July 20, 2022
12 mins read

አማራ እየታደነ በመጨፍጨፍ ላይ ያለው በአማራነቱ ነው፡፡ የሚድነውም በአማራነቱ ብቻ ነው!!

ethiopia 90

በፊት በወያኔ አሁን ደግሞ በተረኛው ኦሮሙማ እየታደነ በመገደል ላይ ያለው አማራ ሰው ስለሆነ፣ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ፣ ቀይ ወይንም ጥቁር ወይንም ጠይም ስለሆነ አይደለም፡፡ ከሌሎች ተለይቶ የሚገደለው አማራ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡

ወያኔም ሆነ በተለያዩ ስሞች የሚንቀስቀሱት ተረኞቹ የኦሮሙማ ስብስቦች/ክፍልፋዮች አማራን የሚጠሉበት ዋና ምክንያት ምንድን ነው ተብሎ ቢጠየቅ መልሳቸው የሚሆነው የሚከተለው ነው፡፡  አማራ ጨቋኝ ነው፡፡ አማራ ገዝቶናል፡፤ አማራ ዘውዳዊ ነው፡፡ አማራ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ይላል፡፡ አማራ ይንቀናል፡፤ አማራ ያሰጋናል፡፡ አማራ ነፍጠኛ ነው፡፡ አማራ ሰፋሪ ነው፡፡ አማራ አበሻ ነው፡፡ ወዘተ ወዘተ የሚሉ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡

የማህበረሰብ ሳይንስ እንደሚያስረዳው ጥላቻ በመሰረቱ አንድም ከበታችነት ስሜት አለያም ከቅናትና ከምቀኝነት የሚመነጭ ባህርይ ነው፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ ጥላቻን ለበቀልና ጥላቻን ለማጥፊያነት መጠቀም ባልተገባም ነበር፡፡ ፍራቻ በጥላቻ ውስጥ ቁልፍ ቦታ አለው፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ሀቅ ነው፡፡

የወያኔና የኦሮሙማ ፖለቲከኞች ሁለቱም በአፋቸው እንጅ  ከልባቸው ኢትዮጵያ የምትባልን አገር እንወዳለን አይሉም፡፤ ለዚህም ግብራቸው በቂ ምስክር ነው፡፡ በአፋቸው ግን ይሸነግሉናል፡፤ በተለዬ መልኩ ኢትዮጵያ አትፈርስም እያለ በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ የኦሮሞ የባላይነትን ለማንገስ የሚቃትተውና በቅዠት አለም ውስጥ የሚዋኘው ኮሎኔል አብይ አህመድ አሊ በዚህ መሰሉ የአፍ ድለላና የፖለቲካ ቁማርተኛነቱ ወደር የለውም፡፡ በድምሩ ሲታዩ ሁለቱም ጸረ ኢትዮጵያ ናቸው፡፤ ሁለቱም ጸረ አንዲነት ናቸው፡፤ ሁለቱም ጸረ ህዝብም ናቸው፡፤ እንወክለዋለን የሚሉትን ሰፊውን የትግራይና የኦሮሞ ህዝብ እንኳን አይወክሉም፡፤ ግን የአገሪቱን ቁልፍ ስልጣን ለመያዝ ችለው የፈለጉትን አድርገዋል፡፡አሁንም እያደረጉ ነው፡፡

ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብለን ብንጠይቅ አሁንም መልሱ እነዚህ ሀይሎች አማራን ለምን ይጠሉታል እንደሚለው ጥያቄ መልሱ ከዘር ግንድ እንደሚጎተት አረግ ነው የሚሆነው፡፡

የአሁኑ ትውልድ ለሁለቱም ጥያቄወች የራሱን የግምት መልስ ከራሱ የዘር አቁማዳ እየተረተረ ሊሰጥ ይችላል፡፤ ያም በዘር ላይ የተመሰረተ እንቶ ፈንቶ ነው የሚሆነው ፡፡ ታሪክን፣ እውነትን፣ መረጃንና ማስረጃን ይዘው ሊያሳምን የሚችል መልስ የሚያቀርቡ ካሉ በቁጥር በጣም ትንሾች ናቸው፡፡ እነዚያም ስህተትና ምቀኝነት፣ ተረኝነትና ዘረኝነት ባጎበጠው አብዛኛው ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ ስለዚህ ይህንን ሁኔታ እንፍታው ካልን መጀመሪያ ታሪክንና የሆነውን በሙሉ ከእነ ምክንያቶቹ በትክክል አጥርቶ ማወቅ፣ ለዚሁም ፈቃደኛና ዝግጁ መሆንና እውነቱን ወይንም የእውነቱን ግማሽ ጠቃሚ ጎን ለመቀበል ራስን ማዘጋጀት ግድ ይላል፡፤ ይህ በቅርቡ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ጭላንጭልም አይታይም፡፤ አሁን ላይ ቆመን ስናየው በፖለቲካው ውስጥ (በህዝቡ ውስጥ አላልኩም) ሸረኝነትና አጎብዳጅነት የተወራረሱበትና የፖለቲካ ሱሰኝነት ያናወዘው ይበዛል፡፡ ከዚህ ውጭ አንዱ ወደ ግራ አንዱ ወደቀኝ ሲያስብና በዚሁ ላይ የሴራና የዘር ፖለቲከኞች መሻታቸውን ሲያክሉበት የሚያስማማ ነገር ላይ መድረስ ያቅትና ያው በድፍርሱ መዋኝቱ ይቀጥላል ማለት ነው፡፤

ይህ ሁኔታ ጥርት ብሎ የአስተሳሰብ እድገቱ ተለውጦ ሁሉም ሀቁን እስከሚረዳና በተለይም ምሱን እስከሚያገኝና እንደዚሁም  ለግብረመልሱ ዝግጁ ሆኖ እስከሚቀርብ ድረስ የአማራው ሞት አያባራም፡፤ ምክንያቱም ልከ እንደኦሮሞውና እንደትግሬው የአማራውን ጥቅምና መብት ሊያስከብር የሚችል ትክክለኛ የአማራ ወኪል ስለሌለ ነው፡፡

የአማራ የፖለቲካ መሪወች ናቸው የተባሉት ታሪካቸውና ግብራቸው ሲፈተሽ ለአማራው ሞትም አልቂትም መደንዝና መፍዘዝም ዋና ተጠያወቹ እነርሱ ናቸው፡፡ አለንልህ እያሉ በግፍ አስጨፈጨፉት፡፡ ለአለቆቻቸው አጎብብደው በአማራው ሞት ከሚሳለቁበት ጋር ጨፈሩበት፡፡

አሁን አማራው የትም መሄድ አይችልም፡፡ በራሱ በሁለት እግሮቹ ቆሞ መወራጨትና አፈር ልሶ መነሳት ብቻ ነው ያለበት፡፤ እምቢ ብሎ ገድሎ መሞትን ለወንድሙ ላልተገደለው አማራ ማሳየት አለበት፡፡ ይህም ማለት አማራነቱ እንዳስገደለው ሁሉ አማራነቱ ከሞት እንደሚያድነው አምኖ አንዲነቱን ፣ አማራነቱን ፣ ነፍጠኛነቱን ማጥበቅ መናበብና ከገዳዮቹ ጋር መተናነቅ አለበት፡፤ ያኔ ብቻ ነው እየታደነ መሞት ሊቆምለት የሚችለው፡፡ ይህም በአማራ አባባል ሆኖ መገኘት ተብሎ የሚታወቀው አባባል ነው፡፡

ለዚህም አተገባበር ከታሪክ አኳያ የአማራ ህዝብ ከረዥም አመታት ደማቅና አንጸባራቂ ታሪኮቹ የፈጣን አደረጃጀትና የንቁ አሰላለፍ በቂ ተሞክሮና ልምድ አለው፡፡ ስለሆነም አሁንም ለአማራ ህዝብ አሁን ጊዜው የጠላት ጊዜ ስለሆነ የሚከተሉትን እርምጃወች በፍጥነት መውሰድና በተግባር ላይ ማዋል ለአማራ ህልውና መረጋገጥ እጅጉን ወሳኝ ናቸው፡፡

