August 22, 2022
17 mins read

ይድረስ ለአማራ ምሁራን! ሌላውን ድስኩር ተውና የአማራን ዘር ፍጅት አስቁሙ! – በላይነህ አባተ

Amhara Genocice

በላይነህ አባተ ([email protected])

“እየየም ሲደላ ነው” ይባላል፡፡ አማራን ለማጥፋትና እርስቱን ለመቀማት ዛሬም የጦር ነጋሪት እየተጎሰመበት የአማራ ምሁራን ዛሬም በግድብ ስብከት፣ በሰይጣኖች የማይታመንና የማይጠና እርቅና በሌሎችም አዘናጊ አጀንዳዎች ጀንዲ እሚያካክል ጠልሰም ሲጠለስሙና ጣታችውን እያፍተለተሉ ሲደሰኩሩ ይታያል፡፡ ከንቱነት፣ ሆዳምነት፣ አስመሳይነትና አድርባይነት ካልሆነ በቀር በአሁኑ ሰዓት ለአማራ ከህልውና የበለጠ ሌላ ምን አጀንዳ ይኖረዋል?

የአማራ ምሁራን ሆይ! የሕዝባችሁን እልቂት የሚተነብዩ ጉልህ ምልክቶችን እንዳላየ አልፋችሁ ለሰላሳ አንድ ዓመታት በአማራ ለደረሰው የዘር ማጽዳት ወንጀል አስተዋፅኦ አድርጋችሗል፡፡ “አይሆንም ትተሽ ይሆናልን አስቢ” የሚባለውን ብሂል ዘንግታችህ “በእስቲ እንያቸው!” ዘልዛላ አስተሳሰብ ሕዝባቸሁንና አገራቸሁን ለዚህ አብቅታችኋል፡፡

የትግሬ ነፃ አውጪን ፀረ-አማራ ግቦች መፈተሽ ሰንፋችሁ አማራ ለሃያ ሰባት ዓመታት የገሃነብ ኑሮ ኖሯል፡፡ ይህ ቡድን የአምራን ለም መሬት ወልቃይትና ራያን እንደሚዘርፍ የቀረውንም ለጡት አባቱ ለሱዳን እንደሚያስረክብና የተፈውንም በክልል እንደ በሬ ቅርጫ እንደሚከፋፍል አማራ ምሁራን ለመተንበይ ሰንፋችኋል፡፡ በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ራሱን ለመከላከል ያልተዘጋቸው አማራ እንደ ቅርጫ በተከፋፈለች አገር በማያውቀው “ሕገ-መንግስት” እንዲገዛ ተገዷል፡፡ ከሌሎች በከፋ መልኩ ሲታሰር፣ ሲገረፍ፣ ሲሰለብ፣ ሲሰደድ፣ በርሃብና በበሽታ ሲረግፍ ኖሯል፡፡ ፀረ-አማራ ገዥዎች የራሱን ባንዳ ልጆች ዛቢያ አድርገው ከደጁ ሞፈር ቆርጠዋል፤ ታሪኩና ቅርሱን አፈራርሰዋል፡፡ ከቅየው እያፈናቀሉ በእርዳታ ነፍሱን የሚያሳድር ሜዳ አዳሪ ሕዝብ አድርገውታል፡፡

ህሊና ያለውና ማፈርን የሚያውቅ አማራ ምሁር ለአምሳ ዓመታት በአማራ የደረሰው ግፍ እሳት እንዳየው ላስቲክ ሊያሸማቅቀው ይገባል፡፡ “በሞቴ አፈር ስሆን” እያለ እያጎረሰ ያሳደገውን ማህበረሰብ በጥቅም ታስሮ ወይም ሆዱን መርጦ በጅቦች ማስበላት መረገም መሆኑን ማጤን ይገባዋል፡፡ ፈገግ ሲል ሲል እየሳመ የታቀፈውን፣ ሲወድቅ ያነሳውን፣ ሲማር መቀነት እየፈታና ኪሱን እየፈተሸ ኮቢ የገዛለትን፣ ሲዳር ደግሶ የዘፈነለትንን፣ ሲሞት ፍታትና ተስካር የሚያወጣለትን ሙሉ በኩሉሔ ሕዝብ ለጅቦች አሳልፎ በመስጠቱ ሊፀፀት ይገባል፡፡ ከእነ ድንበሯና ክብሯ አገር ያስረከበውን ሕዝብ እንደ ይሁዳ ክዶ እልቂትን ካመጡበት ክፉዎች ጎን መቆም ሲኦል የሚከት ግዙፍ ኃጥያት መሆኑን ማመን ይኖርበታል፡፡

የአስኳላው፣ የቤተክህነትና የቤተ መስጊድ ምሁራን አማራ ዛሬ ከሚደርስበት እልቂት ወደፊት ሊደርስበት የሚችለውን አደጋ መተንበይ አሁንም ሰንፏል፡፡ ምሁራን በትናቱ ምልክት የዛሬውን መተንበይ ስላልቻሉ አማራ ዛሬ በመላ አገሪቱ እየታረደና እየተሰደደ ይገኛል፡፡ ምሁራን በዛሬው ምልክት የነገውን እየተነበዩ ስላልሆኑ አማራ ገና ብዙ ችግር ይጠብቀዋል፡፡ እንደ አለመታደል የአማራ ምሁራን ከዛሬው ምልክት የነገውን በመተንበይ ፋንታ በሱሰኛ የላቲን ሙሴዎች ቀንበር ተጠምደው በካድሬነት ሲያገልግሉ ይታያል፡፡ ለአማራ ህልውና አስተዋፅኦ ከማበርከት ይልቅ አማራን ለመታደግ የሚፍጨረጨሩትን ፋኖዎች በማብጠልጠልና በመጥለፍ እርኩስ ሥራ ተጠምደው ማየት እጅግ ያሳፍራል፡፡

ወጣቶቹ ለዚህ መከራ የተዳረጉት እኛ ታላላቅ ወንድሞችና አባቶቶች ሐላፊነታችንን ስላልተወጣን መሆኑን የላቲን ሙሴዎች ተከታዮች የማራ ምሁራን ዘንግተዋል፡፡ እኛ ሐላፊነታችንን ብንወጣ ኖሮ ወጣቶቹ ሥለሰማይና ሥለምድር ሲመራመሩ ይውሉ እንደነበር ማስተዋል ተስኗቸዋል፡፡ ወጣቶቹ የህልውና ትግል የሚያደርጉት እኛ ከከተትናቸው ገደል ለመውጣት መሆኑን የሚያመልኩት የላቲን ሙሴ አስረስቷቸዋል፡፡

የህልውና ትግል የሚያደርገውን ወጣት የአማራ ምሁራን እየጠለፉ ከሚጥሉባቸው ወጥመዶች አንዱ ዛሬምት “ኢትዮጵያ፣ ዜግነት፣ ማህበራዊ ፍትህ!” የሚባል ዘፈን ሆኗል፡፡ ይኸንን ዘፈን ማዘውተር አማራን ለሰላሳ ዓመታት አሳርዷል፡፡ እንዲያውም በዚህ ዘፈን ወጣቱን መጥልፍና መጣል አማራው ለሌላ ዙር የዘር ማጥራት አጋልጦ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡

ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ፣ አንድነት፣ ዜግነት” እያሉ በሰፋፊ አዳራሽ የዘፈኑ ፓርቲዎች አማራን በበደኖ ገደል ከመወረውር፣ በአርባ ጉጉ ከመታረድ፣ ከወልቃይት፣ ከራያ፣ ከመተከል፣ ከጉራ ፈርዳና ከወለጋ በችፍርግ ከመጠረግ አድነዋል ወይ? ኢትዮጵያ፣ ዜግነት ማህበራዊ ፍትህ እያሉ እሚደልቁት ቡድኖች ዛሬ አማራ ካድራ ወንዝ፣ ሀረር፣ ወለጋ፣ መተከል፣ ከሚሴ፣ ሸዋና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ሲታረድና ሲሰደድ እንኳን ሊከላከሉ ድርጊቱን የሚያወግዝ ትንፋሽስ ቱስ ብሏቸዋል ወይ? ሲሞዳሞዱ የሚውሉት ከገዳዮችና ከአስገዳይዎቹ ጋር አይደለም ወይ?

ኢትዮጵያ፣ አንድነትና ዜግነት በሚል ፋሻ የአማራን ቁስል እየሸፋፈኑ አማራ ሳይደራጅ በተደራጁ ሐይሎች እንዳለፉት አርባ ሁለት ዓመታት እንዲያልቅ ማድረግ በምድርና በሰማይ የሚያስጠይቅ የወንጀሎችና የኃጥያቶች ቁንጮ አይደለም ወይ? የአማራን የመከላከል ሐይል ለማዳከም የዜግነት ፓርቲ አቋቋምን ብለው የውሸት መሐላ በየወንዙ ከሚማማሉት አብዛኞቹ በድርጅቶቻቸው አማራን አስበልተው በመጨረሻም አማራን ከበላው ድርጅት እግር የወደቁ ይሁዳዎች አይደሉም ወይ? እነዚህ ይሁዳዎች አማራ ነገ የሚደርስበትን ችግር ይከላከላሉ ተብሎ ይጠበቃል ወይ?

የአማራ ምሁራንን ከንቱ ድስኩርና ስብከት እየሰማ ያልተደራጀው የአማራ ወጣት ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ከመከራ ወጥቶ ያውቃል ወይ? የአማራ ምሁራንን የማያልቅ ከንቱ ስብከት ተማምኖ ወጣቱ ዛሬም እንደ ትናንቱ ለመገረፍ፣ ለመሰለብ፣ ለመሰደድ፣ ከትምህርት፣ ከጤናና ከስራ ተገሎ ለመኖር እጁን አጣጥፎ ይቀመጥ ወይ? ድርጅት እንደ አፈር ሲቆልሉና መልሰው ሲንዱ፣ ፓርቲ እንደ ፍሪንባ ሲተለትሉና እንደ ክትፎ ሲከታትፉ የኖሩ ፖለቲከኞችን ዛሬም አምኖ ራሱን ተመከላከል ይታቀብ ወይ? አማራ ሲታሰር፣ ሲገረፍና ሲሞት የኖረው በእነዚህ ፓርቲ እንደ ጪቃ ሰርተው በሚያፈርሱ ፖለቲከኞች አይደለም ወይ? እነዚህ ፓርቲ በመሰንጠቅ እጥፍ ድርብ ፒ ኤች ዲ ያላቸው ከሀዲ ፖለቲከኞች እንኳን የኢትዮጵያን ሕዝብ ራሳቸውንስ አንድ ያደርጋሉ ወይ? እነዚህ ፖለቲከኞች እንደ ሳሙኤል አወቀ ተቀጥቅጠው የተገደሉትን በማተባቸው አዳሪ ወጣቶችና በድርጅቶቻቸው ስም የተሰለቡትንና አካለ ስንኩላን የሆኑትን ዜጋዎች ክደው ዛሬ ከገዳዮችና ከገራፊዎች የሚሞዳሞዱ ይሁዳዎች አይደሉም ወይ?

አማራ ምሁራን ወይ! በዓለም ማህበራዊምና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን ለማስፈን የቻለ ቡድን የለም፡፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ በምድር ሰፍኖም አያውቅም፡፡ ወደፊትም ሕዝብ እየበዛና  እንደ መሬትና ውሀ ያሉ መሰረታዊ እሴቶች እየጠበቡና እያነሱ በሄዱ ቁጥር የማህበረሰባዊና የኢኮኖሚ ስርጭቱ ከፍትህ እየራቀ የሚሄድ ነው፡፡ እስካሁን እንደታየው ዓለም ወደ ማህበራዊ ፍትህ ፊቷን የምታዞረው በማህበረሰቡ መካከል የጉልበትና የጥበብ ሚዛን ሲኖር ብቻ ነው፡፡ አንዱ እንደ ገመድ ወፍሮ ሌላው እንደ ክር ቀጥኖ ማህበራዊ ፍትህ እያሉ ቢተርቱ ህጻንም አምኖ አይቀበልም፡፡ ዓለም ተቻችላ ያለችው በሐይል ሚዛን ነው፡፡ አገርም ተቻችሎ እሚኖረው በኃይል ሚዛን ነው፡፡ የፍትህ ስብከት ህፃናትን የሚጨፈጭፍና የሚሰልብ ጭራቅን ግብር ያከፋዋል እንጅ አያሽለውም፡፡ ምክር የላም አሸናፊን እንደ ፌንጣ  የበለጠ ያቅበጠብጠዋል እንጅ አያስታግሰውም፡፡

