ኢትዮጵያ ሁሉን ከዉጭ የምጠብቀዉ አስከ ምን ይሆን ?

የኢትዮጵያ ጠላቶች ዛሬም እንደ ይንቱ ከዉስጥ እና ከዉጭ ለኢትዮጵያ አንድነት ፤ለህዝቦች ሉዓላዊነት  ስጋት  በመሆን የማይቀፍሩት ጉድጓድ ፤የማይምሱት አፈር ፣ያልተሸረበ ወጥመድ አልነበረም ፡፡

ይህም በመጀመሪ 1888 የወራሪዉ ኢጣሊ ዕብሪት  የቅኝ ግዛት ሙከራ ፣ ዳግም 1928 ዓ.ም. የ፵ ዓመታት የተስፋፊ ዝግጂት ወረራ፣ የዚያድባሪ (ሶማሊያ) ተስፋፊ ወረራ በነበረበት እንዲቀለበስ እና ጠላት በቆመበት አፈር እንዲለብስ የሆነዉ በየትኛዉም የዉጭ ሽምግልና አልነበረም ፡፡

ዓለም የሰዉ ልጆችን ሠባዊ ክብር እና የጥንታዊት ኢትዮጵያን ሉዓላዊ የአገር ግዛትን የማስጠበቅ ፍላጎት ቢኖር ኖሮ ኢትዮጵያም ሆኑ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የደረሰባቸዉን የዘር አድሎ እና የቅኝ ጋዛት ቀንበር ግፍ ከማስተናገዳቸዉ አስቀድሞ ወረራዉን ማስቆም ወይም ማገድ በተቻለ ነበር ፡፡

ያዚያን ጊዜ ኢፍትኃዊ፣ ኢሰባዊ እና ራስ ወዳድነት ከዚያ ጀምሮ አስካን በተለያየ ሁኔታ በተለያየ ደካማ መንግስታት ባሉበት ሁሉ ያለዉ ዘመናዊ ባርነት እና ቅኝ ገዥነት አስተሳሰብ ከነተግባሩ ይስተዋላል ፡፡

ኢትዮጵያ በመላዉ ዓለም በቅኝ ግዛት እና ባርነት በተስፋፋበት የጨለማ ዘመን በዓለማችን ነፃነታቸዉን እና ብሄራዊ ጥቅማቸዉን ካስጠበቁ ቁጥራቸዉ በጣት ከሚቆጠሩ አገሮች አንዷ መሆኗን  በህይወት ያለ ቀርቶ በሞት የተለየ ጠላቷ ምስክሮች ስለመሆናቸዉ የአደዋ ተራሮች ፤ የኢትዮጵያ ወንዞች እና ሸለቆዎች ፤የካራ ማራ ተራሮች ….ሳይቀር ከነሳር ቅጠል ዋቢ ናቸዉ ፡፡

እንግዲህ ኢትዮጵያ የራሷን ጉዳይ  በራሷ የመወጣት  ብቃት በዚህ የሚገለፅ ሆኖ ሳለ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ የዉጭ ጣልቃ ገብ ሽምግልና  ምን ዉጤት እንዳመጣ የትናትም የዛሬም መዘዝ ሆኖ ይገኛል ፡፡

በዓለም ህብረት(ሊግ ኦፍ ኔሽን) ስለ ኢጣሊያ ወረራ፣ ስለ ኢትዮ-ኤርትራ……በዉጭ  ፍረደ ገምድል የወዳጂ ጠላት የሖነዉን እና እየሆነ ያለዉን እንዴት መርሳት ቢቻል ነዉ ዛሬ የኢትዮጵያ ጉዳይ ከኢትዮጵያን ዉጭ መፍትሄ ፍለጋ ጊዜ ማጥፋት እና የማይሆን /የማያዛልቅ ዕርቅ አይሉት መዘባረቅ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሙሥና የብልፅግና ፀር ነውና “ይበቃል ! “ ልንለው ይገባናል   (አባ መላ ዘ አብደናጎ)

እንዴት ኢትዮጵያ ከራሷአልፋ ለመላ የሰዉ ልጂ ነጻነት ፣ሠላም እና ሉዓላዊነት በሽምግልናም ሆነ በወታደራዊ ኃይል ለኮንጎ፣ ለኮሪያ፣ለላይቤሪያ….የሆነች አገር የራሷን የዉስጥ ችግር በራሷ ለመፍታት የሚገዳት ፡፡

ኢትዮጵያ የባህላዊ እና ዘመናዊ ጥበብ ፣ አስተሳሰብ ፣ ባህል  እና ታሪክ ያላት ሆና ጭግሩም ፤ የችግሩ ምንጭም ሆነ መፍቻዉ በራሷ ልጆች እጂ ሆኖ የትኛዉን የኢትዮጵያ ችግር መቸ እና በማን የተፈታዉን ነዉ አፍሪካም ሆነ ዓለም እንዲፈታ የሚጠበቀዉ ፡፡

ኢትዮጵያ ከጥንት አስከ ዛሬ ለዕዉነት እና ለሰዉ ልጆች ነፃነት የሚያስቡ እና በዚህም የተካኑ የህይወት ልምድ ያላቸዉ ጠፍቶ ነዉ ወደ ዉጭ ዞትር የምናማትረዉ ፡፡

ዕርቅ ሆነ መስማማት  ዕዉን የሚሆነዉ እናሚዘልቀዉ ለደረሰዉ ጥፋት እና ዉድመት ሁሉ ባለቤት ኖሮ ለዚህ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት በዉል ሲረጋገጥ ነዉ ፡፡ ይህ ባልሆነበት የይስሙላ ይቅርታ እና ዋይ ዋይታ ታጥቦ ጭቃ ነዉ ፡፡

ከኢትዮጵያዉያን የበለጠ ለአገራቸዉ እና ለህልዉናቸዉ ለይኩን መፈለግ ልጂ ለናቷ…..አስተማረች እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል ፡፡

“ሲታጠቡ ከክንድ …..ሲታረቁ ከልብ፤ ያገሩን ሠርዶ   ባገሩ በሬ ….”  ያለ ከኢትዮጵያዊ ዉጭ ማን ነበር ? ፡፡ ለባዊ ዕርቅም  የሚሆነዉ የተጣላ ወገን ከተቀመጠበት ተነስቶ ፣ ከተሰቀለበት ወርዶ ሲዳኝ  ፣የተበደለ ሊካስ ፤ የበደለ ሊክስ (ሊከሰስ እና ሊወቀስ    ) ሲችል ብቻ ነዉ ፡፡

አብን እንደተቋም የህዝብ እንጂ የተወሰኑ አመራሮች  ምሽግ እንዳልሆነም በዚህ አጋጣሚ አሁን ላይ ስለ ዕርቅወይም ድርድር የሰጠዉን መግለጫ እና ተያያዝ ጉዳዮች ስንዳስስ ቀድሞ ህዝብ የሚጠይቀዉን እና ቃል የገባዉን የፖለቲካ ትግል ሁሉ የዘነጋ አስኪመስል ብይታ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ይስተጋባሉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፋኖ እስረኛ አያያዝና አወዛጋቢ ውሳኔዎች፤ከተሞችን በመስዋዕት ይዞ በማግስቱ በነጻ መልቀቅ፤ ለምን???

ዕርቅ የአገርን እና የህዝብን ቁስል የሚያድን ፤ ትዉልድን የሚያንፅ እንጂ ከጊዜያዊ ትኩሳት እና ግርሻት ለመዉጣት መሆን የለበትም ፡፡

ለማስታረቅም መፈጠር እና መሆንን ይጠይቃል  ታላቁ መፅሀፍ እንደሚለዉ  “የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸዉ ክርስቶስ ይመስላሉ እና …..” ይህ ከሆነ ምንም ይሁን ምን ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን ከኢትዮጵያዉን ዉጭ  ለእኛ ህመም አስታማሚ እና አስማሚ  መሻት ለማስታረቅ ሳይሆን ዕዉነትን ማራቅ ስለሚሆን ለራስ ማወቅ እና ከራስ መታረቅ ነዉ ለእኛ የሚበጀዉ ፡፡ በአገራችን ዓሜን ማለት አቅቶን በባዕዳን ቋንቋ ማንነት አሳጥቶ ዉርደት እና ሞትን የሚያስከትል ዕርግማን ይሁን ማለት በአዲስ ዘመን በዘመነ ድህነት(ሉቃስ) ልነፈወስ ይገባል ፡፡

“ስለ እኛ ከዕኛ ሌላ አማራጭ እንደ ባህር ድንጋይ መሙለጭለጭ ነዉ   ፡፡”

“የወዳጂ ጠላት ሲያስማማ እንዳትስማማ ብቻ ሳይሆን እንዳትሰማማ ነዉ  ፡፡ ”

NEILLOSS- Amber

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share