August 28, 2022
11 mins read

ፈንድ ፈንዳጅ ዲያስጶራ እባክህ ስማ! ለዘራፊዎች የማይነጥፍ ጥገት መሆንህ ይብቃ!

ቦንድ-ቦንዳጅና-ፈንድ-ፈንዳጅ

ዘራፊዎች መውረራቸውን፣ ፈንድ ፈንዳጅ ለዘራፊ ስንቅ ማቀበሉን፣ የእነተኔ ጦር ማፈግፈጉን፣ ባንዳ ፋኖን እንደ ክርስቶስ አሳልፎ መስጠቱን መቼ ነው የሚያቆመው?

tplf Lit leba

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

“ይህን ብዬ ነበር ለማለት ነው” የሚለውን የባንዳ፣ የውሽልሽል፣የጅል፣ የከርሳምና የአድርባይ ምፀት ያቁሙና ይኸንን ተዚህ በፊት በተደጋጋሚ የቀረብ ምክር ያዳምጡና በግብር ያውሉ፡፡ እባክዎ እየተንዘላዘሉ ለመዝረፈ ለተፈጠሩ ሌቦች የምይነጥፍ ጥገት መሆኑን አይቀጥሉ፡፡

እኛ የዛሬ ኢትዮጵያውያን ተሩቅ ታሪካችን ቀርቶ ተቅርብ ልምዳችን መማር ያለመቻላችን ዝግመት ሰፊ ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ ባንዳ ተደብቆ ወይም አቀርቅሮ ተሚውልበት ባህል ወጥተን የባንዳዎችና የከሃዲዎች አድናቂና ተከታዮች የመሆናችን መርገምት ልባዊ ፀሎት ያሻዋል፡፡

ለገሰ ዜናዊ በወቅቱ በነበረው ያረቦች አመፅ መክንያት በእስራኤሎችና በምዕራባውያን ትዕዛዝ እንደዚሁም ሲወለድ በተነቀረበት የአማራ ጥላቻ የአማራን ጥቅም ለመንጠቅ ዓባይን ተሱዳን ደጃፍ ሊገድብ “ሕዳሴና ቦንድ” እያለ ቃዠ፡፡ የለገሰ ቅዥት እንደ ዛር ተኮፍሷቸው የለገሰ ቦንድ እንዲሳካ ስንቶች “ምሁራን” ስንክሳር እሚያካክል ጥሑፍ ጣፉ፡፡ ስንቶች ሆዳም ካድሬዎች የቦንድ ስብሰባዎችን ለማዘጋጀት መቀመጫቸውን ተወዲያ ወዲህ አማቱ፡፡ ስንቶች በሕዝባቸው መቃብር እንጀራ እሚጋግሩ ዘፋኞች ልማት፣ ህዳሴና ታድሶ እያሉ ዘፈኑ፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም የሰይጣን ቁራጩን ለገሰን “ባህር አሻጋሪው ሙሴ” እያሉ በሌለ ባህር የአፋቸው ቀዳዳ ተጆሯቸው እንስተሚደርስ እየከፈቱ ዘፍነው ዛሬም በሰው ወግ ይኖራሉ፡፡ “ከሀዲዎችን እየተከተላችሁና ያለ ድብዳብ እየተሸከማችሁ ሕዝባችሁን አታስፈጁ” ቢባሉም አልሰማ አሉ፡፡ በእነዚህ ህሊና ቢስ ጉዶች ተላላኪነት የተሰበሰበው የቦንድ ገንዘብ ወገኖቻችውን እንደ ደን ከማስጨፍጨፍ በተጨማሪ ለገዳዮቹ መሳከሚያ፣ ለሰርግ መደገሻ፣ ለግል መርከብና ለአውሮጵላን መግዣ መዋሉ  ገሃድ ሆነ፡፡

ከቦንድ መቦንደድ ውድቀት ትምህርት መውሰድ ያቃታቸው ጉዶች ይህ አድግ ቁጥር አንድ በይህ አድግ ቁጥር ሁለት ሲተካ ለገሰ በአማራ ጨቋኝነትና በብሔር ብሔረሰቦች ተጨቋኝነት ግሳንግስ ልብወለድ ዘፍቆ፣ በካድሬነት አስደቁኖና በጆሮ ጠቢነት አስቀስሶ ሕዝብ ለመፍጀት ለሃያ አመታት እንደ እቃ ለተጠቀመባቸው ባንዳዎች ፈንድ ፈነደዱ፡፡ በፈነደዱት ፈንድም ሕዝብ የሊጥ ሌባ የሚላቸው ዘራፊዎች በማፈግፈግ ደቁኖ በማፈግፈግ የቀሰሰውን የእነተኔን ጦር እያባረሩ በተደጋጋሚ በዘረፉትና ባወደሙት አካባቢ “የአገልግሎት መስጫ ድርጅቶን እንገነባለን!” እያሉ ለዘራፊዎች ስንቅ ለማቀበል ደፋ ቀና ማለቱን ቀጥለዋል፡፡

መቼ ይሆን ዘራፊው እየወረረ መዝረፉን፣ ፈንድ ፈንዳጅ ለዘራፊ ስንቅ ማቀበሉን፣ የእነንተኔ ጦር ማፈግፈጉን፣ ባንዳ ፋኖን እንደ ክርስቶስ አሳልፎ መስጠቱን የሚያቆመው?

ተሰደህ የምትኖር ኢትዮጵያዊ  እባክህ ስማ! ዘራፊዎች እንደገና ሊያፈርሱት ተሚችሉት ጎጆ በፊት ፋኖን ገንባ!

አብዛኛህ  በየዋህነት አንዳድህ ደሞ በዘልዛላነት ዘራፊዎች እስከመጨረሻው የተባረሩ መስሎህ የተጎዱ ወገኖችን መኖሪያ፣ ት/ ቤት፣ የሕክምናና የሌሎችም አገልግሎት መስጫ ሥፍራዎችን ለመገንባት ገንዘብህን በመመስለጥ ላይ ትገኛለህ፡፡ አንተ የዋሁ በውጪ የምትኖር ኢትዮጵያዊ የሕዝብን ደህንነትና ንብረት የሚያስጠብቅ የጠነከረ መንግስት ያለ መስሎሀል፡፡ በማፈግፈግ “ስልት” የአገዛዙ ጦር ከመቀሌ ደብረ ብርሃን በአጭር ጊዜ  መስክ ላይ ከተለጋ ኳስ በበለጠ ፍጥነት እንደ ደረሰ “አጪሩ ሚሞሪህ” ረስቷል፡፡ በሌላ በኩል ደግም ፋኖ አብሮ ሲሰለፍ ሌባዎች የተሸከሙትን ቡሃቃ ጥለው አስፋልት ላይ ከተለጋ ኳስ በበለጠ ፍጥነት በስብት ተቃራኒ አቅጣጫ (against gravity) ወደ መጡበት እንደተመለሱ ማገናዘብ ተስኖኻል፡፡

ዶላር መዛዡ ኢትዮጵያዊ ሆይ! ራያና ቆቦ ሲያዙ የወልዲያን ሆስፒታል ወልዲያ ሲያዝ  ደግሞ የደሴን ሆስፒታል አገልግሎት ፋኖን ተመገንባትህ በፊት ገንብተህ ነበር፡፡ ዳሩ ግን የሕዝብ ደህንነትና ንብረት ያስከብራል የተባለው ኃይል ፊቱን ሳይሆን ጀርባውን ለባሩድ ሰጥቶ አዳኝ እንደ ታያት ሚዳቋ ሲፈተለክ የሊጥ ሌባ የምትላቸው ዘራፊ ባንዳዎች ሞጭልፈው አገራቸው መውሰዳቸውን እረስተሃል? መልሰህ የገነባሃው አጣዬ መዘረፉንና መውደሙን ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ዘንግተሃል?

አንተ የዋሁ አገርህን የምትሞድ ኢትዮጵያዊ የሚታመን ጠባቂ ያለ መስሎህ ለእነዚህ ሌባዎች የኋላ ደጀን እንደነበርክና  በቁሳቁስ እንደረዳኻቸው ዘንግተህ ቁጪ ብለሃል? ዘራፊዎች በላከው ገንዘብ እየታከሙና እየተመገቡ ማፈግፈግ የማይሰለቸውን “ጦር” እያባራሩ የወሎንና የሸዋን ከተሞች እንደ ባቢሎን ግንብና እንደ ሰለሞን ቤተመንግስት እንዳጠፉ ተገንዝበሃል?

ማፈግፈግ ባህሉ ያልሆነውን ፋኖ ብትገነባና ብታጠነክር ኖሮ ያወጣኻው ገንዘብ ለወንበዴዎች ጉልበት መሆኑ ቀርቶ ይኸኔ ከአብራኩ የወጣኻውን ሕዝባ ያገለገል እንደነበር ማሰላለስል ችለሃል?

ዛሬም ፋኖን በማጠንከር ፋንታ የፈረሰ መንደርና ከተማ ልትገነባ በየአዳራሹ በስሜት እየጨፈርክ ገንዘብህን ስታወጣ ይታያል፡፡ ፋኖ በባለጊዚዎች ተፈረሰ ወይም ታልጠነከረ ብር እየመሰለጥክ የገነባሀው መንደር ወይም ከተማ መልሶ በወንበዴዎች ላለመዘረፉ ምን ዋስትና ተሰጥቶኻል? ዛሬም ማፈግፈግ ተፈጥሮው ወይም ባህሉ በሆነው በእነ እንቶኔ በሚመራው ጦር ታምናልሀ ወይስ በዝርፊያ የተጠመቀ ወንበዴ ንስሃ ገብቶ ዘረፋውን እንደገና ተመጀመር ይቆጠባል ብለህ “በአጪር ሚሞሪ” ታስባለህ?

ቦንድ ቦንድደህ ለትግሬ ነፃ አውጪ መርክብ የገዛህ፤ ፈንድ ፈንድደህም ሁለተኛውን ይህ አድግ ያደላደልክ ጥገቱ “ዲያስፖራ” ሆይ:-

መለኮት የሚያስተውል ልብና የሚያሰላስል አይምሮ ይስጥህ! ወንበዴ ደጋግሞ በሚወረው አገር ዘበኛ ወይም አጥር ሳትገነባ ነገ ተመልሶ የሚፈርስና የሚዘረፍ ጎጆ መስራት ይቅርብህ፡፡ የምትሰራው ጎጆ ተእነ ቡሃቃው እንደገና ሳይወድም ወይም ሳይዘረፍ አገልግሎት እንዲሰጥ ከፈለክ መጀመርያ ጠንካራ አጥር ወይም ብርቱ ዘበኛ ይኑርህ፡፡ ያ ጠንካራ አጥር ወይም ብርቱ ዘበኛ ፋኖ ነውና ተጎጆው በፊት ፋኖን ገንባ፡፡ እባክህ ንቃ! ብርህን እየመሰለጥክ ዘላለም ሌባንና የወገንህን ከተማ የሚያጋይ ወንበዴ በተዘዋዋሪ አትርዳ! ለብዙ ሺህ ዓመታት የኢትዮጵያ አጥር፣ መከታና ዋልታ ፋኖ ነውና ፋኖን እርዳ! ፋኖን ገንባ! አመሰግናለሁ፡፡

 

ተመሳሳይ ጽሑፎች

  1. ዓባይንማን መቼ ይገድበው? http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/06/Abay.pdf
  2. እስከመቼ ከትል ያነስን ቦንደኞች?  http://quatero.net/amharic1/archives/28589
  3. ምሁራንበእባብ ተሸውደው የዕፀ በለስ ፍሬ መግመጥ እሚያቆሙት መቼ ነው? https://www.satenaw.com/amharic/archives/37149

 

ጥር ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ.ም.

 

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ONLD 750x500 1
Previous Story

የአማራ ብልፅግና ግሳግስ ሆይ ወይ ይቅርታ ጠይቅ ካልሆነ አሁኑኑ ስልጣን ልቀቅ !!! (ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ)

Abiy 71
Next Story

መንጋነት እና ፓለቲካል በግ’ነት ተነጣጥለው አይታዩም ( አባታጠቅ  ምንዳሁነኝ )

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop