መላዉ ኢትዮጵያ ከግፍ እስር እና ፍትህ ዕጦት ነፃ አስኪሆን መሰራት አለበት

መስከረም ፭ ቀን ሁለት ሽ አስራ አምስት ፲፬ የሚሆኑ የዓማራ ህዝባዊ ኃይል አደራጂ እባላት ከወራት አልቦ ምክነያት አስር እና አንግልት በኋላ በነፃ መሸናበታቸዉን እና ከዕስር መዉጣታቸዉ ሰምተናል፡፡

ይህ እጂግ ደስ የሚል እና እንኳን ለዚህ አበቃእሁ የሚያስብል የመላዉ ኢትዮጵያዉያን ፍላጎት እና ምኞት ነበር ፤ሆኗል፡፡ እነኝህ ሠዎች ወደድንም ጠላንም የህዝብ እና የአገር ህመም እና ስቃይ አሳስቧቸዉ እንጂ ላማ እና ጫማ ሆነዉ በማጎብደድ እና በአጉል መወደድ መኖር አጥተዉ ወይም ጠፍቶባቸዉ አለመሆኑን ማንም ያዉቃል፡፡ ፋኖም ሆነ የፋኖ መሰረት ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑ ታሪክ ቀርቶ ተፈጥሮ የሚናገረዉ የአደባባይ ሀቅ ሆኖ የፋኖን ታሪክ እና ስራ ማጣጣል ለግል እና ለቡድን ጥቅም ካልሆነ ለህዝብ እና ለአገር ክህደት ይሆናል፡፡

በይትኛዉም ጊዜ ፣ቦታ እና ስርዓት ጥፋተኛ ይኖራል ነገር ግን ጥፋት በጥፋት ሳይሆን በማስተዋል እና በስርዓት መስተካከል አለበት ፡፡ የፋኖ አደረጃጀት እና ህብረት የኢትዮጵያ አንድነት እና ገናናነት የጀርባ አጥንት ሆኖ ሳለ በሆነ ባልሆነ ትኩር ጥምድ ህዝብ እና ስርዓቱን ማራራቅ ነዉ ፡፡ ምክነያት ለሚል ፋኖ ኢትዮጵያዊ ነዉ ፤ ኢትዮጵያዊነትም ዓማራነትን የሚያቅፍ እና የሚደግፍ ሆኖ ከሠፊዉ የዓማራ ህዝብ የሚጠለቀዉን የብዙ ሽ ዘመናት የኢትዮጵያ አንድነት እና ኩራት መለያ /ዓርማ በመሆን የነፃነት እና የእምቢባይ ምልክት ፋኖ እንደ ደራሽ ጎርፍ መቁጠር ኢትዮጵያዊነት ያልሆነ ማንነት ነዉ ፡፡ ይህ ደግሞ ለዓመታት የነበረዉን ጭቆና ግፍ የሚያራዝም እና የኢትዮጵያዉያንን ዕስራት እና ዕንግልት የሚስቀጥል አፋኝ ምኞት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ፣ ህዝቧ እና መንግስት ሳይቀር ከዘመናዊ አስር እና ባርነት ከሁለት አስርተ ዓመታት በኋላ ከሶስት ዓመታት በፊት ነፃ የወጡት በማንም ምኞት እና ፍላጎት ሳይሆን በኢትዮጵያዉን እና በኢትዮጵያዉን ቁርጥ ቀን ልጆች መሆኑን መዘንጋት የሚቻል አይመስልም ፡፡ ይህም የዓማራ ህዝብ ትግል እና የወታቱ ተሳትፎ መሆኑን ሲታወስ ፋኖ ማለት የአባቶቹን ጋሻ ያነሳበት ጊዜ ሲሆን ለዚህም አስካሁን የሚታየዉ ተገቢ ያልሆነ ፍርኃት እና ማዋከብ የጫማራ ህዝብ ለአገሩ እና ለክብሩ ለዘመናት የሚከተለዉን ቀናኢ አቋም ለማስቀጠል ዛሬም በትግል ሀዲድ መሆኑን የሚረዱ ጠላቶች ስጋታቸዉ ማየሉን ያሳያል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከቁጫ እስከ ኦሮሞ – ማንነትና የማንነት ፖሎቲካ እንደምታና መዘዞቹ

ለአገሩ እና ለህዘቡ ብሎም ለራሱ በጎ የሚያስብ ማንም ለብዙኃን ህዝብ እና ለዓማራ ህዝባዊ ኃይል ድጋፍ እንጂ ማነቀፍ እንደማይኖርበት ዕሙን በመሆኑ አሁን ከዕስር የተለቀቁት የብዙኃን ከዕስር የመዉጣት ፋና ወጊ መሆናቸዉን አመላከች በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አብሮ ያደገ በሽታ ካልገደለ አይለቅም!!

“ለፍትህ እና ዕኩልነት ማሳየዉ ምህረት እንጂ ጥላቻ እና ፍርኃት አይደለም፡፡”
አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡
NEILLOSS-Amber

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share