አድርባይነት ! የሞራል ዝቅጠት : የለውጥ መርገም ! /(ኢዜማ?) – ከቴዎድሮስ ሐይሌ

አንድ ንጉስ ልጅ ይወልድና ታላቅ ደስታ በቤተመንግስቱ ይሆናል :: ንጉሱም የተወለደው ልጁ የወደፊት እጣ ፋንታእጅግ ያሳስበና በዘመኑ ያሉ አዋቂ የተባሉ ጠንቋዮች ኮከብ ቆጣሪዎችን ደብተራና አስማተኞችን አስጠርቶ ልጁ ሲያድግ ምን እንደሚሆን ይጠይቅ ጀመር::  ሁሉም በየተራ እየተነሱ ልጁ አድጎ የአባቱን ግዛት እንደሚያስፋፋበሃይለኝነቱ ጠላቶቹን የሚደመስስ የጦር ሰው እንደሚሆን ሌላም ሌላም የውዳሴ ትንቢት እያዘነቡ የንጉሱንመንፈስ በሃሴት ሞሉት ::

በዚህ የአድርባዮች በነገሱበት የንጉስ እልፍኝ በአዋቂነቱ ተጋብዞ የነበረ አንድ ፈላስፋ ካነበበው ታሪክከመረመራቸው መጽሃፍት አንጻር የንጉሱንን ልጅ የመጪ ዘመን እድል እንዲናገር በንጉሱ ይታዘዛል:: ፈላስፋውም ንጉስ ሆይ ሺ አመት ንገስ እኔ የማውቀው ቢኖር ልጁ ጎርምሶ ሆነ እርጅቶ እንድ ቀን ሟች መሆኑንአውቃለሁ:: ስለ መጪ ዘመኑ እድል ፋንታ ግን የማውቀው የለም ብሎ ይቀመጣል::

በንጉሱ ስጦታና በግብዣው ወይን ጠጅ ልቡ የተደፈነው የአድርባይ መንጋ ይህ ፈላስፋ መጥፎ ተመኝቷል : በታላቁ ንጉሳችን ልጅ ላይ አሟርቷል:: ፍርድ ይገባዋል በሚል በእድርባዮች ተከሶ ንጉሱም በከንቱ ውዳሴ አይነልቦናው ታውሮ ሊሆን የሚችለውን ከመጽሃፍት ያነበበውን ከሕይወት የተማረውን እውነት የተናገረውን ፈላስፋበሞት እንዲቀጣ ወሰነበት ይባላል::

የአድርባይ ምላስ ለሞላ መሶብ ስልጣን ለያዘ ሹም ሃብት ላካበተ ከበርቴ ለመነጠፍ ሃሰት ለመዝራት ከንቱውዳሴን ለማዝነብ የሚቀድማት የለም:: አድርባይ ለሞቀ ዙፉን ሰጋጅ ቀን የሞላለት አይጥ አንበሳ ጭለማውንብርሃን ብላ ለመግለጽ የሚለጉማት ሞራል የተባለው የሕሊና ጠፍር የላትም:: አድርባይነት የለውጥ እንቅፋትየፖልቲካ ቫይረስ ናት::

በተለይ ለሃገራችን መቆርቆዝ ዛሬ ለደረስንብት ውድቀት የአድርባዮች ሚና የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል:: ጃንሆይመቃብር ሲማስላቸው ሞት ተደግሶ ቀን ሲቆጠርላቸው : ስህተታቸውን አውቀው ለማረም እንዳይችሉበከበቧቸው መንጋ አድርባዮች ከንቱ ውዳሴ ታንቀው ላሳፋሪ ፍጻሜ በቅተዋል:: ሊቀመንበር መንግስቱምበተመሳሳይ ባቡር ተሳፍረው ለስደት እንደበቁም አይተናል::

ለዚህ ነው መካሪ የሌለው ንጉስ ያለ አመት አይነግስ አባቶች የሚሉት:: ምክር ሰይፍ ናት ትቆርጣለች:: ትችትሞረድ ሆና ትስላለች:: ሂስ ኮንፖስ ሆና አቅጣጫዎችን ታሳያለች:: እውነት መስተዋት ነችና ጉድፍን ታሳያልች:: ልባም መካሪ እንዲህ ነው:: ይህን መሰል እስተዋይነት የተሞላው መካሪና ወዳጅ መሪዎች እያጡ ባልሆኑትእንደሆኑ : ከስረው እንዳተረፉ ተዋርደው እንደከበሩ በጣፈጡ ቃላት ተሽሞንሙነው ወደ አይቀሬው ውርደትያዘግማሉ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  እዉነተኛና ዘላቂ ግንባታ

ለአድርባይነት ሰው የሚጋለጠው የስልጣን ጥማት ሕሊናውን ሲጋርደው : አፍቅሮት ንዋይ እረፍት ሲነሳው : ወኔሲያጥር ድፍረት ስትነጥፍ ፍርሃት ሲያይል ነው:: ሆዳምነት ለከት ሲያጣ ለቁሳዊ አላፊና ጠፊ እንስሳዊ ባህሪ ይዳርጋል:: ሕሊና ሲደርቅ መንፈሳዊነት ሲሳሳ ስጋዊ አረም በላያችን ሲነግስ የአድርባይነት እርጉም መንፈስና የሞራል መርገምት የሃገር ደዌ ይሆናል::

ምሳሌዎች በሽ ናቸው ከጁንዲን ሳዶ እስከ አየለ ጫሚሶ : ከካሱ ኢላላ እስከ ታምራት ላይኔ : ብዙ አይተናል:: የሃይለማርያምን ባዶ ወንበር የነጋሶን መገለል : የገነት ዘውዴን ቅጥ ያጣ ምግባር በየፈርጁ አይተናል :: መርሕ እውነትና ሃቅ ይዘው እስከመጨሩሻው የጸኑ ጀግኖች በቁጥር እጅግ ቢያንሱም ለትውልድ ተምሳሌት የለውጥ ብርሃን ሆነውን ተስፋችን በአድርባዮች ጠውልጎ እንዳይጠፋ ጠል ሆነውናል::

ዛሬ ሃገራችን ያለችበት ሁኔታም ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ ከዛው አሮጌ አድርባይንት ከነገሰበት ዋሻ አልወጣንም:: አበው በካባ ላይ ደበሎ እንዲሉ ፖለቲካችን ላይ ጨለምተኛ የጎሳ እርዕዮት ተጨምሮበት አድርባይነት ሲታከልበት የሚፈጥረው ተጽዕኖ ለመገመት ከባድ ነው::

አሁን ደግሞ በመደመር ወሽመጥ በአድርባዮች ሰልፍ ውስጥ እነ ዶር ብርሃኑን እያየን ነው:: ማህበራዊ ፍትህን የሚያህል ታላቅ ሕዝባዊ አጀንዳ ተሸክሞ የአማራጭ ፓርቲ ሚና ለመወጣት ተቋቁሚያልው የሚለው ኢዜማ እየተናጠ ያለበት ውስጣዊ ቅራኔ ዕሪዎታለማዊ ወይም እስትራቴጂያዊ ጥያቄ አይደለም:: በፓርቲው መርህና በሚከተለው ፍልስፍናም አይደለም:: ዋናው የፓርቲው ቀውስ ለገዥው ፓርቲ ለመንበርከክ ሱሪያቸውን ባወለቁና የሕዝብና የሃገርን ጉዳይ እናስቀድም የሚል ባርኔጣ ባጠለቁ መካከል እንደሆነ በገሃድ እየታየ ነው::

የዛሬው የዶር ብርሃኑ አቋምና ሲያራምዱት የቆዩት ተግባር የፖለቲካ አድርባይነት የተጣባው ሃላፊነት ካለበት የድርጅት መሪ የማይጠበቅ ነው:: ግለሰቡ ባላቸው ስብዕና ከብዙ አቅጣጫ ብዙ ቢባሉም ሌሎች ያልሰሙ ትጥቂቶች የምናውቀው የሴራና የአሻጥር ፖለቲካ ተዋናይ ቢሆኑም ያለፈውን ሁሉ ትቶ ባለው የለውጥ ሂደት ውስጥ ተሽለው ይገኛሉ የሚል እምነት ነበረ :: ያ ቢቀር እንኳ በዚህ ደረጃ ወርደው የአድርባዮችን ካንፕ ይቀላቀላሉ ብሎ የሚገምትም አልነበረም::

አብይን ዛሬም አምነዋለሁ የሚሉት ጎምቱው የሴራ ፖለቲከኛና የኢኮኖሚ ኤክስፐርቱ ብርሃኑ የአድርባይነትን ጥግጋት ከአንድ የታሪክ ኩነት ጋር ይመሳሰልብኛል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሐምሌ ጨረቃ! (ክፍል አንድ) - ከአንዱዓለም አራጌ ዋለ (አንድነት ም/ሊቀመንበር ከቃሊቲ ማጎሪያ)

አድርባይነት በየዘመነ መንግስቱ የተለያየ ባህሪና ገጠመኝ አለው:: በ66 አብዮት ማግስት ገና በአፍላው የተፈጸመ ወደር የለሽ የአድርባይነት ጥግ በታሪክ ተሰንዶ ማየት ይደንቃል:: ከፈረሱ አፍ እንዲሉ ከጊዜው ተራማጆች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አማረ ተግባሩ ኃይሌ ፊዳ እና የግሌ ትዝታ በሚል እርዕስ በጻፉት መጽሃፍ በገጽ 137 እንዲህ ብለውያሰፈሩት ይጠቀሳል::

“’ኢሃፓ ፍቅሬ መርድን ከገደለ በሗላ ለደህንነትችን ሲባል ኮሎኔል መንግስቱ መኖሪያ ቤት እያመሸን በአጃቢ ወደቤታችን እንሸኝ ነበር:: አንድ ቀን እንደወትሯችን የፖለትካ ክርክሩ አብቅቶ ወደ ጨዋታና ቀልዱ አምርቶ እሳቸውም ዘና ብለው ከተቀመጡበት ሶፉ ላይ ሆነው ሰዓቱም እየመሸ በመሄዱ ይሆን የተለምዶ የወታደር ቡት ጫማቸውን ክር ለመፍታትና ካንጋቾቻቸው መካከል ለእግራቸው ሙቅ ውሃ ይዞ በመቅረብ ላለው ሰው እራሳቸውን ሲያዘጋጁ ሌላው አንጋቻቸው ጫማቸውን ለመፍታት ተንደረደረ:: ይህንን የተመለከተው ከሕብረቱ ድርጅቶች መሪዎች መካከል አንዱ ሰውም አብሮ ተንደርድሮ ካንጋቹ ጋር ትንቅንቅ ያዘ:: ይህን የተመለከቱት ኮሎኔል መንግስቱ ኧረ አይገባም ቢሉም .. ይህው ከህብረቱ ድርጅቶች መሪ አንዱ የሆነው ሰው ጡንቸኛና ፍርጥም ያለ ስለነበር አንጋቹን ገፍትሮ ጫማቸውን አውልቆ እግራችውን አጠበ:: ግለሰቡ አጠባውን ጨርሶ ወደ መቀመጫው ሲመለስ የሚያስነውር ሳይሆን የሚያኮራ ተግባር እንደፈጸመ ፈገግ እንዳለ ወደ መቀመጫው ተመለሰ”

በዚያን ግዜ በኮሎኔል መንግስቱ ቤት አብረው የነበሩት የኢማሌድህ ድርጅት መሪዎች ነበሩ:: በግዜው የግራ ፖለቲካ እርዕዮተ አለም የሚጠበቡት የመኤሶኖቹ ሐይሌ ፊዳ አንዳርጋቸው አሰግድና ፖለቲካን የሚራቀቁባት ዶርነገደ ጎበዜን አቶ አሰፉ ጫቦ ዘገየ አስፉውና ዶር ሰናይ ልኬን የመሰሉ አብዮተኞች የታደሙበት ስብስብ ነበር:: ጸሃፊው ተንበርካኪውን እግር አጣቢ የፖለቲካ መሪ እከሌ ነው ብለው በመጽሃፉቸው ስሙን ባይጠቅሱም ዶር ሰናይ ልኬ እንደነበር በወቅቱ እዛ አካባቢ ከነበሩ ሰዎች ሰምቻለሁ::

ዛሬስ እግር ለማጠብ የተሰለፉት ምሁራን የሉም ወይ? የእነ ዶር ብርሃኑ አብይን አምነዋለሁ የሚለው አቋም ከአድርባይነት የተቀዳ እምነት አይደለምን? አብይ የብሄር ፖለቲካን አስወግዶ ሃገራዊ አቋም እንዲጠናከር ያግዛል ሲሉም አልነበር? የታል ኢትዮጵያዊነት? ዛሬ ላይ ሰዎች በማንነታቸው በሺዎች ታርደው የሚያድሩበት ሃገር በዚህ ዓለም ላይ ከኢትዮጵያ ውጪ ማንም የለም:: ተረኝነት አፍጥጦ በሚታይበት ጄኖሳይድ የዕለት ዜና በሆነበት ገዥው ቡድንና ጠቅላይ ሚንስትሩ ከብሄር ፖለቲካ ቀኖናቸው ሳይላቀቁ ፖርቲያቸው ግጭት ጠማቂና ፍጅትፈጻሚ በሆነበት የሰቆቃ ምድር እንዴት ተስፉ ይሆናል:: በዚህ ሁሉ ሰቆቃ ውስጥ ዛሬም ለነዶር ብርሃኑ መንገድም ሕይወትም አብይ ነውን? ሕዝብ የሚጠይቀው ይህንን ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህህዋት የዘረኝነት ፓለቲካና መዘዙ ( ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ ሌና)

አንድ አማራጭ ፓርቲ የሚመራ መሪ የመርከቧን ቀዳዳ ለመድፈን ከመታገል ይልቅ የካፒቴኑን ባዶ የተስፉ ኑዛዜ አምኖ አብሮ ለመስመጥ የሚያድርገው ምን ሃይል ይኖራል:: ከፍርሃት ከሞራል አልባነትና ከአድርባይነት ውጪ:: እንደ ዶር ብርሃኑ በኢትዮጵያ ፖለቲካ እድሜውን የጨረሰ ፖለቲከኛና ጥርሱን የነቀለ የአራዳ ልጅ እንደወረደ በባዶ የባልቴት ፕሮፓጋንዳ ሊነዳ የሚችልበት ምንም ምክንያት የለም:: ከላይ እንዳነሳንው ከተልዕኮው ውጪ በማይመልከተው የእግር አጣቢነት የተሰማራው የፖርቲ መሪ ለግርድና ያንብረከከው የሞራል ዝቅጠት የአድርባይነት መንፈስ ብቻና ብቻ ነው::

የትግሉ እርዝማኔ በየፌርማታው የሚያወርዳቸው የጽናት ማጣት ትጥቃቸውን የሚያስፈትቸው የስልጣን ፍርፋሪ የቤተመንግስቱ እልፍኝ የሚያንበረክካቸው መርህ የለሾች በታሪክ ፊት ማየታችን ትላንትም ነበር ዛሬም ይቀጥላል:: በዛው ልክ የአቋም ሰዎች አሻራቸውን እያኖሩ በጥላቸው እያስበረገጉ በሃሳብ ሰይፍ እየመተሩ ምርኮኛና ምስለኔውን ብቻ ሳይሆን ገዢዎችንም እያራዱ ትግሉ ይቀጥላል:: ኢዜማ ውስጥ ሕዝባዊና ሃገራዊ ስሜት ያላችሁ ከየትኛውም ዘውግ ይሁን ሃይማኖት ውጡ በመርህ የምትመሩ ሞራልና እውነትን ትጥቅ አድረጋችሁ አድርባይነትን ልትጠየፉት ይገባል:: ለራሳችሁ ክብር ለልጆቻችሁና ለትውልድ የሚኖር አሳፉሪና አዋራጅ ታሪክ እንዳታወርሱ ተጠንቀቁ:: ለባለግዜ ዘረኛ ገዥዎች በአድርባይነት የሚታየው የፓርቲያችሁን አዋራጅ ምስል ለውጣችሁ ወደ ሕዝባዊነት ከፍታ ልትመልሱት ግድ ይላችሗል:: አለያ እውነት ጨልማ ሞራል ጠውልጋ አድርባይነት ደግፎት የሚጸና ወንበር አይኖርም:: መጨረሻውም ለሰጋጁም ለአሰጋጁም አያምርም:: የጨለመው መንጋቱ ሕዝብ የድሉ ባለቤት መሆኑ ዲሞክራሲ ሰፍኖ በዘረኝነትና በአድርባይነት መቃብር ላይ የሃሳብ የበላይነት በሃገራችን መረጋገጡ ቢዘገይም አይቀሬ ለመሆኑ አንጠራጠርም::
በመጨረሻም ኢዜማዎች ከታሪክ ተማሩ በእራሳችሁ እንዳታፍሩ!!!
ድል ለሕዝባችን!!!

14 Comments

  1. ነገሩ መልካም ሁኖ ብርሀኑ መርህ አልባ እድሜ ልኩን ምንጣፍ ጎታች፣አድር ባይ፣ፈሪ በመሆኑ ዛሬ በስተርጅናው የተዋሃደውን ባህሪ ተው ማለት የጎበጠን ግንድ ማቃናት ነው። አንድ ያልተዋጠልኝ የዚህ ሰውዬ ምሁርነት ነው ሲናገር ሰምቻለሁ ጽሁፍን እንኳ አይደፍርም ምንም ልብ የሚያደርስ ነገር አላየሁበትም። በአጋጣሚ የሀገር መሪ ቢሆን ትግሬዎች መርከብን የሚያህል ግዙፍ መርከብ ለመሸጥ እንዳልተሸማቀቁ ሁሉ ብርሀኑም አገር ለመሸጥ ወደሁዋላ አይልም።

    • የሀበሻ ድፍረት ያስቀኛል የዶክተር ብርሀኑን ፖለቲካ እንኳን ብንተው አሜሪካ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ነው: ይህ በወሬ አይገኝም

  2. ውድ ወዳጄ የጻፍከው ጽሁፍ መልካም ነው። አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄዎችን እንድናነሳ የሚጋብዝ ነው። የአድርባይነትን ጉዳይ አንስተሃል። ለመሆኑ አንድ ሰው አድርባይ ነው የሚባለው ከምን በመነሳት ነው? ይህንን ጉዳይ ትንሽ ጠጋ ብሎ መመልከት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። አንድ ሰው አድርባይ ነው የሚባለው የራሱ ርዕይ ወይም መመሪያ(Principle) የሌለው እንደሆነ ነው። እንደሚታወቀውና በአገራችን እምብዛም ግልጽነት የሌለው ጉዳይ ፖለቲካ የሚባለው ትልቅ ጽንሰ-ሃሳብና የአገር መገንቢያ መሳሪያ ከርዕይና ከሞራል ውጭ መታየቱ ነው። አንድ ሰው ፖለቲከኛ ነኝ ሲል ዝም ብሎ አይደለም የሚነሳው። ርዕይ ወይም ደግሞ በሞራል ላይ የተመሰረተ መመሪያ እንዲኖረው ያስፈልጋል። ፖለቲካ የአገርንና የህዝብን ጥያቄ የሚያካትትና ተከታታይነትም ያለው ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን የሚነሳበት መመሪያ ያስፈልጋል። ፖለቲካ ከህዝብና ከአገር ጉዳይ ተነጥሎ የማይታይ እንደመሆኑ መጠን፣ የህዝብን ጥያቄዎች የሚመለሱበትና አገርም በጸና መሰረት ላይ እንዲገነባ የሚያገለግል ነው። ስለሆነም ፖለቲካ ወደ አንድ ግለሰብ የሚቀነስና የአንድ ግለሰብ ጥቅም ማርኪያ መሳሪያ አይደለም። ስለሆነም በፖለቲካ ዓለም ውስጥ እሳተፋለሁ የሚል ሰው የብዙ ሚሊዮን ህዝብን ዕድል ያንጠለጠለና ህዝብም የሚመካበት እንደመሆኑ መጠን፣ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ሰው ሀቀኛ መሆን አለበት። በአገራችን ምድር ፖለቲካ የሚባለው ጉዳይ ከህዝብና ከአገር ጋር ሳይሆን ከግለሰቦች ወይም ከአንዳንድ ድርጅቶች ጋር ስለሚያያዝ የየግለሰቦች ፍላጎት ማርኪያና ማጎልመሺያ መሳሪያ ሊሆን በቅቷል።
    ሌላው ከላይ መሰረታዊ-ሃሳብ ጋር የሚያያዘው ጉዳይ ፖለቲካ ከሌሎች አገርን መገንቢያ ከሆኑ ዕውቀቶች ጋር መያያዝ ያለበት ጉዳይ ነው። እነዚህም የሳይንስና የቴክኖሎጂ ጉዳይ፣ ትክክለኛ የኢኮኖሚ ቲዎሪና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳይ፣ የማህበራዊ ጉዳይ፣ የፍልስፍናና የባህል ጉዳይ፣ አንዲሁም አገርን ለመገንባት የሚያገለግሉ ኢንጂነሪንግ በመባል ከሚታወቁት ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ነው። በእርግጥ አንድ ሰው በእያንዳንዱና በሁሉም ነገሮች ላይ ዕውቀት ሊኖረው አይችልም። ይሁንና አንድ በፖለቲካ ዓለም ውስጥ እሳተፋለሁ የሚል ሰው አገርን ለመገንባት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ አጠቃላይ የሆነ ግናዘቤ ያስፈልገዋል። የመሪነትን ቦታም በሚይዝበት ጊዜ የሚመርጣቸውን ሰዎች ሊያውቅ ያስችለዋል።
    ከዚህ አልፈን ስንሄድ አንድ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ሰው ወይም አንድን ድርጅት እወክላለሁ የሚል ሰው የህዝብንና የአገርን ጉዳይ አስመልክቶ በየጊዜው ሰፋፊ ሀተታ ለመስጠት መቻል አለበት። እነዚህም ፖለቲካዊ፣ የጸጥታን ጉዳይ አስመልክቶ፣ የኢኮኖሚ ፖሊሲንና ሰፊው ህዝብ የሚኖርበትን ሁኔታ፣ የገቢ ጉዳይና ክፍፍልን በሚመለከት፣ የሀብት ፈጠራንና ሀብት ሚዛናዊ በሆነ መልክ ስለመከፋፈሉ ጉዳይ‹፣ ከዚህ ስንነሳ አገዛዙ የሚከተለውን ፖሊሲ ጠጋ ብሎ በመመልከት በቂና አጥጋቢ ትንታኔ መስጠት ያስፈልጋል። ስለሆነም አንድ ድርጅት ህዝብን የሚያስተምርበት የራሱ የሆነ ልሳን እንዲኖረው ያስፈልገዋል። የራሱ የሆነ የሳምንት ጋዜጣ ወይም ወርሃዊ መጽሄት የሌለው ድርጅት እንደፖለቲካ ድርጅት በፍጹም ሊቆጠር አይችልም።
    በአገራችን ያለው ትልቁ ችግር በፓርቲ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች የተለያዩ ነጥቦችን በማንሳት ህዝብን ለማስተማር የሚችሉበት ልሳን የሌላቸው መሆኑ ነው። ስለሆኑም የድርጅቶችንና የመሪዎቻቸውን ተግባርና ርዕይ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። እንደምክታተለው ከሆነ አብዛኛዎች በፓርቲ ስም የሚንቀሳቀሱና ፖለቲካዊ ዕውቅና ያላቸው ሰዎችና ድርጅቶች ለምን ዓላማ እንደሚታገሉ ግልጽ አለመሆኑ ነው። እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የፖለቲካውን ሜዳ በመያዝ ግራ ሲያጋቡ ይታያል። የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የሚከበሩና ብዙ ተከታዮችም ያላቸው መሆኑ ነው። ይህም የሚያረጋግጠው ፖለቲካ የሚባለው ትልቅ ነገር በአገራችን ምድር ሳይንሳዊ ግንዛቤ ያለማግኘቱና ከዕውቀት ውጭ መታየቱ ነው።
    ወደ አነሳኸው ወደ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዳይ ስንመጣ ስራው ሁሉ በጣም የሚያሳዝን ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት ሚኒስተር የሆነበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። በሌላ አነጋገር የሌላፓርቲ አባል የሆነ ብቻ ሳይሆን መሪም የሆነ ሰው ስልጣን ሊሰጠው ሲል ከድርጅቱ ጋር የግዴታ መወያየት ወይም መከራከር አለበት። በተለይም ደግሞ በምን ዐይነት ቅድመ-ሁኔታ ስልጣንን እንደሚይዝ መታወቅ አለበት። የፓርቲውን ርዕይ የማያንፀባርቅና ተግባራዊም ለማድረግ የማያስችል ስልጣን የግዴታ ወደ አድርባይነት ማስለወጡ የማይቀር ጉዳይ ነው። ሌላው ጉዳይና መታወቅ ያለበት መሰረተ-ሃሳብ አንድ ከ90% በላይ ያሸነፈ ፓርቲ ለምን ስልጣኑን ለሌሎች እንደሚያጋራ ነው። በአውሮፓ ምድር አንድ ፓርቲ በፍጹም ድምጽ ምርጫን ካሸነፈ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጣምራ መንግስት የሚመሰርትበት ጉዳይ የለም። ወደ ብርሃኑ ነጋ ስንመጣ ሰውየው ስልጣንን የያዘው ከንጽሁ የአድርባይነትና ከራስ ፍላጎት አንጻር በመነሳት እንጅ አገርንና ህዝብን አገለግላለሁ ከሚለው ቅዱሳዊ ስሜት በመነሳት አይደለም። ሰውየው ለመታወቅና ለመታየት የሚፈልግ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሰዎችንም በከፍተኛ ደረጃ የሚንቅ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሆነ የአምባ-ገነንነት ስሜት ያለው ነው። ስለሆነም በፖለቲካ ዲስኮርስ የሚያምን ሳይሆን ግልጽነት በሌለው አስተሳሰብ የሚመራ ነው።
    ለማንኛውም ብርሃኑ ነጋ የአገርንም ሆነ የውጭ ፖለቲካን በሚመለከት የጠራ አቋም የለውም። ለምሳሌ አንተ ያነሳኸው ኢኮኖሚስት የሚለው አነጋገር፣ የተማረው ኢኮኖሚኮስ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ወያኔ 27 ዓመታት ያህል ተግባራዊ ያደረገውንብ የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲን አስመልክቶ አንዳችም ጽሁፍ አላወጣም። የአቢይንንም የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን እንደሆን ሲነግረን አይሰማም። አንተ እንዳልከው ብርሃኑ ነጋ አቢይን እንደሚያምነው ነው። በምን ምክንያት እንደሚያምነው ግን አልነገረነም። ፖለቲካ ደግሞ አንድን ሰው በማመን ላይ የሚመሰረት ሳይሆን በመመሪያና በርዕይ ላይ ነው። ይህም ማለት የህዝብን ጥያቄ የሚመልስና ህዝብን የሚያነቃና የሚያደራጅ፣ እንዲሁም የአገርን አንድነት የሚያስጠብቅና ወደ ውስጥም ስላም የሚያሰፍን መሪም ሆነ አገዛዝ ብቻ ነው አመኔታ የሚጣልበት። ከዚህ አጭር ሀተታ ስንነሳ አቢይ አንዳቸውንም ጉዳይ የሚያሟላ አይደለም። እንዲያውም አገርን ለማፈራረስ የሚሯሯጥ ነው የሚመስለው። ስንትና ስንት ሺህ ሰው ሲገደል ፅፀት የማይሰማው ነው። በተለይም በአማራው ላይ በተቀነባበረ መልክ የማፈናቀልና የግድያ እርምጃ ሲካሄድ ዝም ብሎ የሚመለከት ሰው ነው። በአጭሩ አቢይ የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው የጥቁር ህዝብም ጠላት ነው። ኢትዮጵያን የሚያክል ታላቅ አገር ለማፈራረስ ከውስጥና ከውጭ ኃይሎች ጋር የሚሰራ ሰው ነው። በሰላይ ድርጅቶችና በራሱም በአገዛዙ የታጠቁ አገር በታታኝ ኃይሎች በተለይም ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ሲንቀሳቀሱና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገድሉና የአገርን ሀብት ሲያፈራርሱ ዝም ብሎ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን እንዲያምውም ግፉበት የሚል የሚመስል አስገራሚ ፍጡር ነው። ሰውየው መንፈስ ይኑረው አይኑረው ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። ታዲያ ብርሃኑ ነጋ ከእንደዚህ መንፈሰ-አልባ ከሆነ ሰው ጋር ነው የሚሰራው።
    ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ ብርሃኑ ነጋ ከአሜሪካን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያለውና አሜሪካ በነበረበት ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት ወጣ ገባ የሚል ነበር። በአጭሩ የእነሱ ተላላኪ የሆነና ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰራና የአገርን ብሄራዊ ነፃነት ለማስከበር የሚችል ሰው አይደለም። እንደነዚህ ዐይነት ግለሰቦች ስልጣን ላይ በሚወጡበት ጊዜ የአሜሪካን ተላላኪ ከመሆን በፍጹም የሚያልፉ አይደሉም። በአጭሩ ብርሃኑ ነጋ አገርን በሚመለከት በሺህ ጉዳዮች ላይ ምንም ዐይነት ግልጽ የሆነ አቋም የለውም። ስለሆነም አድርባይ መሆኑ የሚያስገርም ጉዳይ አይደለም።
    ለተጨማሪ ማስረጃ ይህንን ድረ-ገጽ ተመልከት፦ http://www.fekadubekele.com
    ፈቃዱ በቀለ

    • ዶር ፈቃደ ጥሩ አስተያየት ወይም ግምገማ ነው የሰጠኸው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ብርሃኑ ነጋ የረከሰ የተረጉመ የተዋረደ ሰው ነው። ነገር ግን የአዞ ቆዳ የለበሰ አድርባይ አድርባይ በመሆኑ ምንም ፍንክች ሳይል የሚሆነውን እየሆነ መቦዘኑን አላቁዋረጥምም፥ የቦዘኔም ጠባይ ይሄው ነው።

  3. ወንድማችን ዶ/ር በፍቃዱ በቀለ ስለ ብርሃኑ ብዙ መናገር ይቻል ነበር ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ liability ነው ብሎ መዝጋቱ ይቀላል፡፡ በህይወቱ ዘመን እንዳልከው በመርህ የሚመራ ሳይሆን በሽፍጥ የተሞላ ብልጣ ብልጥ ሰው ነው፡፡ እሱና ህዝቅዬል ጋቢሳ ፕሮፌሰርነት ስማቸው ይሁን በትምህርት የተሰጣችው ማእረግ እስኪያጠራጥር ድረስ ክብሽሽቅ በቀር አንድም ረብ ያለው ነገር ሲናገሩም ሆነ ሲጽፉ አይታዩም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ሰውዬው ለክብርም የታደለ አይደለም እራሱንም ችሎ አይቆምም ሁል ጊዜ መደገፊያ ይፈልጋል፡፡ ነገ የአብይ መንግስት ቢወድቅ ቀድሞ የሚከዳው ለወንጀሉም ምስክር የሚሆነው ብርሃኑ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሲባረሩ (በገነት ዘውዴና መለሰ ዜናዊ) ብርሃኑ አለደሞዝ እሰራለሁ ብሎ ተንደርድሮ የገባ ደካማ ሰው ነው፡፡ እነ መለስም በሚገባ ስላወቁት ፊትም አልሰጡትም ምን ቢላላጥ አልሆነም ከታጋዮች በስህተት ተድባልቆ ታስሮ ለስጋው ምቾት ሲል ፈርማችሁ ካልወጣን ብሎ ከሽማግሌዎች ጋር ሲደባደብ የነበረ ማፈሪያ ሰው ነው፡፡ ጥሩ ጥሩ የማፊያ መንጋዎች አገር ቤትና ዋሺንግተን ዲሲ አሉት ኢሳት የሚባለው እሳትም አንዱ መሳሪያው ነው በስንት ማጭበርበር በተሰበሰበ ገንዘብ የተቋቋመውን የማፊያ የዜና ድርጅት ቀምተው በጓደኛው አንዳርጋቸው ጽጌ ይተዳደራል፡፡ እነዚህ ሰዎች አጋጣሚውን አላገኙም እንጅ መርከብ እስከ ነብሱ ይሸጣሉ በዚህ አሰራራቸው ክትግሬዎች የሚሻሉበት ነገር አይታየኝም፡፡ ለማንኛውም ሳትደክም ሳትታክት ለሃገርህ ዘወትር በማሰብህ ምስጋናችን የላቀ ነው አስተዋጾህ ያልታወቅ አይመሰልህ ኢትዮጵያ ልጆቿን አትረሳም፡፡ ባጠቃላይ ብሬ ጩሉሌ የከተማ ልጅ ነው ችግር ሲመጣ መውጫውንም ያውቃል ቅንጅት ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ ብሬ ሌሊቱን እንድብር እንሰት ሰብል ውስጥ ተሸሺጎ ያንን ክፉ ጊዜ አለፈው፡፡ ቅምዝምዝና ክፉን ጊዜ ጎምበስ ብሎ ወይም ባለስልጣን ተጠግቶ ማለፍ ነው የሚል መመሪያ አለው በዚህ ነገር ግርማ ሰይፉም ይረዳዋል፡፡ አንድ የመርህ ሰው ቢኖር ተረባርበው ጣሉት፡፡

  4. በአገራችን ምድር ለአድርባይነት መስፋፋት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ውስጥ ሰተት ብሎ የሚገባው ሁሉ በቂ የቲዎሪ፣ የሳይንስና የፍልስፍና እንዲሁም የህብረተሰብ ሳይንስ ግንዛቤ ሳይኖረው ነው። ይህን ዐይነቱን ሂደት ያልተጓዘ የአካዴሚክስ ዕውቀት ብቻ ያለው ግለሰብ በተለይም በአንድ የትምህርት ዘርፍ ለምሳሌ በኢኮኖሚክስ ውስጥ ያሉና የሚያከራክሩ አስተሳሰቦችን ለመረዳት አይችልም። በተለይም እንደኛ ባለ ክርክርና ትችት፣ እንዲሁም ጥያቄ መጠየቅ ባልተለመደበት አገር ውስጥ ተማርን የሚሉና የራሳቸውን ውስጣዊ ፍላጎት ለማርካት የሚፈልጉ ቀድመው በመውጣት ልዩ ልዩ ህብረተሰብን የሚመለከቱ ጉዳዮች ክርክር እንዳይደረግባቸው መንገዱን ይዘጋሉ። መጽሀፍ ማንበብና ልዩ ልዩ አስተያየቶችን ማወዳደር ባልተለመደበት አገር ውስጥ በፖለቲካ ውስጥ ሰተት ብሎ የሚገባ ቶሎ ብሎ አንድን ግለሰብ ወይም አንድን ድርጅት ማምለክ ይጀራል። በዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ሌላ የተሻለና ተፃራሪ አስተያየት በሚሰነዘርበት ጊዜ አስተያየት ሰጪው እንደጠላት መታየት ይጀመራል። በተለይም መሪ ነኝ የሚለው ላይ የሚሰነዘር ገንቢና ሳይንሳዊ ትችት ልክ እንደስድብ በመቆጠር ትችት ሰንዛሪው ላይ የስድብና የማስጠንቀቂያ ውርጅብኝ ይወርድበታል። ትዝ እስከሚለኝ ድረስ የዛሬ አስራአምስት ዓመት ገደማ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ዳላስ ስብሰባ ላይ ተጋብዞ በተለይም ስለምዕራቡ ዓለም ፖለቲካ አምስት ያህል ገጽ የራሱን አስተያየት ይሰጣል። ያቀረበውን ጽሁፍ ካነበብኩኝ በኋላ የሰጠውን አስተያየት እኔ በምረዳው መልክ መስመር በመስመር ከሳይንስና ከፖለቲካ ቲዎሪ እንዲሁም ከኢምፔሪካል አንጻር ተቸሁ። በአጭሩ ዶክተሩ ያቀረበው ትክክል እንዳልሆነና፣ ለትግልና ለዕድገት የማያመች መሆኑን ነበር ለማሳየት የሞከርኩት። ታዲያ የኔን ጽሁፍ ካነበቡት ውስጥ ወደ ሃምሳ ያህል የሚጠጉት የስድብ ውርጅብኝ አወረዱብኝ። አንዳንዶችም በህይወታችን እንከፍላለን የሚል ዛቻ አስተላለፉ። እንገድልሃለን ማለት ነው። የእነዚህን ሰዎች የስድብና የማስጠንቀቂያ ውርጅብኝ ካነበብኩኝ በኋላ ለመረዳት የቻልኩት አንዳቸውም ቢሆኑ ዶ/ር ብርሃኑ ዳላስ ላይ ቀርቦ ያነበበውን ጽሁፍ ያላነበቡ መሆናቸውን ነው። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የእኔን ገንቢ ጽሁፍ ትችት አንብበው በደንብ ያልተረዱ መሆናቸውን ነው። በሶስተኛ ደረጃ፣ እንደነዚህ ዐይነት ሰዎች በሳይንስ ዓለም ውስጥ በምሁራን ዘንድ ከሚደረገው ክርክር ጋር ያልተዋወቁ መሆናቸውን ነው። በአራተኛ ደረጃ፣ አንድ የዶክትሬት ዲግሪ ያለውና የታወቀ ሰው ሊተች አይችሉም የሚሉ ናቸው። እንደዚህ ዐይነት ሰው አንድነገር ሲጽፍ ወይም ሲናገር ዝምብለህ አሜን ብሎ ከመቀበል በስተቀር ሌላ አማራጭ የለም የሚል ነው። በእነዚህ ሰዎች ዕምነት ፖለቲካ ህዝባዊ ወይም ህብረተሰባዊ ባህርይ ያለው ሳይሆን ለግለሰቦች የተሰጠና እነሱ የሚሉትን አንገትን ደፍቶ ዝምብሎ ማዳመጥ ነው። ከዚህ አስተሳሰባቸው ስነሳ እንደነዚህ ዐይነት ሰዎች ስልጣኔና የተሟላ ህብረተሰብአዊ ዕድገት ምን ማለት እንደሆነ በፍጹም አልገባቸውም ማለት ነው።
    ስለሆነም የእኔ መልዕክት ከእንደዚህ ዐይነቱ ጠባብ አሰተሳሰብና ግለሰቦችን ከማምለክ እንላቀቅ ነው። በዚህ አስተያየታችን የምንቀጥልና ሜዳውን ለጥቂቶች ግለሰቦች የምንለቅ ከሆነ የአገራችን ውድቀት እናፋጥነዋለን። እንደምትከታተሉት ከሆነ አገራችንን ለማጥፋት ደፋ ቀና የሚሉት የውስጥ ኃይሎች ብቻ ሳይሆኑ የውጭ ኃይሎችም ናቸው። እኛም ዝም ብለን የምንመለከት ከሆነ ለአገራችን ውድቀት ተባባሪ ከመሆን አናልፍም። በአሁኑ ጊዜ ይህንን እያደረግን ነው። የሚታዩ ነገሩችን ሁሉ እየካድን ነው። ህዝባችን እየታረደ ምንም ነገር እንዳልተካሄደ በአንድ ሰው ፍቅር ብቻ በመታወር አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ገብተናል። አገራችንን የሚያድናት ከአድርባይነት የፀዳ የተባበረ ትግልና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው። የዛሬው አገዛዝ ምናልባት ነገ ሊወድቅ ይችላል። ይሁንና ጥሎት የሚሄደው በቀላሉ ሊወገድ የማይችል ህብረተሰብአዊ ችግር አፍጦ አግጦ ይቀራል። ለተወሳሰቡ ህብረተስብአዊ ችግሮች ሳይንሳዊ መልሶች ለመስጠት የግዴታ በቂና የጠለቀ ጥናትና ዝግጅት ያስፈልጋል። ስለሆነ ሁሉም በተማረበት ፊልድ የጠለቀ ጥናት በማድረግ አማራጭ መፍትሄዎችን ማቅረብ አለበት። ለአድርባዮች መፈናፈኛ የማይሰጥ አዲስ የፖለቲካ ስልትና ሜዳ መፍጠር አለብን።
    ይህ ጸሀፊ ይህንን ክፍተት በመረዳት ከሃያ ዐመታት በላይ በተቻለ መጠን በተለይም እንደኢኮኖሚክስ በመሳሰሉት ነገሮች ላይ የጠለቀ ጥናት አካሂዷል። የተለያዩ አርዕስቶችንም የያዘ ድረ-ገጽ አዘጋጅቶ ለአንባቢያን አቅርቧል። በተጨማሪም የየቱብ ቻናልና ፖድካስት በመክፈት ለማስተማር ሞኩራል። መጽሀፎችም ጽፏል። የመጨረሻ መጨረሻ ይህ ሁሉ ልፋት ኪሳራን ከማድረስ በስተቀር በሰፊው በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ለመሰራጨት አልቻለም። የአብዛኛው ታጋይም ፍላጎት በቀን ተቀን ድርጊቶች ላይ ያተኮረ እንጂ ስትራቴጂያዊ በሁኑና አገርንና ህዝብን በሚያድኑ ነገሮች ላይ አይደለም። አሁንም እንደገና የማሳስበው ጊዜያችንን በከንቱ ከማባከን ይልቅ እንደነዚህና ሌሎች ትምህርት የሚሰጡ ድረ-ገጾችን መመልክቱ በጣም ጠቃሚ ነው። ይህ ጸሀፊ በዚህ እንዲቀጥል ከተፈለገ የግዴታ ዕርዳታ ያስፈልገዋል። እስካሁን ድረስ እንዲያውም ድርጅት አለን ከሚሉ በላይ ትምህርታዊ የሆኑ ነገሮችን ለማቅረብ ሞክሯል። ይህንንም ማወዳደርት ትችላላችሁ። ይህ ከሆነ ድረ-ገጼን በመመልከትና በማንበብ አስፈላጊውን ልገሳ እንድታደርጉ እጠይቃለሁ። ፕሮፌሽናል ስራ ብዙ ወጪን ስለሚጠይቅ አስፈላጊ ዕርዳታ ሲደረግ ብቻ ነው ጠለቅ ያለና አገር የሚያድን ጥናትና መፍትሄ ማቀረብ የሚቻለው። እንደገና የድረ-ገጹ አድራሻ፦ http://www.fekadubekele.com
    ከመልካም ትብብር ጋር፣ ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) fekadubekele@gmx.de

  5. ዶር በፍቃዱ ሊንክህን መተውህ መልካም ነው ከዩኒቨርስቲ የማይገኝ እውቀት ደብቀህብን እባክህ በተቻለ መጠን ብዙ ህዝብ ዘንድ እንዲደርስ አድርግ የተቻለንን ትንሽ ነገር ለመወርወር ፈልገን ይህንን መልእክት አገኘን “This recipient is currently unable to receive money.”
    አክባሪህ

  6. ውድ ወንድሜ አቶ ሰመረ፣

    ወደ Paypal ለመግባት በኢሜይል አድራሻ ቀጥታ መግባትና ማስተላለፍ ትችላለህ። እሱ ካስቸገረህ Introduction ጋ ሄደህ የባንክ አካውንቴ ታች ተቀምጧል ። በዚያ በኩል ማስተላለፍ ትችላለህ። fekadubekele@gmx.de በሚለው የኢሜይል አድራሻዬ በቀጥታ መግባት ትችላለህ። ለማንኛውም ለትብብርህ በጣም አመሰግንሃለሁ።

    ፈቃዱ በቀለ

  7. አቶ ሰመረ Donate የሚለውን ስትጫን በቀጥታ የPaypal አካውንቱ ይከፈታል። እዚያ ላይ ምን ያህል ለመለገስ እንደፈለግህ ያሳይሃል። አሁን ሞክሬው ነበር። ካለምንም ችግር ነው የተከፈተው።
    በድጋሚ ላማሰግንህ አላልፍም።

    ፈቃዱ በቀለ

  8. ውድ እህቶቼና ወንድሞቼ ለድረ-ገጼና ለዩቱብ ቻናል ገንዘብ ለመለገስ ሞክራችሁ እንዳስቸገራችሁ ለማወቅ ችያለሁ። እኔ እራሴ የራሴ ኮምፒዩተር ካልሆነ ጋ ሄጄ ስሞክረው ካለምንም ችግር ይሰራል። ማድረግ ያለባችሁ መጀመሪያ ድረ-ገጹን መክፈት፣ http://www.fekadubekele.com፣ ድረ-ገጹን ስትከፍቱ በስተቀኝ በኩል Donate የሚል ይታያል። Donate የሚለውውን ስትጫኑ ላይ ሊንኩ ጋ አሁን መለገስ ትችላላችሁ የሚል ይታያል። እሱን ከተጫናችሁትም በኋላ ወደ ታች ወረድ ብላችሁ በጀርመንኛ የብጫ ምልክት ያለበትSpenden(Donate) የሚል ይታያል። እሱን ስትጫኑ እንደመስኮት ነገር ይከፈታል። እዚያ ውስጥ የምትችሉትን ያህል በPaypal ማስተላለፍ ትችላላችሁ። ካለበሊዚያ በባንክ አካውንቴም ማስተላለፍ ትችላላችሁ። ሁሉም ነገር ህጋዊ ስለሆነ ምንም ችግር የለውም።
    ለመልካም ትብብራችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
    ፈቃዱ በቀለ

  9. Dr Fekadu I would do all my best this is the simple thing I can do for a reliable person like you. The time you spent to send us this information and knowledge is priceless many thanks again.

  10. There are many people who received millions and millions of money in the form of loan (the loan that they would not pay back) from the Government. People like Berhanu Nega and Hailu Shawel are reported to be one of those. They support repressive regimes for power and money.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share