እርምጃ ቁጥር አንድ፦

በየአካባቢው ሆነው የሚያስገድሉትን ሆዳም አማራወችን መለየት፡፡ ማስጠንቀቅ፡፡ እምቢ ብለው ለጠላት ባደሩ የአማራ ሹመኞች ላይ አስተማሪ ሊሆን የሚችል የማያወላውል እርምጃ መውሰድ፡፡

እርምጃ ቁጥር ሁለት፦

በፋኖ ዙሪያ መሰባሰብና በፍጥነትም በየሰፈሩና በየነጥብ ጣቢያው መደራጀት፡፤ ሰንሰለቱንም ከውስጥ ሰርጎ ገቦችና ውጫዊ የአማራ ጠላቶች  በንቃት ጠብቆ  መገኘት፡፡ ከዚያም ፋኖንና ለህዝብ የወገኑ የአማራ ልዩ ሀይሎችን ለማጥፋት የተሰማራውን ሀይል መቀልበስና ብሎም ክልሉን ነጻ ማድረግ፡፡

እርምጃ ቁጥር ሶስት፦

ክልሉ ነጻ ከማድረግ ጎን ለጎን  የክልሉን ህዝብ  በወቅታዊ ሁኔታወችና አሰላለፎች ላይ ህዝቡ እንዴት አድርጎ ህልውናውን ሊያስጠብቅ እንደሚችል ህዝቡን ማንቃት፡፡ ማደራጀትና ህዝቡን ለጊዜውም ቢሆን በጎበዝ አለቃ ማስተዳደር፡፤ በፖለቲካ ውስጥ ቋሚ ጥቅም እንጅ ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ እንደሌለ በማመን ለአማራ ህዝብ ቆይቶም ለኢትዮጵያ ሊጠቅም የሚችል ግንኙነትን ሊፈጥሩና ሊያሳድጉ ከሚችሉ የውጭና የውስጥ ሀይሎች ጋር ተገቢውን በእኩልነትና ሰጥቶ በመቀበል ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን መፍጠር፡፡ ይህንኑ ማጠናከርና ከዚሁም መጠቀም መቻል፡፡

እነዚህን ጉዳዮች አማራው በቶሎ ከተገበራቸው በአማራነቱ እየተለየ መጨፍጨፉ ይቆምና በአማራነቱ ከእልቂት መዳኑ ያለጥርጥር ይመጣል፡፤ ቀስ በቀስም ክሌሎች መሰል ኢትዮጵያዊነትና አንዲነት ከሚሰማቸው ሀይሎች ጋር በጋራ አገሪቱን ነጻ ማድረግ ይችላል፡፡ ይህንን ካላደረገና በእውንም “”አማራ”” ሆኖ በተግባር ካልተገኘ እልቂቱ ይቀጥላል፡፤ መቆሚያም የለውም፡፤

ስለዚህ ውድ የአማራ ልጅ ሆይ፦

አንድ ሆነህና በአስቸኳይ ዛሬዉኑ በያለህበት በየጎበዝ አለቃህ እየተደራጀህ ከፋኖ ጎን ቁም፡፤ ጠላቶችህንም መክተህ መልሳቸው፡፤ ክልልህንም አጽዳ፡፤ የክልሉ ከሆዳሞች መጽዳት የጨዋታው መቀየሪያ ዋና ካርድ ነው፡፡ ከዚያም ለሌሎች ከክልልህ ውጭ ላሉት አማራወች የመዳኛ ቤዛቸው ትሆናለህ፡፡

ይህንን እመንም እወቅም፡፡ ራስህን ካዳንክ በኋላ ብቻ ነው አገርህን ልትታደግ የምትችለው፡፡

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop