ባዶነት ሰለቸን !
ሁሉም የመጣዉ ሁሉ በአገር እና ህዝብ ስም ሲምል ሲገዘት ባዶ ካዝና ፣ ባዶ ዲሞክራሲ ፣ ባዶ ሰባዊ መብት አየያዝ ……. ይላል፡፡
ይቀጥል እና ራሱን አልፋ እና ኦሜጋ በማድረግ ብቸኛዉ የአገር እና ህዝብ አለኝታ ራሱ ብቻዉን የሠላም ፣ ዕድገት እና አንድነት ምሰሶ ማድረግ ይዳደዋል ፡፡
ይህም የአምልኩኝ ዳር ዳርታ መሆኑ ነዉ ፡፡ ራሱ እና ግብረ አበሮች የሚያደርጉት ሁሉ ትክክል እና የተቀደሰ ነዉ ብሎ ከማመኑ የተነሳ ጥዋት ያለዉን በረፋድ ለመካድ የለዉጥ አካል አድርጎ የለዉጥ ሀዋርያ መሆኑን እዩልኝ ስሙልኝ ይላል ፡፡
በህዘብ ስም በህዝብ ትከሻ እንደመዥገር ተጣብቀዉ አገር እና ህዝብ ሲያደሙ ፣ ሲያወድሙ እና ሲያቆስሉ የሚዉሉትን የዕድገት እና ብልጽግና ደቀመዝሙር ማድረግ ከባዶነት ይሻላል ብሎ ጆሮ ዳባ ልበስ በባዶ ለባዶ እንድንኖር እና ሳንኖር እየሞትን መኖርን በባዶ ተለማመድነዉ ፡፡
ይባስ ተብሎ ከሰሞኑ ዞትር ለአለፉት ዓመታት እንደሚሆነዉ በህዝብ ላይ በማንነት እና በአመለካከት ልዩነት እየተደረገ ባለዉ የዘር ፍጂት ስለሞቱ የህዝብ ወገኖች እና ዜጎች የህሊና ፀሎት ለማድረግ ፣ ቁጥራቸዉን ለማወቅ እና በአገር ባህል ፣ወግ እና ዕምነት ቀብር ለማድረግ ፈቃደኛ እና ኃላፊነት የሚወስድ አካል ለማግኘት አለመቻሉ በባዶ መኖር እና በባዶ መጀመር አባዜ እንደህዝብ ልማድ ሆኗል ፡፡
ለመሆኑ በማንነት ላይ ጥቃት ፣ ሞት ፣ ስደት እና የመሳሰሉት የጅምላ የወንጀል ድርጊቶች የአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማናጋት ሆኖ ተብሎ የሚከናወኑ እና በተደጋጋሚ ለረጂም ዓመታት የታዩ መሆኑ እየታወቀ እንደ ተዘረፈ የአገር ሀብት ፤ንብረት እና የይስሙላ ዲሞክራሲ(ህዝባዊ መንግስት)፣ ኢፍትኃዊነት……ከባዶ እንጀምር ማለት እንዴት ኢትዮጵያ ዓምላክን እና ዕዉነትን የሚፈራ ሠዉ ብታጣ ነዉ ፡፡
ዜጎች በማንነታቸዉ ሲሞቱ ፤ሲገለሉ፤ ሲገደሉ …..ለዓመታት እያየን ይህ የአገር ጉዳይ ፣ የህዝብ ጥያቄ…..አይደለም እየተባለ መኖር ከዚህ በላይ ባዶነት ምን ይምጣ ፡፡ ዕዉነት ኢትዮጵያ ዉስጥ በማንነት የደረሰዉ ግፍ እና መከራ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ቢቆጠር ከዚህ በላይ በዓለም ላይ በሰዉ ልጆች በራሳቸዉ አገር ፣ምድር እና ግዛት እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ኢትዮጵያዉያን እና ዐማራ ላይ የደረሰዉ ሰቆቃ ከዕዉነት በላይ ምን ሊሆን እና ማን ሊናገር ይችላል፡፡
ከባዶ መነሳትን ክህደት እና በአገር እና ህዝብ ላይ የማላገጥ ሴራ መሆኑን አዉቀን ሁላችን ለራሳችን እና ለአገራችን የባዶ ጅምር ነጋዴዎችን በቃ ልንል ይገባል ፡፡
ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ባዶ ሆነዉ አያወቁም ባዶነትን ለከንቱ ዉዳሴ ትረፍ የሚገለገሉበት የህዝብን እና የአገርን አንጡራ ሀብት እና ንብረት ለግል እና ለቡድን ለሚመዘብሩት መንደርደሪያ መንገድ መሆኑን ይህም የባዶነት ጭምብል እጂ እጂ ማለቱን እና እንደሰለቸን ሊያዉቁት ይገባል፡፡
ነፃነት ወይም ሞት !
ሞት ለፀረ ኢትዮጵያ!
Neilos Amber