የአማራው ጩኸት (አንዱ ዓለም ተፈራ)

ማክሰኞ፡ ሐምሌ ፲ ፪ ቀን፣ ፳ ፻ ፲ ፬ ዓ. ም.

አብዛኛዎቻችን ስለአገራችን ኢትዮጵያ ስናስብ፤ ለረጅም ዘመን ከፍተኛውን መስዋዕትነት ከፍለው፣ አስቃቂና ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፈው፣ ለራሳቸው ሳይሆን ለኛ ለመጪዎቹ ያደረጉት ተጋድሎ ከፊታችን ይደቀናል። ለዘመናት ከቀን ሐሩርና ከሌሊት ብርድ፣ ከእርሻ ልፋትና ከንግድ እንግልት ጋር በመጋፈጥ፤ እኛን እኛ ያደረጉበትን ሂደት ስናስብ፤ በትጋታቸው እንመሠጣለን። በዚህ መሐል ለወደፊቶቹ ያለብን ኃላፊነት፤ ሕልውናችንን ፈርጥሞ ይወረዋል። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊነታችን ስንኮራና ትናንት አለን ስንል ትርጉም የሚኖረው፤ እኛ የትናንቶቹን ለነገዎቹ ስንሆን ነው። በጥቅሉ፤ አንድ ራሳችንን ችለን የቆምን ግለሰቦች ብቻ ሳንሆን፤ በትናንቶቹ የተቀፈቀፍንና የነገዎቹ ሕልውና በጭብጣችን ያለ መሆኑ፤ ከራሳችን ውጪ የድምር ኃላፊነቱ አዕምሯችንን ይገዛዋል። አገራችን ኢትዮጵያን ከሕልውናችን ጋር አስተሳስረን የያዝን ብዙዎች ነን። የመኪና መንገድ በማይገባበት የእርሻው መሬት ጋር ከሚታገለው አርሶ አደር አንስቶ እስከ በውጪ አገር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የኢንዱስትሪ ዘርፎች አንቀሳቃሾች ድረስ ያለነው ኢትዮጵያዊያን፤ ኢትዮጵያን በልባችን ይዘን ነው ውለን የምናድረው። የኢትዮጵያ አንድ አገር ሆኖ መቀጠል፤ ባጠቃላይ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ በተለይ ደግሞ በሥልጣን ላይ ላሉት የበለጠ ይጠቅማል። ይሄ ግልጥ ስለሆነ፤ ማብራሪያ አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ አንድ አገር ሆና የመቀጠሏ መረጋገጥ፤ ለጎረቤት አገሮችና ብሎም ለአፍሪካ አገሮች ሰላምና መረጋጋትን ሲያስከትል፤ ለዓለም በሙሉ የዕድገት ሂደትን ይጠቁማል። የአገራችንን የኑሮ ሀቅ ስንመለከት፤ ግለኝነት በጣም ነግሦ፣ አገር አቀፍ ግንዝቤና እሳቤ ደብዝዞ፣ የነገ እውነታን መሪ ራዕይ ጠፍቶ፣ ወደ አንድነትና ብልፅግና ሳይሆን ወደ አዘቅት ሩጫ የተያያዝንበት ነው። የግለሰቦች ሕግንና ደንብን ባልተከተለና ባመቻቸው መንገድ ሁሉ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ማሰደድ፤ ለአገር ዕድገትና ለዴሞክራሲ መንሰራፋት መሠረት የሚሆነውን የመካከለኛ ገቢ ባለቤት የኅብረተሰብ ክፍል ለማጎልበት አይረዳም። በተለይም በአገር ውስጥ ምርታማነት ሳይኖር በብልጣብልጥነት የርስ በርስ መነጣጠቅና ያየር ባየር ስምሪት የመንጠላጠያ መሰላል፤ ይሄ ክፍል አያድግም። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ጠባብ አጀንዳ የያዙ አራጋቢ የፖለቲካ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፤ በሕዝቡ ጉስቁልና የራሳቸውን የግብ ግፊት ማጋጋል ይዘዋል። በዚህ ሁሉ መሐል፤ አማራው በያለበት እየተጨረሰ ነው። የት ላይ ነው ያለነው! በዚች አጭር ጽሑፍ ላነሳ የፈለግሁት የአማራውን ጩኸት ነው።

መነሻ

ያለንበትን የፖለቲካ ሀቅ ስንመለከት፤ ድሮም ሆነ ዛሬ የአማራው መኖሪያ መላ ኢትዮጵያ ነው። አማራው እየተጠቃ ያለው በመላ ኢትዮጵያ ነው። አማራው እየተጨረሰ ነው። የፌዴራል መንግሥት አለ። አሁን ላለው ችግር ሁሉ መንስዔ የሆነው ሕገ-መንግሥት አሁንም በሥራ ላይ ነው። የኦሮሞ ክልል መንግሥት፤ አማራው እንዲጠቃ መንገድ ከፍቷል። የአማራው ክልል መንግሥት የአማራው ወኪል ሳይሆን፤ ለአማራው መጠቃት ለበቅ አቀባይ ሆኗል። አማራጭ ሆኖ የአማራን ጉዳይ ይዞ የቆመ ሌላ ጠንካራ የተደራጀ ኃይል የለም። አገሪቱ አገር ሆና እንዳትቀጥል፤ በውስጥና በውጪ በብዙ በኩል ተዘምቶባታል። አማራውን እናድን ስንል፤ በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አማራ ነው። ታዲያ፤ አማራው እንዴት ይድናል?

ቁም ነገር

የአማራውን መዳን እና የሕልውናውን መቀጠል ለማስተማመን፤ ጠለቅ ያለ ግንዛቤና ሁላችንን የሚያቅፍ ራዕይ ያስፈልጋል። በድረገጾች በሚወጡ ጦማሮች፣ በውጪ አገሮች በሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችና ጊዜውን ተመልክተው በሚረቀቁ መፈክሮች፤ በደልን ከመግለጥ ውጪ፤ መፍትሔ ለማምጣት በቂ አይደለም። ታዲያ ምን ይሻላል! አማራው የሚድነው፤

አንዲት ኢትዮጵያ ኖራ፤ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ የፖለቲካ ተሳትፎ የምናደርግበት ስርዓት ሲኖር

አማራው፤ በቀሪው ኢትዮጵያ ክልሎች ብቻ ሳይሆን፤ ለሱ በተመደበለትም ክልል ተቆርቋሪ አጥቷል። ባሁኑ ሰዓት፤ እንደሚታወቀው፤ አማራው ያልተወከለበት ስርዓት ነው ያለው። ሕገ-መንግሥቱን ከማርቀቅና ማጽደቅ ጀምሮ እስከ አገሪቱን በክልል ማዋቀር ድረስ፤ አማራው እንዳይወከል ተደርጓል። ሕገ-መንግሥቱ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርን መሪዎችን ፍላጎት ብቻ የያዘ ነበር። በተጨማሪ ሕገ-መንግሥቱ የጎደለው፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነትና ፍላጎት በትክክል አለመያዙ ብቻ ሳይሆን፤ ሀቀኛና ለሀቅ የቆሙ ሰዎች በሕጉ ዙሪያ አለመኖራቸው ጭምር ነው። ያለ ሀቀኛ ሰዎች፤ ትክክለኛ ሕገ-መንግሥትም ቢኖር ጉልበት የለውም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ

በወቅቱ አማራውን ወክለው የነበሩት፤ ስኳር ሰርቆ እስር ቤት የገባው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ትግሬ ሆኖ አማራን ወክሎ አሁን እስር ቤት የሚገኘው መሪ፣ ኤርትራዊ ሆኖ አማራን ወክሎ የነበረው አሁን እስር ቤት የሚገኘው ሁሉን አውቃለሁ ባይ መሪ፣ በራሳቸው የክልል አባልነት መመዘኛ እንኳን ከሞላ ጎደል ሁሉም አማራና የአማራ ተቆርቋሪዎች ያልሆኑ ነበሩ። እኒህ ተወካዮች፤ የፖለቲካ አጀንዳቸው አማራ ያልነበረ፣ ለአማራው ችግር መፍትሄ ማስገኘት ሳይሆን ለትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የአሽከርነት ሚና ለመጫወት የተጎለቱ፤ ነበሩ። አማራ ከዚህ ሁሉ ተላቆ መኖር የሚችለው፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አና እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ባገራቸው የፖለቲካ ሂደት የሚሳተፉበት ስርዓት ሲኖርና ሕገ-መንግሥቱም ይሄንን ሲያንጸባርቅ ነው። በዚህ ስሌት፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያስቀመጠው ሕገ-መንግሥትና የአስተዳደር መዋቅር መፍረሱ ግድ ይሆናል። በቦታውም ኢትዮጵያዊያንን በግለሰብ ደረጃ፣ መብታቸውን እና ኃላፊነታቸውን በትክክል የሚያስቀምጥ ሕገ-መንግሥት ይሰፍራል። ያ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ በመላ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነታቸው ይኖራሉ። ይህ ዘለቄታ ያለውና ትክክለኛ መፍትሔ ነው። ይሄ በልመና ወይንም ቁጭ ብሎ በመጠበቅ የሚገኝ ሥጦታ አይደለም። ዛሬ ይሄ ይሆናል ብዬ ሳይሆን፤ መሠረታዊ መፍትሔነቱን ለመጠቆም ነው እዚህ ላይ ያሥቀመጥኩት።

ወይንም

   ደሌሎቹ ክልሎች ሁሉ፤ አማራ የራሱ ተወካዮች ኖረውት፤ በትክክል በፌዴራሉ መንግሥት ሲሳተፍ ነው

ይሄ ሁለተኛው አማራጭ ሁለት ችግሮች አሉት። ወደ ችግሮቹ ከማለፌ በፊት ግን፤ ይሄ የፖለቲካ ዕውነታ በአማራው ጫንቃ ላይ የተጫነ ሀቅ በመሆኑ፤ ይሄን አማራጭ ወስዶ መመርመሩ ግዴታዬ ነው። እናም በዚህ ልጀምር።

አሁንም በድጋሚ፤ አማራው በቀሪው ኢትዮጵያ ክልሎች ብቻ ሳይሆን፤ ለሱ በተመደበለትም ክልልም ተቆርቋሪ አጥቷል። በቀሪው ኢትዮጵያ ክልሎች ያለው አማራማ፤ እየደረሰበት ላለው እልቂት ሊያድነው የሚችል ቀርቶ፤ ዝርዝር በደሉን በትክክል የሚመዘግብለት የተደራጀ የፌዴራሉም ሆነ የአማራ አካል የለም። የአገራችን የመከላከያ ሠራዊት የፖለቲካ ጉዳይ አስፈጻሚ ስለተደረገ፤ ለአማራው መዳን፤ ደንታ እንዳይኖረው እጅ እግሩ ታስሯል። የአማራ ኃይልም ሆነ ፋኖ፤ በቦታው ደርሰው እንዲያድኑት፤ የመንግሥት ፈቃድም ሆነ ፍላጎት የለም። እናም ተቀፍድደው የተያዙ ናቸው። ታዲያ ምን ይከተል?

አማራው መጀመሪያ ወዳጆቹን እና ጠላቶቹ ለይቶና አጥብቦ ማስቀመጥ አለበት። በዚህ ሂደት፤ ዋናና ዘላቂ የሆነውን፤ ከጊዜያዊ ጠላቶቹ ነጥሎ ማስቀመጥ አለበት። እናም ትኩረቱን ከዋናውና ዘላቂ ጠላቱ ላይ አድርጎ፤ ጊዜያዊ ጠላቶቹን ለጊዜው ወደ ጎን ይበል። መዘንጋት የሌለበት፤ የአማራው የትግል ውጤት፤ በሁለት ምርኩዞች የቆመ መሆኑን ነው። በአማራው ጥንካሬና በጠላቶቹ ድክመት! ወደ ዝርዝሩ ልግባ።

የአማራው የአሁንና የወደፊት ግቦቹ ተለይተው በአግባባቸው ሊያዙ ይገባል። ጊዜያዊ ግቦቹ በምንም መንገድ የዘለቄታ ግቦቹን ሊጎዱ አይገባም። ምኞትንና ሊያደርጉ የሚችሉትን ለይቶ ማወቅ መነሻ ነው። የምንመኘውን ማግኘት ብንፈልግም፤ ልናገኘው የምንችለው በጥንካሬያችን መጠን ብቻ ነው። በፖለቲካ ዓለም፤ በልግስና የሚገኝ አንድም ነገር የለም። ሌሎቹ አዝነው ወይንም ለጋስ ሆነው የሚሠጡት ምንም ነገር የለም። ለዚህም ነው ትግሉ ያስፈለገው። በዚህ ትግል፤ ማንኛውም ግለሰብ፤ በሚመቸውና በሚመርጠው መንገድ አስተዋፅዖ ማድረጉ አስፈላጊ ነው። “በዚህ መንገድ ብቻ ነው ትግሉ የሚካሄደው!” አይባልም። ግቡ የሚሳካው፤ ዘርፈ ብዙ በሆኑ የትግል መስመሮች ነው። እናም ሌሎች የሚያደርጉትን አስተዋፅዖ ማስተናገድና ማቀናጀት እንጂ፤ መንቀፍ አይገባም። የተገኘን ውጤት ቢያስተውሉ፤ የተጀመረው በትንሹ መሆኑን ይገነዘቧል። እዚህ ላይ፤ የራስን አቅም አግንኖና የጠላትን አቅም አኮስሦ ማየት ለውድቀት መዘጋጀት ነው። በአንጻሩ ደግሞ፤ የራስን ድክመት አግዝፎና የጠላትን ጥንካሬ አግንኖ መመልከት፤ ላለመታገል ምክንያት መደርደር ነው።

በአሁን ሰዓት እየተደረገ ያለው የአማራው በየቦታው መሳደድና መገደል፤ የግድ መሆን ያለበት ክንውን አይደለም። ይህ፤ አማራውን ከፖለቲካ ውጪ ለማድረግ ሆን ተብሎ ታቅዶ እየተሠራበት ያለ፤ የጥቂት ሥልጣን ፈላጊዎች ግልጥ ተግባር ነው። ይህ፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ መመሥረት ጀምሮ፤ በተንኮል የተከናወነ ሴራ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዛሬ ሌላ ቀን ነው!! - አንድነት ይበልጣል - ሐዋሳ

አማራው እንዲድን፤ የአማራው ጥረት ብቻ ሳይሆን፤ ይሄንን የተከበረ ኢትዮጵያዊ ተልዕኮ፤ “ለዚህ ነው የቆምኩት!” ብሎ የሚወስድ የአማራ ክልል መንግሥት፣ “ይሄ የኔ ተግባር ነው!” የሚል የፌዴራል መንግሥት፣ ሌሎች ክልሎችን የሚመሩ ባለሥልጣናት ጥረትንና የብዙኀኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በትብብር አብሮ መቆምን ይጠይቃል። በርግጥ ባለንበት የፖለቲካ ሀቅ፤ ይሄ ይሆናል ብሎ መጠበቁ አይደለም፤ ማመኑም አስቸጋሪ ነው። በዚህ አስሸጋሪነቱም ነው! የዚህ ጉዳይ ባለቤቶች አጥብቀን መሥራት ያለብን። ይሄን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ አድርገን ካስቀመጥነው፤ አኙዋኩ ይሁን አፋሩ፣ ሲዳማው ይሁን ሶማሌው፣ ወላይታው ይሁን አዲስ አበቤው፣ አደሬው ይሁን ጉጂው፣ ኦሮሞው ይሁን ትግሬው፤ “ነግ በኔ!” ነውና ለራሱ ሕልውና በማሰብ ይተባበራል። የአማራው መዳን በዚህ ላይ የቆመ ነው። በርግጥ የኦሮሞ ክልል መሪ ሽመልስ አብዲሳ ይሄንን ይቀበላል ብዬ፤ በልቤ ቦታ አልሠጥም። ነገር ግን፤ እሱ እየተቃወመም ቢሆን ይሄ ይተገበራል! የሚል ፅኑ እምነት አለኝ። እሱ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አይበልጥም። በአገራችን ላይ ነግሦ ያለው፤ “አንዱ እንዲጠቀም ሌላው መጎዳት አለበት!” የሚለው አባዜ፤ ጥልቅ ጉድጓድ ተምሶ መቀበር አለበት። መልሶ እንዳይነሳ፤ ጥርብ ድንጋይ በላይ ላይ መጫን አለበት። የአማራውን የሕልውና ትግል አስመልክቶ፤ ግንዛቤያችን ጠለቅ ያለ ይሁን።

የአማራ ክልል አስተዳደርን፣ የሌሎች ክልሎች አስተዳደሮችን፣ የፌዴራል መንግሥቱን እና የተለያየ ኩል የተቀባውን ኦነግ ባንድ ላይ ደርቦ ዋና ጠላት ማድረግ፤ አዋጪ መንገድ አይደለም። ሁሉም አማራን እየጎዱ ያሉ ቢሆኑም፤ ዘላቂውና ዋናው የአማራ ጠላት፤ በመጨረሻ ላይ የተቀመጠው ነው። የአማራው የሕልውና ትግል ከዚህ ይነሳ። ጊዜያዊ ወዳጅን ማብዛት ለሂደት ይረዳል። በፖለቲካ ሂደት፤ ጊዜያዊ ጠላት ቆይቶ ወዳጅ የሚሆንበት ሁኔታ አለ። እናም ጊዜያዊ ብሎ ያስቀመጣቸውን ጠላቶቹን ማስተናገድ የሚገባው በጥንቃቄ ነው። ምኞቱ እኒህን ወደ ወዳጅነት ለመቀየር ነው። የትግል ስልት የሚጀምረው፤ ወዳጅን አብዝቶ ጠላትን በቁጥር አነስተኛ በማድረግ ነው። ይህ ኃይልን ያበዛል፤ የጠላትን ሰፈር ያዳክማል። የፌዴራል መንግሥቱን ከወዳጅ ወገን ማስለፍ አለብን። ራሳችን የፌዴራል መንግሥቱ አካል ነን! ይሄ መታወቅ አለበት! የኛው ጥረት ይሄን ማረጋገጥ አለበት። በሂደቱ የፌዴራል መንግሥቱ ቢያንስ ከጠላትነት ይልቅ፤ አንጻራዊ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖረው ማድረግ ይቻላል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ አሁን በኦሮሚያ ክልል ያለው አስተዳደር ያለ ምንም ማቆላመጫ ከኦነግ ጋር አብሮ፤ አማራን እያስጠቃ ነው። ሆኖም፤ ሕጋዊ አካልነት ያለውና የሚወክለው ወገን ስላለ፤ ይሄንንም ከጠላት ወገን ማሰለፉ ለአማራው አይረዳም። ይሄን የክልል አስተዳደር፤ ከኦነግ ትሥሥሩ አላቆ፤ ድጋፉን እንዲነሳው ለማድረግ መጣር፤ የትግሉ አካል ነው።

አሁን በተያዘው የፖለቲካ ሂደት፤ ጠንካራ የአማራነት ስሜትና የተደራጀ የአማራ የፖለቲካ ኃይል መኖሩ፤ ለራሱ ሕልውናና ለኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል ወሳኝ ነው። ይሄ፤ በያንዳንዱ አማራ አእምሮ ማደግ አለበት። መንግሥት ኃላፊነቱን መወጣት ሲሳነው ወይንም ሳይፈልግ ሲቀር፤ አማራው ራሱን ለማዳን የግድ የራሱ ድርጅት ፈጥሮ መከላከል አለበት። የፋኖ ሕልውና ከዚህ ይመነጫል። ነገር ግን፤ አሁን ባለንበት የፖለቲካ እውነታ፤ ፋኖ ተቀፍድዶ የተያዘና አደጋ ያለበት ኃይል ነው። የፌዴራሉ መንግሥት በምንም መልኩ ፋኖን አይቀበልም። አማራ ደግሞ፤ እንኳንስ ያለ ፋኖ፤ አሁንም ፋኖ እያለ ሕልውናው አደጋ ላይ ነው። በርግጥ የአማራው ክልል አስተዳደር፤ የአማራ ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ፤ ፋኖ ዓላማውን ሳይስት፤ በመንግሥት መዋቅር ገብቶ፤ ሕግን የሚያስከብርና የአማራ ኃይል አካል በሆነ ነበር። ፋኖ የመፎካከሪያ ጉዳይ ሆኗል። ተፎካካሪዎቹ ደግሞ፤ አማራውና በአማራው ክልል ያለው አስተዳደር ናቸው። ይህ፤ የፌዴራሉና የአማራ የብልፅግና መሪዎች መሰሪ ቅመራ ነው።

መድረሻ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውስጥ ጣልቃ የመግባት ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ መሰረት የለውም!!! - መሰረት

የዚህ የሁለተኛው ምርጫ ችግሮችን እንመልከት። አማራነትን የፖለቲካ ማንነት ያደረገው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነው። ትግሬነትን፣ ኦሮሞነትን፣ ሶማሌነትን፣ አፋርነትን፣ ደቡብ ኢትዮጵያዊነትን፣ ቤንሻንጉልነትን፣ አዲስ አበቤነትን፣ ጋምቤላነትን የፖለቲካ ማንነት ያደረገው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነው። ይሄን ክስተት ደግሞ አሁን ያለው ገዥው ብልፅግና ፓርቲ “የኔ!” ብሎ ይዞታል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በጊዜው ይሄን ያደረገው፤ ጠላት ፈጥሮ ትግሬዎችን ለማሰባሰብና ድርጅቱን ለማጠናከር ነበር። ወደድንም ጠላንም ይህ፤ ላለፉት አርባ ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ የተቆጣጠረ እውነታ ነው። ይህ የፖለቲካ እውነታ፤ አገራችንን ወደ አዘቅት ከመውሰድ ያለፈ፤ ዘለቄታ የሆነ ፍትኅ፣ ሰላምና ለአገራችን ብልፅግና አያስገኝም። አማራው ባሁኑ ሰዓት አማራጭ አጥቶ ይሄንን ሀቅ ለመቋቋም፤ የራሱ የሆነ የአማራ ፖለቲካ ሂደት ቢከተልም፤ አደጋውን መጠቆሙ ግዴታዬ ነው።

ይህ የክልል የፖለቲካ ሂደት ከላይ የጠቆምኳቸው ሁለት ችግሮች አሉት። የመጀመሪያው ዘለቄታነት የሌለው መሆኑ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ሰላም፣ ፍትኅና እኩልነትን የማያስገኝ መሆኑ ነው። አሁን ያለው ስርዓትና አካሂያዱ፤ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ወደ ጎጡ እንዲሸጎጥ አድርጓል። እናም የበለጠ ብሔርተኛ ለመሆንና ለመባል፤ የአክራሪነት እሽቅድድምና ሌሎችን ጠላት አድርጎ መፈረጅና ማጥቃት፤ የፖለቲካ ሂደቱ አካል ሆኗል። አሁን ላለንበት የፖለቲካ ሀቅ መነሻና መድረሻው ይሄው ነው። የዘራነውን እንጂ፤ ጊዜው የሚፈቅደውንና የምንፈልገውን አናጭድም! እንዲህ በተከፋፈለ አስተዳደር፤ ከመካከላቸው የግድ አንድ የበላይ ወገንተኛ ገዥ መኖሩ አይታበል ሀቅ ነው። ትናንት የትግሬዎች ገዥዎች ነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የኦሮሞዎች ገዥዎች ናቸው። ይህን በግልጥ ማስቀመጥ፤ ያለውን ሀቅ በትክክል ለመረዳት ይረዳል። በዚህ ገዥ ሥር ሆኖ ማን ይኖራል!

ሌላው ፍትኅንና ሰላምን ይመለከታል። ሁሌም አንድ ገዥ እያለ፣ ሁሌም ተቀጥላ ሆኖ መኖር እያለ፣ ሁሌም የቁጥር ጉዳይ ሆኖ እያለ፤ እንዴት ብሎ ነው እኩልነት የሚሰበከው? መነሻና መድረሻው በፓርቲው ውስጥ ባለው ተወካይ ቁጥር ከሆነ፤ እንዴት ብሎ ነው እኩልነት የሚኖረው? ማንስ ነው ጉልበት ኖሮት በመንግሥቱ መዋቅር ውስጥ የራሱን ሰዎች ሊሰገስግ የሚችል? እያንዳንዱ ክልልስ ይሄን ማድረግ ካልቻለ፤ እኩልነት አለ ወይ? እኩልነት ከሌለስ እንዴት ያለ የፌዴራል መንግሥት ይኖራል? በፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ ማነው ሁልጊዜ የበላይነቱን ይዞ የሚቀመጠው? ይህ ነው አደጋው። ሆኖም አማራው ራሱን ማዳን ስላለበት፤ ይሄን ሀቅ አውቆ፤ ራዕዩን ነድፎ ወደፊት መቀጠል አለበት።

የጥላቻ ፖለቲካ

በአገራችን የነገሠው የጥላቻ ፖለቲካ ምን ያህል ሥር እንደሠደደ ላሳያችሁ። ደቡብ ካሊፎርንያ የምትገኘዋን እህቴን ልጠይቅ ሎስ ኤንጀለስ ሄድኩ። ክሬንሾው የገበያ አዳራሽ በሚገኝ አንድ የመንገድ የኤሌክትሪክ ገንዳ ግድግድ ላይ፤ አንድ ኢትዮጵያዊ፤ ያለ ከተማውና አካባቢ ነዋሪው ተቃውሞ፤ መላ ጥቁሮችን አኩሪ የሆኑትንና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩትን የአፄ ሚኒሊክን ገጽ፤ ከአረንጓዴ ብጫና ቀይ ቀለም ሰንደቅ ዓላማችን ፊት ለፊት አሳምሮ ስሎታል። ያየው ሁሉ እያደነቀው ያልፋል። ሰዓሊው ዮናስ ኃይሌ የሚኖረው በአካባቢው ነው። ዮናስ ይሄንን ያደረገው ያለ ማንም ድጋፍ ነው። ከኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆነ ከአካባቢው ኢትዮጵያዊ ኅብረተሰብ ድጋፍ አልነበረውም። በንጹህ አገር ወዳድነትና በራሱ አነሳሽነት ያደረገው በጎ ተግባር ነው። ተመልከቱት፤ በግራ በኩል የምታዩት ዮናስ የሳለው ነው። ጥላቻ ፖለቲካን ጠንሳሽና አስፋፊው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት በቀኝ ያለውን እንደምታዩት ስዕሉን አጎደፉት።

ይሄ ምን ይባላል! አሜሪካ ውስጥ! ሎስ ኤንጀለስ ከተማ! ይሄን የመሰለ ድንቅ ሥራ መሞገስ ባለበትና ሰዓሊውን በአኩሪ ተግባሩ መመስገን በነበረበት ሁኔታ፤ ካገራችን ውጪ በሰው አገርም ጥላቻን የትግል መሳሪያ አደረጉት!

ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ያለ ጥቃት እየደረሰበት ነው። የአማራ ጥላቻ በከፍተኛ ደረጃ ነግሷል። በዚህ ሀቅ አማራ ራሱን ማዳንና በሂደቱም ኢትዮጵያን ማዳን አለበት። የአማራ መዳን፤ በራሱ በአማራው ጫንቃ ላይ ነው የወደቀው! አማራ በያለበት ይሄን ተረድቶ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት።

2 Comments

 1. ውድ አዘጋጅ
  በቁጥር ሁለት፤ እንደሌሎቹ የሚለው ተቆርጧል
  የአፄ ሚኒሊክን ሁለት ስዕሎች አላስገባኸውም

 2. Selam! Selam!

  One Shegitu Dadi, a very forward looking Oromo woman has the following to say on confederation. I’m copying and pasting her write-up without her authorization hoping that she’ll not mind.

  “Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

  Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

  Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

  As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

  So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

  The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

  In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

  Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

  Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

  It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

  Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

  Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

  For us, Oromos, conederation is also the answer. ”

  GREAT!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share