ጠንካራ ዲሞክራሲና ሕግ አላቸው በሚባሉት አውሮጳና አሜሪካ ሳይቀር የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ ፍትህ ዛሬም የለም፡፡ ቀለማሙ ሕዝብ ሊፈጥር በሞከረው የኃይል ሚዛን ትግል ከቤት ባርያነት ቢላቀቅም ዛሬም የውጪ ባርያ ነው፡፡ ባርያው ያደረገው መጠነኛ ትግል ፈቀቅ ያደረገው ከቤት ወደ ውጪ ብቻ ነው፡፡ ይህ የውጪ ባሪያ ዛሬም መንገድ፣ ሽንት ቤት፣ ሆስፒታልና ቢሮ ጠራጊ ነው፡፡ ይህ የውጪ ባሪያ ዛሬም የጡረተኞችንና የአካለ ስንኩላንን ሽንት እየጠረገ የሚጦር ባርያ ነው፡፡ በየትኛውም ዓለም የማህበራዊ ፍትህ ያለው ከወረቀትና ከውሸታም ፖለቲከኞች ላንቃ ብቻ ነው፡፡

ዓለምን ሲገዛት የኖረው፣ ዛሬም የሚገዛት ወደፊትም የሚገዛት የአካላዊና የአይምሮ የበላይነት ወይም ጉልበት ነው፡፡ ዓለምን የሚያሽከረክራት የከዳነው የመለኮት ትዕዛዝ ሳይሆን የተቀበልነው የሳጥናኤል መንፈስና ዳርዊን የቀመረው የጉልበት አሰላለፍ ብቻ ነው፡፡

አማራ በአጥንቱ ግድግዳነትና በደሙ ምርግነት ባቆማት አገሩ ቤቱ በግኒደር እየፈረሰና ንብረቱ እየተቀማ ተገድሎ በጅምላ በግኒደር ታፍሲ የሚቀበረው የውጪ ጠላትን ያንበረከከበትን የጉልበትና የጥበብ ሕግ ለውስጥ ጠላቱ ስላልተጠቀመበት ነው፡፡ አማራ እየተገደለ ገደልና ሽንት ቤት የተጣለው ሊበላው የመጣውን ጅብ ኢትዮጵያ፣ አንድነት፣ ዜጋ፣ ፍትህ በሚባሉ ለጅብ በማይገቡ ጽንሰ-ሐሳቦች ሊመልስ በመሞከሩ ነው፡፡ አማራ ህልውናው አስጊ ደርጃ የደረሰው ምሁሮቹ ለጅብና ጭራቅ በማይገቡ ቋንቋዎች ቀፍድደው እንዳይደራጅ ስለከለከሉት ነው፡፡ ዛሬም አማራን ለእልቂት የሚያጋልጡት ከትናንቱ ምልክት ዛሬን ከዛሬውም ነገን መተንበይ የማይችሉ ከአብራኩ የወጡ ድስኩራም ምሁራን ናቸው፡፡

የአማራ ምሁራን ሆይ! አማራን በጠላትነት የፈረጁ ሐይሎች ዛሬም በውጪ ኃይላት እየተረዱ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ነው፡፡ ይኸንን ለመቋቋም እንደ አያቶች ጎራው ያለው ፋኖም በሆዳምና በባንዳ ውሻዎች አቀንጣጤ እየተነከሰ ነው፡፡ ተምድር የሚታየው ይኸ ሆኖ ሳለ የአማራ ምሁራን አማራን በድርጅት፤ በጥበብ፣ በቁሳቁስና በመንፈስ እንዲጎለብት ሌተ ተቀን መስራት ሲገባ በግድብ፣ በሰይጣኖች እርቅና በሌላም ሌላም ወለፈንዲ ማዘናጊያ አጀንዳዎች አማራን ሰንጎ መያዝ ተይሁዳም አልፎ የሳጥናዔል እኩይ ግብር አይደለም ወይ?

 

የአማራ ምሁራን ሆይ! እባካችሁ ሌላውን ከንቱ ድስኩር ሁሉ ተውና የአማራን የዘርፍ ፍጅት በመከላከልና በህልውናው ትግል አተኩሩ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ. ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop