንድ እንኳን ጊዜ አፎይታ አትስጠው ። ጊዜ ከሰጠኸው ጠላትህ ተጠቃሚ አንተ ተጎጂ መሆናችሁ አይቀርም ። ለዚኽም ነው ፤ ተዋቂው የባህል ከያኒ ባህሩ ቀኚ፤ ………….
“ከእንግዲህ አይሆንም ነገር ማለሣለሥ
እነሱም አያርፉም እኔም አልመለሥ ። “ ብሎ የተቀኘው ፡፡
፩ ለሠላም ረጅም ርቀት የምትጓዘው ጭላንጭል የሠላም ሃሳብ ያለው ጠላት ሲያጋጥምህ ብቻ ነው ።
የሰው ቁጥርህ ከጠላትህ የሰው ቁጥር እየበለጠ ፤ የነፍስ ወከፍ መሣሪያህ ከጠላትህ አሥር እጅ ሆኖ ፤ የዘመነ የምድር እና የአየር ኃይል እያለህ ፤ ወዘተ ። ለምን ሚጢጢው ጠላትህ ዳግም ጡንቻውን አፈርጥሞ እንዲወጋህ ጊዜ ትሰጠዋለህ ? ሌላ የጥፋት ዕድል ለምን ትለግሰዋለህ ?
ከላይ በርዕሱ ሥር የተጠቀሰው የኒኮሎ ማኪቬሌ ብዙ እውነታዎችን ያዘለ ገመዜ የማይሽረውን ሃሳብ አለሸተመለከትክምን ? ጦርነትን እንዳይፈጠር ባይቻልም ፤ ማሥቀረት ባይቻልም ፣ ማራዘም ግን ይቻላል ። ይሁን እንጂ ጥቅሙ ” ለሚጢጢው ጠላትህ ብቻ ነው ። “ ነው ፤ እኮ የሚልህ ። ታላቁ የፖለቲካ ሊሂቅ ኒኮላማኬቬሌ ።
ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ፣ ተወዳዳሪ የሌለው የመከላከያ ሠራዊት እንደገነባች እና ጦሯም በማርሻል ደረጃ እንደሚመራ አወጀህ ስታበቃ ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ውሥጥ እጅግ የታወቀ እና የሚፈራ የመከላከያ ሠራዊት አገር እንዳላት እርግጥ ሆኖ ፣ አገርህን በየአቅጣጫው በሤራ እና በገንዘቡ ኃይል ተጠቅሞ ሌት ና ቀን እያቆሰለ በድህነት እንድትማቅቅ ያደረጋትን አንድ ሚጢጢ የውሥጥ መዥገር ፤ በጀግናው መከላከያ ሠራዊት ደፍጥጠህ መገላገል እንዴት መቻል አቃተህ ?
እንዴት ይህንን የማፍያ ቡድን አንገቱን ይዘህ ለፍርድ በማቅረብ የትግራይ ህዝብን ጨምሮ መላው ጦቢያን ማሠሰደሰት አቃተህ ? ተመሥገን ብለሸ ፣ ያለሥጋት ይኽቺን አጭር ህይወቱን አጣፍጦ እንዲኖር ማሥቻል እንዴት ተሳነህ ? እርቅን ፈፅሞ ለመቀበል የማይፈልገውን ጥቂት የአውሬ ህሊና ያለውን መዥገር ቡድን ፣ በእርቅ ወደ ሰውኛ አሥተሣሠብ ይመለሳል በማለት ተሥፋ አድርገህ ነውን ? ለተከታታይ 2 ዓመታት ሥለ ሰላም ሥትል የኢትዮጵያ ህዝብ ማስዋት እንዲከፍል አላደረክምን ? ለዚች ወድ ፣ ውብ እና እንቁ እናት አገሩ ብሎ ከአንድም ሦሥት ጊዜ ፣ ይኽ ወጣት ትውልድ ህይወቱን አልገበረመሰ እንዴ ? መሰዋትነቱስ እንደ ቀላልል የሚታይ ነው እንዴ ?
ጠላትህ አሥሬ እያንሰራራ አገርህን ሲያጠፋ ፣ እየተመለከትክስ እንዴት ለዚህ መሠሪና መዥገር ጠላትህ ለአሰቃቂው የአራተኛ ጊዜ የጭካኔ ተግባሩ እንዲሰናዳ ጊዜ ትሰጠዋለህ ?
ወያኔ እኮ አንድበአገራችን የሚገኝ የኢትዮጵያም ሆነ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ። ጠላትነቱንም ትግራይን ዪለህዝቡ ይሁንታ ፤ ያለ ግልፅ ፣ ነፃ ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፤ በጠመንጃ ዘላለሜን ልግዛ ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትም ውሥጥ ቁልፍ ቦታ ይሰጠኝ ባይ ነው ።
ይህ መዥገር እና እሥሥት ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ እድገትና ብልፅግና የማይፈልግ ፀረ ልማት ሆኖ ሣለ ፤ በለመደው ውሸት ሥለ ሠላም በቀባጠረ ቁጥር ፣ ለምን አገርን ለመጉዳት የሚያሥችል ኃይል እሥከሚገነባ ድረስ የእፎይታ ጊዜ ይሰጠዋል ። አገርህን ለሦሥተኛ ጊዜ እያደማት ያለው ፣ ንፁሐንን በግፍ እየገደለ እና መሠረተ ልማቶችን እና የህዝብ መገልገያዎችን እያወደመ ያለው እኮ ትላንት መዥገሩ ትህነግ ተጨፍልቆ ግብዓተ መሬቱ ባለመፈፀሙ ነው ።
ይህ እንደ እባብ አፈር ልሶ የተነሳው ጥቂት ቡድን ትላንት ” ንፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ነው ። ” ያልከው ነው ። ይኽ ቡድን ትላንት ሸዋ ሮቢት ደርሶ ፣ የሸዋ ልጆች ህይወታቸውን ገብረው በመሰዋትነት ድል ያደረጉት ቡድን ነው ። ይኽ ቡድንን ወደ መቀሌ ያባረሩት ለአገራቸው ለመሞት የወሰኑ ፣ የመከላከያ ሠራዊቶች ፣ የአማራ ፋኖዎች ፣ ከመላው ኢትዮጵያ በክተት ጥሪው ጦርነቱን የተቀላቀሉ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አሰንደሆኑ አትዘንጋ !
ከነዚህ ውድ ኢትዮጵያውያን መሰዋትነት በኋላ ግን ጦርነቱ ሳይቋጭ ፣ ጦርነቱ ይቁም ተባለ ። ከአሸባሪው ወያኔ / ትህነግ ጥቂት ቡድን ጋር መንግሥት እደራደራለሁ አለ ። ” ለትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥቅም ሥል ። ምክንያቱም ጦርነት ያቀጭጨናል እንጂ አያሳድገንምና ! ”
እውነት ነው ። የመንግሥት ሃሳብን ንፁህ ህሊና ያለው አይቃወመውም ። ግን ፣ ግን ወያኔ /ትህነግ ለሠላም ዝግጁነት እንደሌለው እየታወቀ ፣ ለሠላም አላሥፈላጊ እርቀት መጎዝ አሥፈላጊነቱ አይታየኝም ።
፪ . ” ሠላምን በጠረጴዛ ዙሪያ ለማግኘት የማይፈልግ በጦር ሜዳ እንዲያገኛት ይገደዳል ። ”
ወያኔ ለሠላም ደንታ እንደሌለው ያሥመሰከረው እኮ ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ነው ። በዛን ቀን የትግራይ ህዝብን እና ኢትዮጵያን ከጠላት የሚጠብቀውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ፣ በትግራይ ልዩ ኃይልና በሚሊሻው እንዲሁም ሆድ እንጂ ማሰቢያ አእምሮ በሌላቸው በሠራዊቱ ባልደረቦች ( ቋንቋና ዘርን በሚያመልኩ ) በተቀናጀ ሤራ ድንገት የጦር ከምፑ ተወሮ የተፈፀመበትን አረመኔያዊ ድርጊት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ለዘላለም አይረሳውም ።
ይሁን እንጂ ፣ ይኽንን ወራዳ ታሪክ ይቅር የማይለው በጭካኔ እና በግፍ የተሞላ ተግባር ፈፅመው ፣ መንግሥት በአሸባሪነት ፈርጇቸው ሲያበቃ ፤ ” ለአገሬ እና ለህዝብ ከበጀ ለይቅርታ እጄን እዘረጋለሁ ። ” በማለት ለሠላም ሲል ያልተገባ እርምጃ ቢወስድም ከሠላም ይልቀሰ በጦርነት የሚያተርፉ ኢምንት የወያኔ መሪዎች ፣መንግሥትን እንደ ጅል የኢትዮጵያን ህዝብ ደግሞ ፣ እንደፈሪ በመቁጠር ይኸው ለሁለተኛ ጊዜ በአማራ ክልል እና በአፋር ላይ ጦር መዘው እየወጉት ነው ።
የትግራይን ህዝብ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ምሽጋቸው ነው የሚቆጥሩት ። እናም ይህ አገርን የሚወጋ ሠራዊታቸው የእነሱ ምሽግ ነው ። በእርሱ ሞት እንጂ በእርሱ በሠላም መኖር የእነሱ ነፍስ ቀጣይነት አይኖራትም ። ይኽንን አሣምረው ሥለሚያውቁ ጠቅላላ የትግራይ ወጣት ለእነሱ ህይወት መቀጠል አላስፈላጋ መሰዋትነት ቢከፍል ቅንጣት ያህል ሐዘኔታ አይሰማቸውም ።
ወዳጆቼ ሆይ እነዚህ ኢምንት ሰው ያልሆኑ ሰዎች እኮ በትግራይ ኃይማኖት እንዲጠፋና ጥቂት የማይባል ቄስ ካድሬ እንዲሆን ያደረገ ፀረ ኃይማኖቶች ናቸው ። የእግዚአብሔር መሪነት ተወግዶ የነደብረፅዮን መሪነት በየቤተክርስቲያኑ ነግሷል ። በንፁህ ልብ አምልኮ ቀርቷል ። በአጭሩ ወያኔ በሚያሳዝን መልኩ የትግሬ እግዛብሔርን ፈጥራለች ። ወዳጄ ፈጣሪያችን እግዛብሔር አንድ ነው ። ፈጣሪ በፍጡሩ የማይመዘን ችሎታ እንዳለው ተረዳ ። መድሃኒዓለም በሸክላው ፍጡሩ ሊመዘን ፣ ሊገለፅና ማብራሪያ ሊሰጥበት አይችልም ። እና የፈጣሪ አገልጋይ የሆኑት ቄሶች ፣ በሰማይ ዙፋኑ በምድር መረገጫው ኃያል ዓምላከሰ እንመራለን የሚሉት ቄሶች ለምን የወያኔን ጠመንጃ ፈርተው የወያኔ አገልጋይ በመሆን በፀረ _ ሰው ድርጊት ሥጋውያን ሆነው ተሠለፉ ? ? ” መጀመሪያ ሰማይና ምድርን የፈጠረው እግዛብሔር ነው ። ምድርም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም ። ” የዘፍጥረት ጅማሬው ይኽ ነው ። ኦሪት ዘፍጥረትን አንብብ ።
እናም እነዚህ መዥገሮች ሰውን በጭካኔ ቆራርጠው ለመግደል ምን ያህል ርቀት ለሠጓዝ እንደሚችሉ ፣ ከእምነተ ቢሥነታቸው ተረዳ ። ለነዚህ ፀረ_ እምነቶች ርህራሄ ፈፅሞ ማሳየት የዋህነት ነው ። እነሱ ቢያገኙህ አይንህ እያየ ሰውነትህን በቁሙ እየቆራረጡ ለአውሬ የሚሰጡ ጨካኞች ናቸው ። ይኽንን ድርጊት እኮ ከትግራይ እናት መሐፀን በወጡ በብዙ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ያውም በትግራይ ልጆች ላይ ያለርህራሄ ፈፅመውታል ። ለነሱ የሰው አካልን እንደ እንስሳ መበለት እና የሰው አንገት መቅላት ብርቅ አይደለም ።
ከነዚህ በሰው አምሳል ከተፈጠሩ የሰው ጭራቆች ጋራ መደራደር ከቶም አያሥፈልግም ።እነዚህን ሰው በላ ጠሸቂት የወያኔ አመራሮች በመከላከያ ሠራዊታችን የሚመራው የኢትዮጵያ ጥምር ጀግና የጦር ሠራዊት ተገቢውን ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል ። በነሱ መቃብር ላይ ፣ የተግራይ ክልል ነዋሪ የራሱን መሪ በነፃ ምርጫ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት መርጦ ወደ ትክክለኛ ፍትህ ፣ ዴሞክራሲ ፣ እኩልነት ፣ ሠላምና ዕድገትና ብልፅግና መሸጋገር ይገባዋል ። ከእንግዲህ ወደፊት እንጂ ወደኋላ የለም ። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከጠላቶቿ ጋር ለተማማሉ መሠሪ የወያኔ አውራዎች ጋዜ መሥጠት ለዳግም ወረራና ውድመት እንዲዘጋጁ ከማድረግ በሥተቀር ለትግራይ ክልልም ሆነ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም የለውም ።