June 23, 2022
12 mins read

ሲና ዘ ሙሴ : የኢትዮጵያ ዘውጋዊና ቋንቋዊ ሥርዓተ መንግሥት እሥካልተቀየረ ጊዜ ድረሥ፤ የንፁሃን እልቂት ይቀጥላል 

Abiy killer 1እንሆ በኃይል ፣ በጠመንጃ ፣ በእሥር እና በማሠቃየት ከገዛን  ከወያኔ ኢህአዴግ በወረስነው ፣ የዘውግ እና የቋንቋ ፖለቲካ የተነሣ ዛሬም አበሣችንን እና መከራችን አላባራም  ።  ቋንቋዊው ፖለቲካ አብረን  በፍቅር ማደጋችንን አሥረሥቶ ፣ ሁልህም በየቋንቋ ወገንህ በማለቱ ፣ሰውነታችን ተደምስሶ በአባታችን ቋንቋ ፣ አንተ እንትን…ነህ  እየተባባልን ዜግነታችንሰ ረስተን የጎሪጥ እየተያየን መኖር ከጀመርን እንሆ 31 ዓመት ሆነን ። ( የመለያየታችን  ፣ የመጠላለፋችን  ፣ የመጠፋፋታችን ምሥክሮችም   ባንኮቻችን ሆኑ ።   )

ባለንባት ፣ ፈጣሪ በፈጠራት መሬትም አንዳችን በለመብት ና የበላይ አንዳችን መብት አልባና የበታች ሆነን አረፍነው ። በአሣዛኝ መልኩ ። ሰዎች ከሞተ እንሥሣ ቆዳ እንኳን አነሥን ።  የሞተው እንሥሣ አያ በሬ ፣ በየወገንህ ሲባል እከብቶች በረት ነው የተገኘው ። እኛ ግን በሰዎች በረት እንኳን መገኘት አልቻልንም ።   አንደ መቶ ዓመት  የሞላው የበሬ ቆዳ ግን ” በየወገንህ ! ” ሲባል ፤  ከብቶች በረት ተገኘ ። አሉ ።

እናም፣ ከከብት አንሰን ፣ በሥግብግቡ እና በአትድረሡብኝ ባዩ በቋንቋ ፖለቲካችን ዛሬም ደም እንባ አለቀስን  ። ዛሬ  በምእራብ ወለጋ ” ጊንቢ ”  የሆነውም ሆነ  ፤ ትላንት  ” በማይካድራ ” የተፈፀመው ፣ ተመሣሣይና ያው የሆነ ድርጊት እኮ ነው ።

አሜሪካን ውሥጥ አንድ እብድ ነው ህፃናትን ዒላማ አድርጎ ግንባር ግንባራቸውን እያለ በትምህርት ገበታቸው ላይ የገደላቸወ ። ኢትዮጵያ ውሥጥ ደግሞ ያለማጋነን በመቶሺ የሚቆጠሩ የቋንቋ ፖለቲካው ያሳበዳቸው ደመ ቀዝቃዛ ነፍሰ ገዳዮች በግልፅ በአደባባይ የጦር መሣሪያ ይዘው ሲጎማለሉ እና ሰዎችን በዘፈቀደ ሲረሽኑ በተደጋጋሚ እንደ ፊልም በመታየቱ ዓለምን ጉድ እያሰኘ ነው ።

ይኽ የአራዊት እና የእብዶች ተግባር    በወያኔ ትላንት በማይካድራእና በወረራቸው የአማራ ክልሎች ሁሉ ተፈፅሟል ። በወለጋ እና በመላው ኦሮሚያ ደግሞ  በሺ የሚቆጠር የሰው ደም የጠማው እብድ በየጫካው እና እብዶችን ባቀፉ ዘረኞች ጉያ ውሥጥ ተመሳስሎ እየተርመሠመሠ  ሰላማዊ ሰዎችን ፣ ጨቅላ ህፃናትን ጭምር ቃላት ሊገልፁት በማይችሉት ጭካኔ በመግደል ላይ ይገኛል ።

እነዚህ በግፍ እየተጨፈጨፉ ያሉ  ዜጎች ፣ ሥለ ወቅታዊው ፖለቲካ ፣ በግብፅ ሥለሚከፈላቸው የአገራችን አውሬ እና እብድ ነፍሰ ገዳዮች  ተልዕኮ፣ አንዳችም የሚያውቁት ነገር የለም ።  ህፃናቱ እሥከ ለፍቶ አደር ቤተሰቦቻቸው ያላቸው ተልዕኮ የመኖር  ብቻ ና ብቻ ነው ።

እነዚህ የመኖር ተልዕኮ ብቻ ያላቸው ሥለ ዓለም የማያውቁ ፣ ፍቅር የሆኑ  ህፃናቶች እና እናቶቻቸው ህይወትን ለማስቀጠል እንደተቃቀፉ፤ ሰውነታቸውን በሆዳቸው በመለወጥ ፣ አውሬዊ ኑሮ በጀመሩ እና አውሬ በሆኑ ፍጥረታት በጭካኔ ተገደሉ ። አዛውንቶች ፣ አርሶ አደሮች ፣ ላፍቶ አደሮች ፣ በገዛ ጎጆቸው ፣ በገዛ ቀያቸው ፣ በገዛ መኖሪያቸው ውሥጥ ፤ ኑሮን ለማሸነፍ ቀና ደፋ በማለት ላይ እንዳሉ ፣ በድንገተኛ የጦር መሣሪያ ጥቃት ህይወታቸውን ተቀሙ ። ቤታቸው በእሣት ገየ ። ንብረታቸው ተዘረፈ ። ይኼ የጭካኔ ድርጊት ሲፈፀም መንግሥት የት ነበረ ? …

ነገርን ነገር ያነሰዋል እንዲሉ ፣ የማህበራዊ አንቂዋ የመሥከረም እና የፍትሕ ና የሰብዓዊ መብት ተሞጋቹ የተመሥገን ደሣለኝ መታሰር ዋናው ሰበብ  ፣ ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ በመሆን ፣እውነታውን ለአለም እንዳያሳውቁ ለማድረግ ከሆነ ፣ ይኽ የጊንቢ ጭፍጨፋ አሥቀድሞ የተወጠነ ከመሆኑም በላይ የትኞቹ እንደሆኑ ባናውቅም አራዊቶቹ ነፍሰ ገዳዮች  በመንግሥት ባለሥልጣናት ( በኦሮሚያና በፊደራል ውሥጥ ባሉ ) ትበብርና  ሽፋን የሚደረግላቸው እንደሆነ ለመጠርጠር እንገደዳለን ። የኢትዮጵያ ደህንነትም “ የት  ነው ያለኸው ? “ ብለን እጠይቃለን ።  “ ሥራህ  አሥቀድሞ ሽብርን መከላከል እንጂ ንፁሐንን በማሠር ያልፈፀሙትን ወንጀል ሠርቻለሁ ብለው እንዲያምኑ ፣ በእሥር ብዛት መሥገደድ አይደለም ።  ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊያንን ከጥቃት  መከላከል እንጂ !… “ እንላለን ።

289398998 1102317780323440 2312467090821884603 n

ይኽ ሁሉ ኩንን ድርጊት እየተፈፀመ እና እየሆነ ያለው መንግሥት በሚከተለው ፣ የቀደሞው የፋሺሥታዊው ኢህአዴግ ቋንቋዊ ና ጠባብ ብሔርተኛዊ የፖለቲካ መንገድ ምክንያት ነው። ይኽንን መንገድ መንግሥት እርግፍ አድርጎ ትቶ ወደ ሠለጠነው ዓለም ሰውኛ መንግሥታዊ አሥተዳደር እሥካልመጣ ጊዜ ድረሥ መተራረዱ ይቀጥላል ። ገና ለገና ከዘውጌ ቅርጫት ከወጣው ቅንጦት ይቀርብኛል በማለት ህዝብን የሚያጨራርሰውን የተጣመመውን የፖለቲካ አካሄድ ለማሥተካከል አለመፈለግ በራሱ የሚያሥከፍለው ዋጋ እጅግ የሚያሥቆጭ ይሆናል ።

ቁጭቱም  ፣  የደርግ የደህንነት ኃላፊ የነበረው ፣ የከንፈር እንቅሥቃሤን ከርቀት በማየት ሰው ምን እንዳለ የሚያውቀውና በአሥመራ የደርግን ባለሥልጣናት መረጃ እንዳይሰጡ ሲያስጠነቅቅ  ”  የማሃል አገር ሰው ሴትና ሥጋ ይወደል ። ከሴትና ሥጋ ተጠንቀቁ ። ” ያለው። በኦሮማይ የበዓሉ ግርማ መፀሐፍ ለጥቅስ ይበቃለታል ።  ኮ/ል ተሥፋዬ ወልደሥላሤ  እንደተቆጨው ቁጭት  ። አይነት ይሆን ይሆናል ።

ሰውየው ፤ ከደርግ ውድቀት በፊት ፣ አገር የቀይ ባህር ግዛቷን እንዳታጣ ፣ ታላቁ የሶቬት ህብረት ግዛት እንደተንኮታኮተ ፣ ከሲአይኤ ጋር በመተባበር ፈጠን ብሎ በኩዴታም ቢሆን ሥርዓቱን በመቀየር፣ ከህውሃት ጋር እርቅ በማውረድ ፣ ለሻቢያም የራሥ ገዝ ሥልጣን በመሥጠት ፣አገሪቱ ተረጋግታ የካፒታሊሥት የኢኮኖሚ ሥርዓት እንድትከተል ማድረግ ይችል ነበረ ። በወቅቱ አንድ ኃያል አገር አሜሪካ   በመሆኖም ቢያንሥ  ኢትዮጵያ በአሜሪካ ጉያ ውሥጥ ገብታ ህዝቧ በቀን ሦሥት ጊዜ የሚበላበትን መንገድ ማመቻመች ይቻል ነበር ። የደህንነቱ ቁንጮ ሰው ፣ ይኽንን ማድረግ ሲችል ባለመቻሉ ደርግ ኢትዮጵያን አኮሥሦ ያንን ሁሉ መሥዋትነት ከንቱ አደርጎ የእቃ እቃ ጨዋታ በሚመሥል መልኩ ፣ለሞተውና ለቆሰለው ቀርቶ በቁም ላለው ወታደር ምንም ሣይገደው ፤   ሥልጣኑንን እንደዋዛ አሥረከበ ። ያውም አገርን ከድቶ ወደ ውጪ አገር በመፈርጠጥ ። በኢጣሊያን ኢንባሲ በመመሸግ ።

የደርጉ የደህንነት ሹም     ፣ ወያኔ እንደገባች አቀማጥላ ይዛ ፣ በቂ መረጃ እና ሥልጠና ከሰውየው ካገኘች በኋላ ፣ በመዋቅሩ ውሥጥ ያሉ ጠንካራ የሥለላ ተግባር ፈፃሚዎችን ብቻ አሥቀርታ ፣ እርሳቸውን እና ቁጮ የደርግ ባለሥልጣናቱን ወደ እሥር ቤት ወረወረቻቸው ። ግለሰቡም እንደ ተበሳጩ ህይወታቸው አለፈ ።

ዛሬሥ ? የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒሥቴር  አብይ አህመድ ሁሉን ሥልጣን ጨምድደው ይዘው ሲያበቁ ፣ ለሥልጣናቸው ቀጣይነት በመሥጋት ብቻ ፣ ከወያኔ የከፋፍለህ ግዛ መንገድ ያለመውጣታቸው እሣቸውን ብቻ ሣይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ዘግናኝ እና አሠቃቂ የሆነ ዋጋ አያሥከፍለውምን?  በዘር ፣በቋንቋ ፣በወንዘኝነት ላይ የተመሠረተ ሥርዓት ደም የሚያቀባባ እንጂ በፍቅር የሚያሥተቃቅፍ ከቶም እንዳይደለ ታሪክ በየዘመኑ  ደጋግሞ አልነገረንምን ? …

ሲና ዘ ሙሴ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

Go toTop