ዕርቅ እና ድርድር አገር እና ህዝብ ወይስ ስልጣን ስልጣን መታደግ ?    

ከጥንት አስከ ትናንት  ሲመች ጦርነት ፤ሳይሆን ድርድር ፤ዕርቅ እየተባለ ዕድሜ ልክ ኢትዮጵያ እና ህዝቦች ቤተ ሙከራ ሆነዋል ፡፡

ኢትዮጵያ መንግስት አልባ ከሆነችበት ግንቦት ፲፪ ቀን አንድ ሽ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት  መሪዋ ኮ/ል መንግሰቱ ኃ/ማርያም የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ወደ ተጓዙበት ከመነሳታቸዉ በፊት ደጋግመዉ ብዙ ብለዋል ፡፡

የዛሬዎች ነፃ አዉጭዎች  ፀረ ኢትዮጵያ ቅጥረኛ ፤ ከኃዲዎች እና የናት ጡት ነካሾች  ኢትዮጵያ ጥንታዊ ገናነቷን ክደዉ ፤ ክብሯን አሳንሰዉ ፤ ዳር ድንበር በማስደፈር ፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ በማድረግ ፤ ኢትዮጵያዉያንን በጠላትነት በመፈረጂ አጥፍቶ ጠፊዎች መሆናቸዉን ነብዩ እና ርቆ አሳቢዉ እና ነብዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጂ መሪ ያኔ ተናገረዋል ፡፡

ያኔ በነጻ አወዉጭነት ህዝቡን ለሽብር አጋልጠዉ አግሬ አዉጭኝ ጥግ ያየዙት በታሪክ እና ጊዜ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ህዝብ በከፈለዉ መራራ ትግል የጊዜዉ የዚትዮጵያ መንግስት ሲገረሰስ የነፃነት ትግል መታወቂያቸዉን ደብቀዉ ማዕከላዊ ስልጣን ኮርቻ በመዉጣት የስልጣን ዕርካብ ሲይዙ ዛሬ ላይ ዕርካቡ በህዝባዊ ዕምቢተኝነት ሲክዳቸዉ ዳግም ነፃ አዉጭ ሆነዉ አገሪቷን በግዞት ፤ ህዝቡን በባርነት ዳግም ለመያዝ በአንድ እጂ ሠላም በሌላ እጂ ከዕኛ በላይ የለም የለም በሚል ዕብሪት ያሻቸዉን ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡

ኢትዮጵያን ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ በጥላቻ ቀለም መስሎ ኢትዮጵያዊ  እና ህዝባዊ መሆን ባለመቻሉ የአገር መከላከያ የነበረዉን ፤ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የነበሯትን የዉጭ እና የዉስጥ ትስስር እና መዋቅር አፈራርሶ ኢትዮጵያ ማለት ቀልድ መሆኑ  ኢትዮጵያዊ ከዚያ አስከዚህ ሠዉነት እና መሪነት ያለዉ የህዝብ መሪ ለማግኘት ባለመታደል ሾተላይ ሆና ያለችዉ  ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዮናስ ብሩ ቡፋ፤ አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ

የቀደሙት ኢትዮጵያዊ መሪዎች ከምንም በፊት የግለሰብ እና የአገር ነፃነት የማይለያይ  የአንድ ሸማ አካል እንደሆነ በመረዳት ከዉጭ እና ከጠላት ይልቅ ለአገራቸዉ እና ህዝባቸዉ ቀናኢ ነበሩ ፡፡

ይህ ሲባል ያለፉት መሪዎቻችን የእነሱ ህልዉናም ሆነ ስልጣን ከአገር እና ከህዝብ ጥቀም እና ህልዉና በታች መሆኑን የእነርሱ ልጆች እና ቤተሰቦች የህዝብ እና ያአገር በመሆናቸዉ የኢትዮጵያዉ ልጆች ሁሉ የእነርሱ እንደሆነ በነግግር ሳይሆን በተግባር ኖረዉ አሳይተዋል ፡፡

የኢትዮጵያን ህዝብ በማክበራቸዉ እና አገራቸዉን በመዉደዳቸዉ ስርዓቱን እና የስርዓቱን ግድፈቶች እንጂ የኢትዮጵያዉያን  ፍሬ የሆነዉን ኮትኩቶ እና አርሞ ለፍሬ ከማድረስ ዉጭ አገልጋይ አድርጎ ለመቅረፅ ያደረጉት አንድም ህዝባዊ ተቋም አልበረም ፡፡

ዛሬ ላይ ላለፉት የግማሽ ክ/ዘመን የኢትዮጵያ መከራ እና ዉርደት ፤ የህዝቦች ስደት ፣ ሞት ፣ ድህነት እና በኢትዮጵያዊነት ማንነት ለደረሰባቸዉ እና እየደረሰባቸዉ ላለዉ በኢትዮጵያዊት ሳይሆን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን በጥላቻ እና ቂም በቀል በባርነት ግዞት በሁለነተናዊ የማንነት ፣ ኢኮኖሚ ፣ ፓለቲካ እና ማህበራዊ ቀዉስ ማስገባት ተጠያቂ ያልሆነ ፀረ ኅዝብ አስተሳሰብ እና ድርጊት ያላቸዉ የህዝብ እና የአገር ብሄራዊጠላቶች እያሉ ዕረቅ እና ድርድር ማለት ማን ከማን ጋር እንደሆነ እንኳን ግልፅነት  በማይታይበት የአገርን እና ህዝብን መከራ ማለባበስ የትዉልድ የደም እና ቂም ዕዳ ዘመን ማራዘም እና ለትዉልድ ማዉረስ ነዉ ፡፡

ከሰዉነት እና ኢትዮጵያዊነት ቅኝት ዉጭ ኢትዮጵያ ብሎ አገር ፣ ዓማራ ብሎ ህዝብ  በሚል የጥላቻ  ፖለቲካ ሴራ ሟች እና ተበዳይ ሳይካስ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ ከ 1960ዎች ጀምሮ የደረሱ በደሎች  ባለቤት እና ተጠያቂ ሳይኖር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያዉያንን ያገለለ ወይም የማያሳትፍ  ድርድር የቡድን እና የግል ጥቅም ለማስጠበቅ ካልሆነ ለአገር እና ህዝብ ብሎም ለመጪዉ ቂም እና ደም ከማሳደር ዉጭ የሚፈይደዉ የለም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጐንደር ክፍለ ሀገር ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!!

ለዚህ ሁለት ሁነኛ የቅርብ ጊዜ አብነት ብንወስድ  ህገ -ኢህአዴግ   እና ይዟቸዉ የመጣቸዉ ብሄራዊ  ዕንቅፋቶች  ዛሬ አገሪቷን እና ህዝቧን የደም ዕንባ ሳያቋርጥ የሚያጎርፋቸዉ ብዙኃኑን የኢትዮጵያ ህዝብ አግላይ እና የቡድን ጥቅም ማስጠበቂያ አገልጋይ ሆኖ  ወጥመድነቱ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለዜጎች ደህነት ሆኖ በፖለቲካ ስምምነት በመዋቀሩ ነዉ ፡፡

ሁለተኛዉ የባድመ ጉዳይ ወትሮም የፖለቲካ ጥቅም እንጂ የአገር እና የሕዝብ ችግር እንዳልነበረበት የሚያሳየዉ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ የሠዉ ኃይል ፣ የአካል ጉዳት እና ሞት ከተስናገደበት በኋላ በአልጀርስ እንበለዉ በየትኛዉም መለኪያ የኤርትራ መሆኑ በዓለም አደባባይ ተረጋግጧል፡፡

እኮ ያኔም ሆነ አሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላብ ፤ደም እና የህይወት መስዋዕት ዋጋ ከፖለቲካ ስልጣን እና ከቡድን ጥቅም በላይ የአገር እና ህዝብ ጉዳይ የሚረሳ ከሆነ ዕርቅ እና ስርድር  አገር እና ህዝብ ለማስከበር ወይስ የቡድን ጥቅም እና ክብር  ማስቀደም እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል፡፡

ኢትዮጵያዊነትም ሆነ ኢትዮጵያ ወደ ነበረ ክብራቸዉ የሚመለሱት የህዝብ እና አገር ጉዳት እና የዚህ ጉዳት አድረሾች ተጠያቂ ሲሆኑ እና ተጎጂዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ እና አፋር ህዝብ ለዓመታት የደረሰበት ዘርፈ ብዙ ሰቆቃ፣ ጥቃት ፣ ዉርደት ፣ ሞት ፣ዕንግልት እና ስደት  ካሳ እና ይቅርታ የሚያገኝበት በባለቤትነት የሚደራደርበት ሲሆን ብቻ ነዉ ፡፡

ገዳይ እና በዳይ በማይጠየቅበት እና በማይወቀስበት  ለየትኛዉም ወገን ተብሎ  የሚሆን ድርድር ይሁን ምክክር የትዉልድ ቂም እናደም ከማቆየት የሚዘል ፋይዳ አይኖረዉም ፡፡ ይህም  አበዉ “ሳል ይዞ ስርቆት ፤ ቂም ይዞ ፀሎት” እንዲሉ ኢትዮጵያዊነት የበደለ ሲክስ ፤ የተበደለ ሲካስ  ዕዉነተኛ ፍርድ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንደራሴ ስሚዝ እ ኬረን ባስ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው

“ጠላት በማስታመም ኢትዮጵያን ሆነ ህዝቧን መታደግም ሆነ ማከም አይቻልም ፡፡ ”

አንድነት ኃይል ነዉ

NEILLOS –Amber.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share