በመንግስት ሚዲያዎች በተላለፈው ፕሮግራም እንደተመለከትሁት የፓርላማ ውይይት ላይ አንስቻቸው የነበሩ 3 የሥነ–ስርዓት አስተያየቶች/ጥያቄዎች ተቆርጠው እንዳይተላለፉ ተደርገዋል

ማምሻውን በመንግስት ሚዲያዎች በተላለፈው ፕሮግራም እንደተመለከትሁት የፓርላማ ውይይት ላይ አንስቻቸው የነበሩ 3 የሥነ–ስርዓት አስተያየቶች/ጥያቄዎች ተቆርጠው እንዳይተላለፉ ተደርገዋል። ተቆርጦ ያልተላለፈ ሀሳብ የኔ ብቻ እንደሆነም መግለጽ እፈልጋለሁ።
አስተያየቶቹ/ጥያቄዎቹም፦
1) እንደሌሎች መደበኛ ስብሰባዎች የዛሬው ስብሰባ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጥታ በምክር ቤቱ ዩቲውብና ፌስቡክ ገጽ አለመተላለፉ ምክር ቤቱ ስራውን በግልጸኝነት ያከናውናል የሚለውን መርህ የጣሰ መሆኑን
2) በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ወደ 16 የሚደርሱ የተደመጡ አስተያየቶች ከሞላ ጎደል ሞሽኑን ከአንዳንድ ማስተካከያ ጋር የሚደግፉ ሲሆኑ፤ በምክር ቤቱ የሀሳብ ብዝሀነት እንዲስተናገድ አፈ ጉባዔው የውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተቃውሞ ድምጽ ያላቸው አባላትን እንዲጠይቁና ተቃውሞ እንዲስተናገድ ማድረግ አለብዎት።
3) በምክር ቤቱ የአሰራር ስነ ስርዓት መሰረት በምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ በስምምነት ያልፀደቀ አጀንዳ ለምክር ቤቱ ሲቀርብ፣ ምክር ቤቱ በአጀንዳው ላይ ከመወያየቱ በፊት አጀንዳውን ማጽደቅ አለበት የሚለው መርህ መጣሱና ቀጥታ ውይይት መጀመሩ የስነ ስርዓት ጥሰት ስለሆነ ማስተካከያ ወይም ማብራሪያ ይሰጠኝ የሚል ነበር።
ለቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና ድምፃችን ቢታፈንም በተለያዩ አማራጮች ድምፃችንና ሀሳቦቻችን እናሰማለን። ለዚህም ሀሳቤን የማጋራበት ከታች የተያያዘው ኦፊሻል የዩቲውብ ገጽ የከፈትሁ መሆኔን ለወዳጆቼ አሳውቃለሁ!
ተጨማሪ ያንብቡ:  የማዳኛው ክኒን ኢትዮጵያዊነት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share