ዛሬም እንደጥንቱ ወራሪው ትግሬ አማራንም አፋራንም እንደወረረ ነው። ምንም እንዃ የሃይል ሚዛኑ ለኢትዮጵያ መንግስት ቢሆንም መንግስት ይህን የበላይነት ሊጠቀምበት አልቻለም ወይም ፈቃደኛ አይደለም።
እንዲያውም የወያኔን ሽንፈት የመንግስት ድል መሆኑ ቀርቶ ተከታዩን ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ እየተልፈሰፈሰ ነው፣ ምናልባትም አቅጣጫውን የሳተ ወለል ካለ ባህር ላይ ያለ መርከብን ይመሰላል። መንግስት አቅም ስለሌለውም አይደለም፣ ሁሉም ስልጣን በአንድ ሰው እጂ የገባበትና የፈለገውን ማድረግ የሚችል መሆኑ ግልጽ ነውና። የመንግስት ትኩረት እንዲያውም ‘ያልበላውን ያካል’ እንደሚባለው በሌሎች ነገሮች ላይ ህኗል። ክፉ መንፈስ የተጣባው ወራሪው ሃይል እንደታጠቀና እያሸበረ እያለ ንጹሃንን ማፈንና ማሳፈን ተቀዳሚ ተግባሩ ሆኗል።
በተለይም ከወያኔ ባሻገር የኦሮሞ አክራሪወች የሚፈልጉትን ለማሳካት የፌደራል መንግስቱ የአመጽ ጅራፉን በአማራ ላይ እያጮኽ ነው። ለዚህም ህግ ማስከበር በሚል በደፈናው ህዝብን ማግበስበስ ጀምሯል። ያፍናል። በሃሳብ ቆነጠጡኝ የሚላቸውን ጋዜጠኞችም እንዲሁ አፍኗል። ፍርድ ቤት ቢለቀም ስራ አስፈጻሚው ቀልድህን አቁም በሚል አይነት መልሶ እስር ቤት ያጉራል። በሌላ በኩል ዛሬም ንጹሃን አማራዎች እየታረዱ ነው፣ ሸኔን እያጣፈን ነው ይበል እንጂ ሸኔ የሚታየው ሲስፋፋ ነው። እዚህ ላይ መጠየቅ ይቻላል፣ እውን መንግስት ሸኔ እንዲጠፋ ይፈልጋል? የሚለው ነው። ሸኔ መንግስት ውስጥ አለ በተዘዋዋሪ ሸኔ መንግስት አይደለምን?
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በወለጋ የተደረገውን ጭፍጨፋ እናጠናለን ሲል መንግስት አላስገባም ይላል፣ ምን አልባት ጥናቱ ብዙ ጣቶችን እንደሚቀስር ስንሚያውቅ አይደለምን? በስሜን አለ የተባለውን የሰባዊ መብት እረገጣ ገብቶ እንዲያጠና ሲፈቀድ ይህንን ትኩሱን የንጹሃንን እልቂት የከለከለ መንግስት በእርግጣም የሚፈራው ስላለ ነው። አልፎም ደም ከውሃ ይወፍራልና ለመታደግ ነው።
ይህ ሁሉ እንዳለ መንግስትና ወራሪው ሊወያዩ ነው የሚለው ወሬ እየነፈሰ ነው። መወያየቱ ባልከፋ ችግሩ ውይይቱ በምን ላይ ያተኩራል የሚለው ነው። አሁን ባለው የተምታታ አቋምስ መንግስት ታማኒነት አለው ወይ? በመልካም ቃላትና በእርቱእ አንደበት ኢትዮጳያዊነትን ሰምተን ሰማይ እርግጠናል። በትግባር ግን ያየነው ጽኑ እትዮጵያዊነትን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን የሚሸረሽሩትን ነው።
የሰሜኑ ጦር ደም ሳይደርቅና ወራሪውን ሃይል የቅጣት በትር ሳያርፍበት እንዲያውም የአማራንና የአፋርን መሬት ሙጥኝ ብሎ በተቀመጠበት ድርድር እንዴት ነው? ምን ለምስጠት ምንስ ለመቀበል? ወይንስ እንድሚወራው የኤልክትሪክ ሃይል፣ ስልክና ባንክን መልሶ በማቋቋም የጠላትን ሃይል ማጠናከርና ለዘመናት የትግሬ ጠላት ያለውን አማራ እንደገና ማስጨፍጨፍ? ይህ አዲስ አይደለም አማራ ለአርባ ሰባት አመታት ያህል በዚህ አረመኔ ቡድን እልቆ መሳፍርት የሌለው ግፍ ተፈጽሞበታል። ከታች የኦሮሞ የወያኔ ፈረሶች ከላይ ወያኔ አማራን በመሃል አጣብቀው እንድገና ዳቦ እሳት አንድደውበታል። በተለይ በአማራ ደም ጭምር ለውጥ መጣ ከተባለ በኋላ የደረሰው ግፍ ይቅርታ የሌለው የመንግስት ዝምታ ሲያልፍም ትብብር ለምንጊዜውም ቢሆን አይረሳም። በወለጋ ሰውች ሲጨፈጨፉ ጣቱን ያነሳ የለም፣ ሞትን እስከምንለምደው ድረስ የሰው ልጆች በገጀራም በቆንጨራም በካራም ታርደዋል፣ ተሰደዋል ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። በዚህ ውስጥ የኦሮሞ አስተዳደር የለበትም ማለት አይቻልም፣ ሸኔን እዚህ ያደረሱት እነሱው ናቸውና። ወራሪው ትግሬ በደቡብ ጎንደር፣ በስሜን ጎንደር፣ በወሎ ያን ያህል እልቂት ሲፈጽም የመከላዊ መንግስት በዝምታ አስጨፍጭፏል፣ ተጠያቂም ነው። ደብረሲና ላይ ሲደርሱ ለአማራና ለአፋር ብለው ሳይሆን ለስልጣናቸው ተንቀሳቅሰዋል። የተንኮሉና የአማራ ጠሉ ትርክት ተናንቋቸው ስለሚኖር ስልጣናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ጦርነቱ ሳያልቅ የአማራና የአፋር መሬት እንድተያዘ ጦርነት አብቅቷል አሉን። ዛሬም ወራሪው ትግሬ የሚያናፋው እኒህን መሬቶች እንደያዘ ነው።
ታዲያ ድርድሩ በፈቃዳቸው ለወራሪው የተውለትን መሬት ህጋዊ ለማድረግ ወይንስ ሌላ የማናውቀ ሂሳብ ቢኖር ነው። ታሪክ ምስክር ከሆነ ግን ይህ መንግስት ለአማራ መብትና ህይወት ግድ የለውም፣ የአማራ ሞት ምንም ስሜት የማይሰጠው መንግስት ለአማራ መሬት የሚያስብ ጭንቅላት አይኖረውም። በአማራ ክሰርት ከወራሪው ጋር ቢደራደር ምርጫው እንደሚሆን መጠራጠር አይቻልም።
ከወራሪው ትግሬ ጋር እደራደራለሁ በሚልበት በዚህ ወቅት የአማራንና የኢትዮጵያን ህልውና ያስጠበቀውን የአማራ ፋኖ በማሰደድ ላይ ነው። ይህ የወራሪውም የኦነጋውያንም ግብ ነው። ሰበቡ ደግሞ ወሮበልችም፣ ዘራፊወችን፣ቀመኞችን ህጋዊ ስርዐት ለማስያዝ ነው የሚል ነው። እየተደረገ ያለው ግን ሁሉንም ማጋበስ ነው። በተሰበሰብ ህዝብ መካከል ጥይት ተኩሶ ተንኮለኛውን ለይቶ ለመምታት መሞከር ነው። ጥይቷ ትመታለች የምትመታው ግን ያለአድለኦ ያገኘችውን ነው፣ ቀማኛ አትፈልግም፣ ነገሩ የመንግስትም አላማ ይኽው ነው፣ አማራን አንገት ማስደፋት፣ የኦነግንና የወራሪውን ጠላት አማራን ማዳከም እልፍ ሲልም ማጥፋት ነው። ቀማኞችንና ሰፈር አዋኪወችንማ ለማግኘትና ስርዓት ለማስያዝ የሚያስቸግረው ምን አለ? እስክቀበሌ ድረስ የሰገሰጋቸው ካድሬዎቹ ይህንን መረጃ መስጠት አቅቷቸው አይደለም።
የፈደራል መንግስት ሃላፊነቱን ካለመውጣቱ የተንሳ ዛሬ የአማራ ሚሊሽያ አማራን የመከላከል ጥሪ አስተላልፏል። በተጠቁበት ጊዜ ፍጻሜ ማግኘት የሚገባቸው የውራሪው ተዋጊዎች የጦርነት ከበሮ እየድለቁ ባሉበት ስዓት መንግስት አሁንም ይለማመጣል፣ የአማራ ህዝብ የጦርነት ገፈት ቀማሽ ይሆናል። ስለዚህ አሁንም እራሱን አሳልፎ እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነው። የአማራ ህዝብ እራሱን መከላከል እንድሚችል ጠላቶቹም ቢሆን በሚገባ ያውቁታል ለዚህም ነው ከሰሜንም ከደቡብም አማራውን ለማጥቃት የጋራ አሰራር የዘረጉት?
መንግስት ሆይ የትላይ ቆመሃል?
https://zehabesha.com/abiy-fails-to-facilitate-such-a-pragmatic-change-in-ethiopia-he-must-resign-2/