ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሐሙስ፣ ነሃሴ ፭፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Aug. 11, 2022) ቅጽ ፱ ቁጥር ፯
ዐማራ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን አጥብቆ የሚታገልለት ግቡ መንግሥትን ከነህገመንግሥቱ መቀየር ብቻ መሆን አለበት።
ኢትዮጵያን ከድጡ ወደማጡ ለመውሰድ የሚያንደረድረው ኦሮሙማ የአዲስ አበባን ህዝብ በፍርሀት ሸብቦ መያዙ ሳያንስ በወለጋና በመተከል የተጀመረው ጥቃት ጎልብቶ አዲስ አበባ መግባቱ እየታየ ነው። መሀል አዲስ አበባ መኪና ለመውሰድ ሲባል ወጣት የመኪና አሽከርካሪዎች እየታረዱ እንደሚጣሉና ከፍተኛ ወንጀል እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ታይቷል።ወንጀለኞቹ ለህግ ቀርበው ፍርድ አለማግኘታቸውና አዲስ አበባ የሰው ህይወት ቀጥፎ መኪና የሚዘርፍ ወንጀለኛ በመበራከቱ የብዙዎች ቤት እየተፈታ፣ ህዝቡን በሰቀቀን ያለዋስትና እንዲኖር ተፈርዶበታል።
አብይ አህመድ የኦሮሞ ህዝብ መዝሙር በአዲስ አበባ መዘመር የለበትም። ለሚለው የህዝብ ጥያቄ የመለሰው መልስ ኦሮሞን የሚጠላ ሕዝብ በአዲስ አበባ እንዳለ ለማስመሰል የተውገረገረበትና ፍፁም ከጠቅላይ ሚንስትር የማይጠበቅ ጠብ አጫሪ መልስ እንደሆነ አይተናል። ነገር ግን ህዝቡ ተቃውሞው በቋንቋው ብቻ ሳይሆን መዝመሩ ያዘለው ኢትዮጵያን የሚከፋፍል መርዝ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ አሁንም መላው የአዲስ አበባ ህዝብ “የአመታትን ጭቆና በደም አጥበንልሻል” የሚል ይዘት ያለው የኦሮሙማ መዝሙር መቸም ቢሆን አዲስ አበባ ላይ መዘመር ስለሌለበት በአቋሙ ፀንቶ ሊታገል ይገባዋል።
አብይ አህመድ የኦሮሞ ህዝብ መዝሙር በአዲስ አበባ መዘመር የለበትም። ለሚለው የህዝብ ጥያቄ የመለሰው መልስ ኦሮሞን የሚጠላ ሕዝብ በአዲስ አበባ እንዳለ ለማስመሰል የተውገረገረበትና ፍፁም ከጠቅላይ ሚንስትር የማይጠበቅ ጠብ አጫሪ መልስ እንደሆነ አይተናል። ነገር ግን ህዝቡ ተቃውሞው በቋንቋው ብቻ ሳይሆን መዝመሩ ያዘለው ኢትዮጵያን የሚከፋፍል መርዝ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ አሁንም መላው የአዲስ አበባ ህዝብ “የአመታትን ጭቆና በደም አጥበንልሻል” የሚል ይዘት ያለው የኦሮሙማ መዝሙር መቸም ቢሆን አዲስ አበባ ላይ መዘመር ስለሌለበት በአቋሙ ፀንቶ ሊታገል ይገባዋል።
የዐማራ ህዝብ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ተፈርዶበት ቀደም ሲል በህወሓት ወያኔ፣ አሁን ደግሞ በኦሮሙማ ብልፅግና በዘርፈ ብዙ መከራና እልቂት ላይ ይገኛል። መቋጫ ያጣው የዐማራ መከራ ከ 30 ዓመት በኋላም ተጠናክሮ በመቀጠሉ ምክንያት በአውቶብስ ተሳፍሮ የመጡ መንገደኞች መታወቂያቸው ከምስራቅ ዐማራ መሆኑ ከተረጋገጠ አዲስ አበባ ጫፍ ከደረሱ በኋላ በኦሮሚያ የፀጥታ ኃይሎች እንዲመለሱ፣ እንዲጉላሉ መደረጉ ልብ ሰባሪ ግፍ ነው። ዛሬ አዲስ አበባ አትግቡ የተባለው ነገ ከአዲስ አበባ እንዳትወጡ እንደማይባል ምንም ማረጋገጫ አይገኝም፣ አብይ አህመድና ብልፅግና ከወያኔ ጋር ባለው ጥልድረሱልኝ ባለ ሰዓት የሕዝብን እልቂትና የሀገርን የመፍረስ አደጋ ከመንግሥት ጋር ቆመው፣ ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው፣ ደማቸውን አፍስሰው፣ ህይወታቸውን ገብረው ከአደጋ የታደጉትንና ከሞት የተረፉትን ጀግና የዐማራ ፋኖዎች በመክዳት እያፈኑ እንዲጠፉ መደረጉ የኦሮሙማን ብቻ ሳይሆን የአዴፓና የአብንንም ሆድ አደር ባለስልጣናት ፀረ ዐማራ ሰልፍ ማሳያ ነው። ለዐማራ ደግሞ ብቸኛ የመዳኛ አማራጩ ፋኖነት ብቻ ነው።
በመተከልና በወለጋ በዘር ማጥፋት ወንጀል በጅምላ ተፈጅተው በፈጣሪያቸው እርዳታ ከሞት የተረፉ ተፈናቃዮች እስከአሁን ድረስ በቂ ድጋፍና እርዳታ ሳይደረግላቸው እየተንገላቱ ይገኛሉ። በአንፃሩ ከሱዳን የመጡና አሶሳ የሰፈሩ ስደተኞች በውጪ ድርጅቶች ሳይቀር ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተደርጎ የኢትዮጵያ መንግሥትም ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ ይታወቃል። የሰው ልጅ ክቡር ስለሆነ የሱዳን ስደተኞች መደገፋቸው ጥሩ ሆኖ ሳለ በሰሜን ሸዋ፣ በወለጋ፣ በመተከል ወ ዘ ተ ተፈናቅለው በየመጠለያው ያሉት የዐማራ ልጆች ድጋፍ የማያገኙበት ምክንያት ዐማራ በመሆኑ የሚከፈል የግፍ ፅዋ እንደሆነ ልብ ልንለው ይገባል።
የኦሮሙማው መንግሥት ባዘዘውና ባወጀው ጦርነት የአማራና የአፋር ህዝብ እንደቅጠል ረግፏል። ሀብት ንብረቱ ወድሟል። ከትግራይ ወያኔ ጋር ድርድር ለማድረግ ከተፈለገ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን አፋርንና ዐማራን ያማከለ መሆን ይኖርበታል። አዋሳኙ አፋርና አማራ ያልመከረበት በጎን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሐሙስ፣ ነሃሴ ፭፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Aug. 11, 2022) ቅጽ ፱ ቁጥር ፯
2 www.moreshwegenie.org [email protected] ከወያኔ ጋር ድርድር የሚባል ነገር ካለ ይህ ድርድር የሽፍንፍን እርቅ ይሆናል። ስለዚህ ዐማራና አፋርን ያላማከለና የወልቃይትና የራያ ጉዳይ በአግባቡ እልባት ሳያገኝ፣ ቅንነት የጎደለው ሽምግልናም ሆነ እርቅ መረጋጋትና ሰላም እንዳይኖር ፈንጅ እንደማስቀመጥ ይቆጠራል። ስለዚህ መንግሥት የዚህ ሁሉ ጥቃት አድራጊና ተባባሪ አካል መሆኑ ታውቆ፤ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝምታውን እንዲሰብር ፣ ከአዲስ አበቤና ከዐማራ ህዝብ ጎን በመቆም የብልፅግና ሎሌ እንደ አዴፓ ያሉ ግልገል ብልፅግናዎችን ሳይተማመን በራሱ ቆሞ ታግሎ ራሱን ከኦሮሙማ አገዛዝና ከወያኔ ህገ መንግሥት ነፃ እንዲያወጣ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!