July 9, 2022
9 mins read

ትንሽ  መናገር በትግስት ብዙ መስማት ይችሉ ይሆን? (ከጥሩነህ)

 ጠ/ሚሩ የማይገናኙ ነገሮችን በማገናኘት የህዝቡን የማገናዘብ ብቃት ሲሳደቡ ከማየት በላይ ምን ያሳፍራል:
Abiy Ahmed Shine OLF 1

Abiy Ahmed Shine OLF 1የተናገሩትን መልሶ መዋጥ አይቻልም: በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ ንግግር ደግሞ የቃሉን ባዶነት ብቻ ሳይሆን ተናጋሪውንም ያቀላል:  ከዚያም በሁዋላ የሚናገራቸውም የሚያደርጋቸውም ሁሉ ገለባ ይሆናሉ: በተለይ ከአንድ የሃገር መሪ ምላስ የሚወጡ ቃላቶች እውነትና ንፁህ መሆን አለባቸው:  ከመቶ  ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ፊትለፊት ሲነገሩ  ደግሞ እውነተኝነታቸው ተደጋግሞ መጣራት አለባቸው: በጎ ቃላት ተናጋሪውን  ከፍ እንደሚያደርጉ ሁሉ በውሸት  የታጀሉ ቃላት ደግሞ ትልቁን  ያሳንሳሉ፣ ያቀላሉ: በሰዎች ትዝብት ተናጋሪው ታማኒነትን አጥቶ በባዶው እንዲባዝን ያደርገዋል::

ከመናገር በፊት መስማት ይቅደም ይላሉ አበው: ይህ ግን በጠቅላይ ሚንስቴሩ አፈርድሜ በልቶ ወደመቀመቅ የወረደ የጥንታውያን አነጋገር ሆኗል:  ከመናገር በፊት መስማት  አይደለም  መስማት ጭራሹን ነውር ሆኖ የተወስደ ይመስላል። ገና ምንም ሳያደርጉ በበጎ ቃላት ብቻ ህዝቡ ሆ ብሎ ወደ ከፍታ ያወጣቸው ህዝብ በቀላሉ ሆ ብሎ እያወረዳቸው ነው። አማካሪ ይኖራቸው ይሆን። ችግሩ ከሁሉም በላይ ነኝ ስለሚሉ ለፖለቲካ ፍጆታ ያህል አማካሪውች ቢኖሩም የሚተነፍሱት እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም። ዛሬ አብይ አልፋ ኦሜጋ ናቸው። Omini-potent, Omni-present የአብይ ሆኗል።

ጠ/ሚሩ የማይገናኙ ነገሮችን በማገናኘት የህዝቡን የማገናዘብ ብቃት ሲሳደቡ ከማየት በላይ ምን ያሳፍራል: የወጡትን ከፍታ በዚህ ንቀት መንገድ እየተንደረደሩ  እየወረዱ ነው: እውነተኛ  ሪፖርት ማቅረብ ችግር እየሆነ ነው፣  ለነገሩ ብዙ ትዝብቶች ታይተዋልና ክእንግዲህ የሚያምንስ ይገኝ ይሆን? በአሜሪካ የአእምሮ በሽተኛችና የድራግ  ተፎካካሪዎች የሚደረገውን ግድያ በእቅድ የሚደረገውን   የዘር ማጥፋት ግድያ  ጋር ለማመሳሰል  የሄዱበት እርቀት አንድም  መታመምን አለዚያም ንቀትን የሚያሳይ ነው: እንዲህ ብሎ መዝቀጥ አለ?  “አትናገሩኝ የሹም ዶሮ ነኝ”  አባባል በእኛ እየደረሰ ነው::  ከመናገር በተለይም ምንም ከጥያቄው ጋር የማይገናኝ  ነገር ከመዘርገፍ የህዝብን ድምፅ ትንሽም ቢሆን እንኳ ማዳመጥ ማንን ይገድል ነበር: ጠ/ሚንሩ  በሚሰጧቸው መግለጫዎችና ወያኔና ኦንግ በሚያደርጉት የግፍ ግድያ አማራ ብቻውን እንደሆነ ግልፅ ነው: ግን ምን እያደረገ ነው? መቸ ነው የአማራ ህዝብ ከዋይታ ወጥቶ እራሱን አድራጅቶ እራሱን መከላከል የሚችለው?  መቸ ነው ተባብሮ ይህን  ንቀት የሚቋቋመው:   የአማራ ጩኸት ባዶ እንደሆነ የተርዳው መንግስት  የህፃን ግርግር አድርጎታል፣ የግፍ ግፉ እልቂቱን በስም ለመጥራት ስለሚተናናቃቸው አቅለው የርስ በርስ ግጭት ይሉታል። ባጭሩ ጠ/ሚሩ የኢትዮጵያን ንጹሃን በተለይም አማራውን ከድተዋል። የአፍ ወለምታ አይደለም ከልብ የመነጨ እምነታቸው እንጂ። ስለዚህ ይህን ተረድቶ አማራው ከአብይ ጋር የሚደረገውን  ንትርክ ትቶ እራሱን ማዳን ብቻ ነው መፍትሄው።   ለመስማትም  ሆነ  እራስን  ለመከላከል በየቦታው ከማቅራራት ባሻገር ጥብሰቅ ያለ የድርጅትና የመሰባሰብ ስራ ይጠይቃል: ግብንና የመድረሻ  መንገዶችን መቀይስን ይጠይቃል: መደራጀት፣ መደራጀት፣  አሁንም መደራጀት ብቻ ነው እራስን የሚያድን።  ሌሎችም እረጋ ብለው የሚሰሙት መዋሽት የሚያቆሙት ንቀትን አውልቀው  የሚጥሉት ጠንክሮ ሲገኙ ብቻ ነው።

-ንቀቱ ከአማራ መበታትንና አለመደራጀት ላይ የተመሰረተ ነው:

-ንቀቱ ባዶ ሽለላ መሆኑን ተረድተው ነው

-ንቀቱ ከዋይታ አያልፉም ከሚል ነው:

መናገር እንጃ ለአፍታም ሌሎችን መስማት የማይፈልጉት መሪ እራሳቸውን አልፋ ኦሜጋ አድርገዋል: ያልኩት ሁሉ እውነት ይሆናል ብለው ራሳቸስን ስላሳመኑ እንደመጥላቸው ይወረውራሉ፣ በዚህም ህዝብን ያቆስላሉ: ያደማሉ: ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ለአንድ አፍታም ስቅቅ አይላቸውም::

ክሁሉም በላይ አዋቂ ነኝ ስለሚሉ የተናገሩት ሁሉ እውነት ነው፣ ይህን ያልተረዳ አእምሮ እንደሳቸው ያልታደለ ነው:  አራት አመታት ቢፈጅም አሁን ሰውየውን አውቀናልና ምን እናድርግ ነው?

አማራ ታሪካዊ ቦታውንና ሃገራዊ  ድርሻውን ማስከበር አለበት: ይህን ለማድረግ ትግሉ ክእራስ ጋር እንጅ ከአብይ ጋር መሆን የለበትም: ከአብይ ጋር የሚደረገው ትግል የራስን  ትግል አሽንፎ አንድነትን ካረጋገጡና ጊዜ አሻጋሪ ድርጅትን ከፈጠሩ በሁዋላ ነው::ያኔ ክብርም ይኖራል፣ በክብር መፈራትም ይመጣል እንደፈለጉት በአማራ ላይ መቀለድም በቁስሉም እንጨት መክተት ይቀራል:።ክብርም መፈራትም በስድብም ሆነ በቀረርቶ አይረጋገጡም: ስለዚህ ቁርጡ በታወቀ ጉዳይ ላይ አብይ ይህን አልሰራም ብሎ መተከዝ ወይም በጭፍን ጎራው ማለት አንድም ጋት የአማራን ጥያቄ ወደፊት አይገፋም:  የአማራን እልቂት አያስቀርም:  ነፍስ ይማር የሁል ጊዜ ፀሎትእንደሆነ ይቀጥላል::

ስለዚህ ስለአብይ ከማውራት በፊት እራስን መመርመር ይቀድማል:: ክፍተትን መሙላትና መደራጀትን ይጠይቃል: ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም እንዲሉ  ያለፈውን ትቶ እምነትን ከአማራ ህዝብ ላይ አድርጎና ተደራጅቶ ከበጎ አሳቢ ሌሎች  የሃገራችን ህዝብ ጋር አብሮ ለመስራት መነሳት የግድ ይላል።: ሌላ ምርጫ አላይም:

ለደቂቃም  ቢሆን  አማራ በጠላቶች እንደተከበበ መረሳት የለበትም ለዚህም ነው  በተረጋጋ መንፈስ ስትራቴጂና የትግል ታክቲክን ነድፎ አማራ አድን ሀገር አድን  አደረጃጀት የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ የሚሆነው::

 


 

12334445rrr 1

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy wariornoble winner
Previous Story

ቶሌ፤ የቦሌ መለማመጃ – መስፍን አረጋ

blood sucker Abiy
Next Story

አራምባና ቆቦ…..ሰውየው ምን ያህል ጮርቃ እንደሆነ ያሳያል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop