አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ!

እንደ ዋላ ውሀ እደጠማት
እንደራባት ጥም እንደያዛት

የሚያሳብቀው ገላዋ
ጎስቋላ ነው ስጋዋ

ይህቺ እማማ…..

አዲስ አቁማዳ ተሸክማ
አየኋት ማህሌት ቆማ

አዳዲስ ዜማ ስታዜም
ስትደረድር ስትገጥም

አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅልኝ
የወይን አረግ ጥመቅልኝ

እባክህ ውዴ ….

እንጀራዬን ልጋግረው ላስፋ
ፍለቅ እባክህ የኔ ተስፋ

ዳኘው ገበታየን
ጎብኘው ቃል ኪዳኔን

ብይኔን ክፈት ደጁን
የማይ መቅጃየን የምንጩን

ላጠጣ አብራኬን ላርካ
ልዘምርልህ እጄን እንካ

የምስጋና ነዶ ይዤ
እቅፍ ሙሉ አበባ አስይዤ

ከከፍታው ተራራ ላይ አወጣለሁ
ስእለቴን እከፍላለሁ

እያለች ማህሌት ይዛለችና
ክፈትላት እባክህ ራራና

አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅላት
ቆማለችና ተለመናት
እባክህን ፍለቅላት
ተገለጥማ እሺ በላት

እባክህን እባክህን
እባክህን እባክህን
እባክህን ብዬ ስልህ?

ሀምሌ፣ 2014

Geletaw Zeleke

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለሁሉም ጊዜ አለው! የዓባይ ትንቢቱ ሲፈጸም - በገ/ክርስቶስ ዓባይ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share