August 13, 2022
5 mins read

ለምን የብሔር ፖለቲካ የሙጥኝ ይባላል? (ታምራት ኪዳነማርያም)

297942778 5843842298982151 5614254048042794761 n

የፍትሐዊ ሀብት ክፍፍል መታጣት እና ደህና ኑሮ መኖር ያለመቻል መንስዔ የብሔር ዕኩልነት ያለመኖር ነው ብለው የሚያምኑ ፖለቲከኞች ከ30 ዓመታት በላይ የብሔር ፖለቲካ ቢያራምዱም የተፈለገው ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልም ሆነ የተሻሻለ ኑሮ ሊገኝ አልቻለም።

ሀቁን ለመናገር የ20ኛው ክፍለዘመን በኢትዮጵያ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እና የልማት እጦት የሚስተዋለው በዋናነት በብሔረሰቦች መካከል ሳይሆን በገጠርና በከተማ መካከል ነው። ምክንያቱም በብሔረሰብ ጨቆነ የተባለው አማራ ገጠር ውስጥ ቢኬድ በልማት ተጠቃሚነቱ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ የባሰ እንጂ የተሻለ አይደለም።

298460140 1048386545864025 6092905260383410139 nገጠሩ በተቻለ መጠን የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን እና ማንነቱና ባህሉ እንዲከበር ቢደረግ ሁሉም ብሔረሰቦች የልማት ተጠቃሚ ይሆናሉ። ምክንያቱም አብዛኛው የብሔረሰብ አባላት የሚኖሩት በገጠር እንደመሆኑ መጠን ገጠሩ የልማት ተጠቃሚ ሲሆን እነሱም ተጠቃሚ ይሆናሉ። የኢትዮጵያ ባህሎችን፣ ባህላዊ ዕውቀቶችን፣ ቁሳቁሶችን እና ምርቶችን ማበልፀግና በተገቢው ጥቅም ላይ ማዋል ቢጀመር ሀገሪቱን በዓለም መድረክ ላይ የራሷን ተፎካካሪ ሥልጣኔ እንድታሳድግ ከማስቻሉም በላይ በገጠርና በከተማ መካከል ዕኩልነትና የበለጠ መከባበር ያሰፍናል። ይህ የሀገሪቱ ብሔረሰቦች የሚገባቸውን ክብር የበለጠ እንዲያገኙ ከድረግም በላይ ሀገሪቱን ያሳድጋል።

ሌላው የአብዛኛዎቹ የብሔረሰብ ፖለቲከኞች እና መብት ተሟጋቾች አስገራሚ አካሄድ ኢትዮጵያዊነትን ጥለውና አጣጥለው ሲያበቁ በብሔረሰብ ማንነታቸው ሊከበሩ ይፈልጋሉ። የሀገሪቱን ባህልና ታሪክ አንቋሽሸው እጃቸውን ለፈረንጆች ከሰጡ በኋላ ከጣሉት ኢትዮያዊነት ውስጥ የራሳቸውን ብሔር ማንነትና ባህል አንስተው አቧራውን አራግፈው በብሔር ማንነታቸው ሊከበሩ ይሻሉ። በኢትዮጵያዊ ማንነቱ የሚያፍር እና አውሮፓን ከፍ የሚያደርግ ትውልድ እየቀረጹ የብሔር ማንነታቸውን እንዲያከብርላቸው ይፈልጋሉ። የማይሆን ነገር ነው። ኢትዮጵያዊነት ተንቆና ተዋርዶ ብሔረሰቦች የሚገባቸውን ክብር ሊያገኙ አይችሉም።

የብሔር ፖለቲከኞች በገጠርና በከተማ መካከል ያለው መስተጋብር ቢስተካከል፣ ኢትዮጵያዊነት ተገቢውን ክብር ቢያገኝ እና ወደራሳችን ብንመለስ አብዛኛው የብሔር ጥያቄ እንደሚመለስ ተገንዝበው በብሔረሰቦች መካከል ጠብ ከመፍጠርና ሀገርን ከማጥላላት ፖለቲካ ቢርቁ ጥሩ ነው። የችግሩን መንስዔና መፍትሔ በትክክል አገናዝበው፣ ሕዝብን ከማጥላላት፣ እርስ በእርስ ከማጋጨት እና ከፍረጃ ርቀው ለገጠርና ከተማ ፍትሐዊ የሀብትና ልማት ተጠቃሚነት፣ ለኢትዮጵያ ባህሎች መከበር፣ ለባህል ዕድገት፣ ለሀገራዊ ዕውቀቶች መዳበር፣ ለባህላዊ ቁሣቁሶችና ምርቶች መበልፀግ ወዘተ፣ ለኢትዮጵያዊነት ክብር፣ ለታሪኳ ከጥላቻና ከተሳሳተ ትርክት መራቅ፣ ለኢትዮጵያ በአስተሳሰብ እና በዕውቀት እራሷን መቻል ወዘተ. ቢሠሩ ጥሩ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Ethiopia 1 1
Previous Story

ትንሿ ምሳር ወይም ጥልቆ ትልቁን የኮሶ ዛፍ ገዝግዛ ትጥላለች! – አገሬ አዲስ

OLF
Next Story

እንዳንደናገር እንጠንቀቅ፣ – ክገብረ አማኑኤል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop