August 27, 2022
11 mins read

አማራው የሚዘምተው በታማኝ የቁርጥ ቀን የእማራ ልጆች አመራር ስር ብቻ ሆኖ ነው (እውነቱ ቢሆን)

ETHIOPIAN INTEL

የአውሬውና ተንኮለኛው የአብይ አህመድ አገዛዝ ጀግናውን ፋኖን ኢመደበኛ ብሎ ገሚሱን አሰሮ ገሚሱን ደግሞ ጥቁር ክላሽ ዘርፏል ብሎ እያሳደደ ባለበት ሁኔታ ውስጥ አሁን አብይ ራሱ ከወያኔ ጋር ተናብቦ  በጸረአማራነት ሴራ በጋራ አሲረው ሁለቱ ላስጀመሩት ጦርነት ፋኖን፣ የአማራ ወጣትን የአማራ ህዝብን ምስለኔወቹ “ ”ና ዝመት” ” እያሉ ጥሪ እያካሄዱለት ነው፡፡ የፌደራል መንግስት ተብየውም እንደዚሁ ጥሪ እያካሄደ ነው፡፡

የአማራ ዘማች ሆይ፦ አንተ ከመሀል ስትገባ ከወዲያ ወያኔ ከወዲህ ኦሮሙማ ሆኖ ጭዳ ሊያድርጉህ ያሰቡትን ቅዠታቸውን ንቃበት፡  በዚህ መልኩ አማራ ይሰልፋል ማለት መቃዠት መሆኑን ለሁለቱም ጠላቶችህ  ንገራቸውና በራስህ ተደራጅተህ በሁለቱም ላይ በራስህ ጊዜ፣ በራስህ ፕላን፣ በራስህ አመራር ዝመት፡፡  አንድ የማይካድ ሀቅ አለ፡፡  ወያኔ አንደኛ ደረጃ የአማራ ጠላት ስለሆነ ሊዘመትበት ግድ ይላል፡፡አማራው ወያኔን ድል ማድረግና ማጥፋት አማራ ለሆነ ሁሉ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው፡፡  ምክንያቱም አማራን ደጋግመው ክደውታል፡፡  ምሳሌ በበፊቱ ወረራ ደሴ ላይ በአሁኑ ወረራ ደግሞ ቆቦ ላይ ይህንኑ በተግባር ፈጽመውታል፡፡  ምክንያቱም አማራን ጠላታችን ነው ብለው በወያኔ ማኒፊስቶ ላይ አስፍረውታል፡፡ ምክንያቱም  ህዝቡን አማራ ጠላትህ ነው ብለው ለዘመናት ሰብከውታል፡፡ ስለዚህ ወያኔ (የትግራይ ህዝብ አላልንም) የአማራ አንደኛ ደረጃ ጠላት ስለሆነ መጥፋት አለበት፡፡   ስለዚህም ነው አማራ በወያኔ ላይ የሚዘምተው፡፡

አማራ በኦሮሙማ ላይም ይዘምታል፡፡የኦሮሙማ ክፍልፋዮች አንድ የሚስማሙበት ጉዳይ አለ፡፡ እርሱም ወሎ (ሰሜን ኦሞም ነው የሚለው ከንቱ ትርክታቸው ነው፡፡ ስለሆነም ኦሮሙማም የአማራ ጠላት ነውና አማራው ኦሮሙማ እስካልታረመ  ድረስ ይዘምትበታል፡፡  በወለጋ በቅርቡ በየቀኑ አንድ ሽህ አማራወችን እያረደ ግዳይ ይጥል የነበረው በአብይ አህመድ አገዛዝ በእጅ አዙር የሚደገፈው በዳቦ ስሙ ሸኔ እያሉ የሚጠሩት የኦሮሙማ ቡድን መሆኑን ሁሉም ያውቃል፡፡ ማን ሆነና ነው ሰው ገድሎ ዘቅዝቆ የሰቀለው?? ማን ሆነና ነው እርጉዝ የአማራ ሴትን አርዶ ጥሎና  ሽሉን ከሆዷ ቀድዶ አውጥቶ ልጇን በእጇ ያስታቀፈው?? ይህ ይረሳልን??? ስለዚህ ከኦሮሙማ ጋር አማራው የሚያወራርደው ሂሳብ አለው፡፡  ይህ ጉዳይ ሽህ አመታት ቢወስድም ከአማራ ህሊና አይፋቅም፡፡ የሚብላላ የማይታጠፍ  የየትውልዱ የአማራነት  ምህላ ነው፡፡

በተለይ አሁን ላይ አማራ የሚዘምተው ባስገደሉት፣ ባሳሰሩት፣ አንገቱን ባስደፉት አሁን ባሉት ሹመኞች ማለትም የአማራ ብልጽግና ተብየወች ስር ሆኖ አይደለም፡  በእነርሱ አዝማችነት ስር ሆኖ የሚዘምት አማራ የለም፡፡ ካለም ሞኝ፣ ሞኛ-ሞኝ፣ ጅል፣ ጅላጅልና ጅላንፎ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡  አሁን ላይ ዘግይቶም ቢሆን አማራ የጠላቶቹ የወያኔና የኦሮሙማ ስሌት ገብቶታል፡፤ ያልገባው ወይንም እንዳልገባው የሚያስመስለው ክፍል ቢኖር ሆዳሙና ጥቅመኛው ምስለኔው ብቻ ነው፡፡

እንድገምላችሁ፡፡ አማራው ይዘምታል፡፡ የሚዘምተው ግን በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ አመራር ስር ሆኖ ነው፡፡ የሚዘምተው ግን በእውቆቹና ጀግኖቹ የፋኖ መሪወች ስር ሆኖ ነው፡፡ በእነ ዘመነ ካሴ ፣ በእነ መሬ ወዳጆ፣  በእነ ጀኔራል ሀስን ከሪሞና …..ወዘተ ታማኝ የቁርጥ ቀን የእማራ ልጆች አመራር ስር ብቻ ሆኖ ነው፡፡ እነዚህ የቁርጥ ቀን የአማራ አርበኞች ደግሞ በአብይ አህመድ ትእዛዝ አብዛኛወቹ ታስረዋል፣ ተሰደዋል፡፡

መንግስት ተብየው የጅላንፎወች ስብስብ አሁን አገሪቱ ላለችበት አሳሳቢ የወረራ ድራማ  (ድራማው ቲያትር ካልሆነ) እነዚህ የቁርጥ ቀን የአማራ ልጆች በጦርነቱ ውስጥ ገንቢ ሚና ይጫወቱ ዘንድ ከፈለገ በይፋ በህዝብ ፊት በፋኖ ላይ ስህተት መስራቱን አምኖ ፋኖወችን ይቅርታ ሊጠይቃቸውና ዋስትና ሊሰጣቸውም ይገባል፡፡  (ነገሩ ስህተት ሳይሆን ተንኮል ነበር)፡፡ መንግስት ተብየው የጅላንፎወች ስብስብ በአለምና በኢትዮጵያ ህዝብ  ፊት ይህንን በይፋ ካደረገ  የተወሰነ ተአማኒነትን በስንዝርም ቢሆን  ሊያገኝ ስለሚችል ለራሱም ይጠቅመዋል፡፡ መንግስት ተብየው የጅላንፎወች ስብስብ ይህንን ካደረገ አማራው ነቅሎ ወጥቶና በራሱ ልጆች አዝማችነት ስር ብቻ ዘምቶ ወያኔን ድባቅ መትቶ በቀላሉ  ሊያሸንፋትና ከመሰረቷም ነቅሎ ሊጥላት አቅምና ወኔ ያለው ሀይል ነው፡፡ መንግስት ተብየው ስብስብ ይህ እንድሆን ካላደረገ አማራውም በአስገዳዮቹ ስር ይዘምታል ብሎ ማሰቡ ሞኝነት ነው የሚሆነው፡፡

እቅጩን እንናገር፡፡ አማራው በአብይ አህመድ አሽከሮች ማለትም ፣ ደመቀ መኮንን፣ ግርማ የሽጥላ  ዶ/ር ይበልጣል ከፋለና ወዘተ ለኦሮሙማው አገዛዝ ታማኝ በሆኑትና በተሸጡት የአማራ ሆዳም አመራሮች ስር ሆኖ አይዘምትም፡፤ በራሱ በፋኖወችና በራሱ የጎበዝ አለቆች አመራር ስር ብቻ ሆኖ ነው የሚዘምተው፡፤  መንግስት ተብየው የጅላንፎወች ስብስብስ በይፋ ወጥቶ ፋኖን ይቅርታ ጠይቆ ወደዘመቻው ካልሳበው ከሁሉ በፊት የአማራ ዘማች አፈሙዙን በብአደን ላይ ይደቅናል፡፡ ፋኖና ሌላው የማራ ህዝባዊ ሀይል ዘማች በቅድሚያ ይህን ካከናወነ በኋላ ለፋኖና ለአማራው ተዋጊ ሀይል ሌላው ጉዳይ ሁሉ እዳው ገብስ ነው የሚሆንለት፡፤ የወያኔም የኦሮሙማም እዳ ለሀያሉ የአማራ ክንድ ምኑም አይደለችም፡፤ የአማራው ዋናው ጠላቱ ሆዳም አማራወቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ትርፍ አንጀቶች ወይ ይህንኑ አውቀው ከመንገዱ ገለል ይበሉለት፡፡ አለበለዚያም ራሱ እስከወዲያኛው ገለል ያደርጋቸዋል፡፡

ለመድገም ያህል ወያኔ ወጥታ ወርዳ ልትይዝ የምትፈልገው ራያንና ወልቃይትን ሲሆን እነዚህን ታሪካዊ የአማራ ርስቶች ከአውሬው አብይ አህመድ ጋር ሴራ ጎነጎነችም ወይንም ከምእራባዊያን ጋር ዱሮ  ዘረፈችው ዶላር “”ፍጥምጥም”” ፈጸመች   ያ ቢወጣ ይህ ቢወርድ መቼም ቢሆን መቼም ራያንና ወልቃይትን መያዝና የወያኔ ርስት ማድረግ አይሳካላትም፡፤ ኦሮሙማም እንደዚሁ ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ ነው  የሚለው ቅዠቱ ምንጊዜም አይሳካለትም፡፤ በጥቅሉ ሁሉም ይህንን አውቆ ካልተረዳና ካልታረመ በስተቀር በአገሪቱ ላይ የሚኖረው ተያይዞ እልቂት እንጅ ለአንዱ የተለየ ድል አይሆንለትም፡፡

ለማንም ቢሆን የፈለገውን ጊዜ ይወስዳል እንጅ ከሀቅና ከእውነት ውጭ የሚመጣ ቋሚ መፍትሄ አይኖርም፡፡ እልቂቱ ለሁሉም እልቂት ሆኖ ይቀጥላታል እንጅ የአማራውና የአፋሩ እልቂት ብቻ ሆኖ አይቀርም፡፡ መፍትሄው አንድና አንድ ነው፡፤ በሀቅና በታሪክ ላይ የተመሰረተ እውነት ብቻ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop