ይድረስ ለኦሮሞ አባቶችና ልሂቃን – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ምን ብዬ እንደምጀምር ጨንቆኝ ከወረቀቱ ጋር ተፋጥጬ ብዙ ቆየሁ፡፡ ግን መጀመር አለብኝና እንደምንም ጀመርኩ፤ ሰላምታየን ላስቀድም ታዲያንም፡፡ ደግሞም እንኳን ለጠንቀኛዋ የግንቦት ወር በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ዘሩ በያይነቱ ተዘራ፡፡ ቡቃያው አደገ፡፡ ሰብሉም ጎመራ፡፡ እነሆ የዐውድማው ወቅት ደረሰ፡፡ ዘሪውም ወቂውም ደስ ይበለው፡፡ ታዛቢም ይታዘብ፤ ታሪክም ይመዝግብ፡፡ ሁሉም ሆኖ አንድ ነገር ብቻ ቀረ – የኢትዮጵያ ማይቀር ትንሣኤ፡፡

ኢትዮጵያን በተለይም አማራን የማጥፋቱ ዕቅድ ከመቶዎች ዓመታት በፊት በኃያላኑ የስለላ ድርጅቶች ተጠንስሶ፣ በሀገር ውስጥ ከሃዲዎችና ሆዳሞች ተደግፎ ይሄውና ወደመገገባደጃው ተጠግቷል፡፡ ኢትዮጵያን ስለማጥፋት ዕቅድና ዓለም አቀፍ ሤራ አሁን አንተነትንም፡፡ ብዙ ስለተነገረለት ግልጽ ነውና፡፡ በዚህ ታላቅ ሤራ ተሣታፊ ከሆኑት ወገኖች መካከል ግን በአሁኑ ወቅት ወጧ እንዳማረላት ሴት ከወዲያ ወዲህ በደስታ ሰክረው የሚያደርጉትን ያጡትን የኦሮሞ አክራሪዎች በተመለከተ አጭር ማስታወሻ መጻፍ ፈለግሁ፡፡ በመሠረቱ ምንም መናገር  ባልተገባኝ፡፡ ግን ጥቂት መሃል ሠፋሪዎችንና ቅርብ ተመልካቾችን ማዳን ከቻልኩ መጻፌ ካለመጻፌ ይሻላል፡፡ “ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል” ይባል የለም? እንጂ የሀገራችንን ችግር በመዘርዘርና መፍትሔዎችንም በመጠቆም ብዙ ባጅተናል፡፡ ሰሚ በመጥፋቱ ግን የተባለው ሁሉ ላይቀር ግድ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ከንጋት በፊት የመጨረሻ ያልኩትን አስተያየት መቀጠሌ ነው፡፡ በትግስት ተከታተሉኝ፤ የሰማችሁም ላልሰማ ወገኔ አድርሱልኝ፡፡

ውድ የኦሮሞ አባቶችና ወንድሞች!

እንደጨለመ የቀረ ሌሊት የለም፡፡ እንደቦረቀ ዝንታለሙን የቆዬ ጥጃም ታይቶ አያውቅም፡፡ የወጣ መውረዱ፣ የወረደ መውጣቱ ያለና የነበረ ነው፡፡ ይህን እውነት ማንም ይረዳዋልና ለማስታወስ ያህል እንጂ አዲስ ነገር እንዳልተናገርኩ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ልጆቻችሁና ልጆቻችን የኦሮሞ አክራሪ ወጣቶች ከአራት ኪሎ እስከ ደምቢዶሎ ምን እየሠሩ እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ አገር ጠባቸው ይሆኑትን አጥተዋል፡፡ በጥላቻ ነፍዘው፣ በዘር ፖለቲካ ሃሽሻዊ መርዝ ደንዝዘው፣ በሀብትና በሥልጣን ስካር ናውዘው የሚሠሩትን ያጡት በኦሮሙማ ፍልስፍና ህልም አይባል ቅዠት የሚቅበዘበዙት አክራሪ ኦሮሞዎች አሁን አሁን በተለይ ኅሊናቸው ታውሮ የሚያደርጉትን አጥተዋል፡፡ በመሆኑም ተፋቅሮና ተከባብሮ እርስ በርስ እየተጋባና እየተዋለደ የኖረውን የኢትዮያ ሕዝብ ከወያኔ ዘመንም በከፋ ደረጃ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በጎጥ ከፋፍለው ሀገራችንን የለየላት ሦርያና የመን አድርገዋታል፡፡ በእግዚአብሔር ልዩ ቸርነት እንዳለን ተቆጠርን እንጂ በመካከላችን እንደገባው ንፋስ ቢሆን ኖሮ አንድም ቀን ማደራችን አጠራጣሪ በሆነ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትኋኑን ለማጥፋት ቤቱን ማቃጠል አይኖርብንም! – የኢትዮጵያን ነቀርሳዎች ለማከም ኢትዮጵያ መፍረስ የለባትም!!!

ውድ ወገኖቼ! ምድር ጠባቸው ለታዛቢ እስኪገርም ድረስ የእግዜሩን ዐይን እየወጉ ያሉ ባለጊዜ ልጆቻችንን እንምከር፡፡ የዱባ ጥጋብ የትም እንደማያደርስ እንንገራቸው፡፡ አሁን የያዙትን መሣሪያ፣ አሁን የተቆናጠጡትን ሥልጣን ለውድመት መጠቀማቸውን እስከቀጠሉበት ድረስ ጊዜ ተለዋዋጭ ነውና የዕኩይ ተግባራቸው ውጤት ለአጠቃላዩ የኦሮሞ ሕዝብም እንደሚተርፍ በግልጽ እናስረዳቸው፡፡ ለኦሮሞ ማኅበረሰብ እያሰጡት ያለው ያልተገባ ስም በአብሮ ኗሪነቱ ለሚታወቀው ኦሮሞ በፍጹም አይመጥንም፡፡

በሕወሓት ጦስ ትግራይና ሕዝቧ በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ የምናውቀው ነው፡፡ ጥጋብን ያለመቆጣጠር ችግር የሚያስከትለው መዘዝ ከፍተኛ መሆኑን ከደርግና ከወያኔ መማር ካልተቻለ የአእምሮ ጤንነት ተዛብቷል ማለት ነውና ችግሮች ከአሁኑ በባሰ ሳይከፉ እንመካከር፡፡ ጥጋብ ወደራብ መንዳቱ ዱሮም ነበር፡፡ አንዳንድ ጥጋብና ዕብሪት ግን በርሀብ ብቻ አይወሰንምና በብርቱ እናስብበት፡፡

ዛሬ እርግጥ ነው – ኢትዮጵያ የለችም፡፡ ትናንት በወያኔ እግር ከወርች ታስራ ለቅርጫ የቀረበችው ኢትዮጵያ ዛሬ ለይቶላት በኦሮሙማ አስተሳሰብ በሚነዱ ኃይሎች በአራት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወያኔን ዕጥፍ ድርብ በሚያስከነዳ ጭካኔና መሪር ፈርዖናዊ አገዛዝ ሀገራችን እንጦርጦስ እየወረደች ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ከኦሮሙማ አገዛዝ የለየለት ሲዖላዊው የሠይጣን አገዛዝ ሳይሻል አይቀርም፡፡

የነገ አሸናፊን ከአሁኑ መናገር ለብዙኃን እፎይታን ቢሰጥም በአንዳንዶች ዘንድ ወቀሳን ማስከተሉ አይቀርም፡፡ እናም እርሱ ይቅር፡፡ የሆነው ቢሆን ግን የእውነትንና የግፍ ሰለባዎችን አሸናፊነት አለመመስከር የታሪክን ሂደት፣ የፈጣሪንም ፍትኃዊ ፍርድ እንደመካድ ይቆጠራልና ይህን ሃቅ በስሱም ቢሆን ማስታወሱ አይከፋም፡፡ እናም እንወቀው እውነት በመጨረሻ ታሸንፋለች፡፡ …

ኦሮሙማዎች እጅግ ነብርረዋል፡፡ አይዟችሁ ያላቸው ለመኖሩ ግልጽ ነው፡፡ ግን ያ ኃይል አሁን በዩክሬን ጉዳይ ዳር ሆኖ ከማጨብጨብና “በርቱ ግፉበት” ከማለት በዘለለ የብዙ ሰው ሕይወት ሲረግፍና በርካታ ንብረት ሲወድም አላስጣለም፡፡ ያ ዓለምን ለብቻየ ጠቅልዬ እንዳሻኝ መግዛት አለብኝ ብሎ የሚያምን ኃይል ጦርነትን መለኮስና ለጦርነት የሚውሉ ግብኣቶችን ማቀበል እንጂ በራሱ የትኛውንም ጦርነት ሲዋጋ አይስተዋልም፡፡  ያ ኃይል ባይኖር ኖሮ ዓለማችን ግሩም የመኖሪያ ሥፍራ ልትሆን እንደምትችል የብዙዎቻችን ግምት ነው፡፡ ግና አልታደልንም፡፡ በጥባጭ ሳለ ደግሞ ጥሩ ውኃ አይጠጣም፡፡ ስለሆነም ዩጎዝላቪያን፣ ሶማሊያን፣ ሦርያን፣ አፍጋኒስታንን፣ ሊቢያን፣ በጥቅሉ መላው ዓለምን በመሣሪያውና በተፅዕኖው ሥር አውሎ ምድርን የመከራና የስቃይ መናኸሪያ አድርጓታል፡፡ ይሁን፡፡ ቀድሞ የተነገረው የመጨረሻ ዘመን ምልክቶች መገለጫ በመሆኑ ወደላይኛው ከመጮህ ውጪ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ቢሆን የዚህም ጣዖታዊ ኃይል ክንዶች የሚሰባበሩበት ጊዜ እየቀረበ መሆኑን መጠቆም እምብዝም ሟርተኛ አያስብልም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውድ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች "እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል አደረሳችሁ!" ጌታቸው ወልዩ (ከሜክሲኮ ባህረ-ሰላጤ)

ወደሀገራችን ስንመለስ የተለዬ ነገር አናገኝም፡፡ ሁሉም እንቅስቃሴዎቻችን ከዐውሬው የታለመና የታቀደ እንቅስቃሴ ጋር የተሰናኙ ናቸው፡፡ አሁን አሁን የሀገራችን ሁኔታ ሲቃኝ ነገሩ ሁሉ የህልም እንጂ የእውን አይመስልም፡፡ መሪ የሌላት ብቻ ሳትሆን መሪዋ ፀረ-ሀገርና ፀረ-ሕዝብ የሆነ ሰው ሆኖ ስትመለከት ከህልምም በላይ ነው፡፡ ባለሥልጣኖቿ ሁሉ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ሀገር ሆነው ስታይ ትደነግጣለህ፤ ትጨነቃለህም፡፡ የፖለቲካ ተሹዋሚው በአብዛኛው ጭንቅላቱን ሆዱ ውስጥ ሸጉጦ በሆዱና በዘር ማንነቱ ብቻ ሲያስብ ስታይ ሰው ሆነህ በመፈጠርህ ዝቅ ሲልም ኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጠርህ ራሱ ትሸማቀቃለህ፡፡ ሀገር(ህ) ውስጥ ሀገር አልባ ሆነህ የበይ ተመልካችና ከዚያም በከፋ በማንነትህ ስትገደልና ከሥራም ከመኖሪያ ሥፍራም ስትፈናቀል “የት ነው ያለሁት?” በሚል ክፉኛ ትጨነቃለህ፤ መፈጠርህንም ትራገማለህ፡፡ ሰው መሃል ሆነህ ሰው የሚናፍቅህ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይመስለኛል፡፡

ግን የዛሬው እውነት ነገም ይቀጥላል ማለት አይደለም፡፡ ነገም ሌላ ቀን መሆኑ ተደጋግሞ የሚነገረው ለዚህ ነው፡፡ ታላቅ አውነት ነው፡፡ እናም ነገ ላለማፈር መሠረቱ የሚጣለው ዛሬ ነውና በስም የጠቀስኳችሁ ወገኖቼ ይህችን ቀጭን ጊዜ በሰላም እንድናልፍ ልጆቻችንን ምከሩ፡፡ ኦቦ ደቻሣ ልጅዎን ይጥሩና ስለቀደመችዋ የጋራ ኢትዮጵያ ይንገሩት፡፡ ጠላት ለራሱ ዓላማ ሲል ጭንቅላቱ ውስጥ የሸቀሸቀበትን መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ውሸት መሆኑን ያስረዱት፡፡ በሀገራችን ጡት ቆራጭ እንዳልነበረም ይግለጹለት፤ ጡት ቆራጭና ጽንስ ከእናት ማኅጸን አውጥቶ የሚበላ፣ ሰውን በግፍ ከገደል በኋላ ዘቅዝቆ የሚሰቅልና ያም አልበቃው ብሎ ሬሣውን በመኪናና በሞተር የሚጎትት ሰይጣናዊ ትውልድ የመጣው አሁን በዚህ ዘመን መሆኑን ይንገሩት፡፡ በዳይና ተበዳይ ካለም ሁሉም ሁሉንም በድሏል እንጂ እንዳሁኑ ዘመን በዘር የተቧደነ ጎራ በሌላ ዘር ላይ ተነስቶ ጥፋትና ውድመትን እንዳላስከተለ ይመስክሩለት፡፡ ኢትዮጵያን የገዙት ነገሥታትና የጦር አበጋዞች በአብዛኛው ኦሮሞዎች እንደነበሩ የትናንትናዎቹን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤንና መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን በመጥቀስ ያስረዱት፡፡ ውድ ሰርቤሣ – ልጅህን ጫልቱን ጥራትና አጠገብህ አስቀምጠህ ለኦቦ ደቻሣ የጠቆምኩትን እያነሳህ ምከራት፡፡

በተረፈ አንድ ጄኔራልና አንድ ኮሎኔል ማፈን፣ በአንድ በኩል የራስን ወምበዴ እየቀለቡና ዘመናዊ ጦር መሣሪያ እያስታጠቁ በርሱም አማካኝነት ማጥፋት የሚፈልጉትን ነገድ በየቦታው እያስፈጁ በሌላ በኩል ከመኖሪያ አካባቢው ያልወጣን የአንድን ነገድ አለኝታ ኃይል ማሰርና ማንላታት፣ ጥቂት ጋዜጠኞችንና የሰብኣዊ መብት ተማጋቾችን ደብዛ ማጥፋት ወዘተ. የነጻነት ትግልን ያጠናክራል እንጂ አንድ ጋት ወደኋላ አያስቀረውም፡፡ በማፈንና በመግደል ፍላጎት የሚሣካ ቢሆን ኖሮ ከደርግና ከወያኔ በላይ ለሽዎች ዓመታት የሚገዛ ባልነበረ፡፡ ከሚያጥበረብሩ የቀን ቅዠቶች እንላቀቅ፡፡ የሚታይ የሚመስል ሁሉ ውሸት ነው፡፡ ያለን የሚመስለን ሁሉ የለንም፡፡  ስሜታዊነት ማንንም ጠቅሞ አያውቅም፡፡ ምክንያታዊነት ግን ትልቅ ምርኩዝ ነው፡፡ የማንኛውም ዘመን ሰው መሆን ዕድለኛነት ነው፡፡ በየትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው የውር ድምብር አካሄድ እየተመሩ ዛሬን መክበርና ነገን ማበላሸት ከጤናማ ሰው አይጠበቅምና በጊዜያዊ ድል ስካር ያበዳችሁ ኦሮሞ ወንድሞቼ ወደኅሊናችሁ ተመለሱ – ብዙም ሳይረፍድ ታዲያ፡፡ እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝን እንደሚያስከትል ካላወቅን ተሳስተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህወሃት ሊወድቅ ነው (ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!) - በያሬድ አይቼህ

ሳይወለድ የጨነገፈው ብአዴንም አያዋጣችሁም፡፡ በአንድ ጥፊ የሚዘረር ሰካራም እንኳንስ እናንተን የቁርጡ ቀን ሲመጣ ራሱንም አያድንም፡፡ … ይሄ ሰውን ማፈናችሁን የተበላ ዕቁብ የሕጻናት የዕቃቃ ጨዋታ ደግሞ በፈጠራችሁ ተውት፡፡ የሚያስቅ ግን ጊዜ ያለፈበት ድራማ ነው፡፡ ከአባታችሁ ከወያኔ ተማሩ እንጂ! የዘሩትን ማጨድ እንዳለ እንዴት ዘነጋችሁት? አንድ ተፈራ ሲታፈን ሽህ ተፈራዎች ወደ አደባባይ እንደሚወጡ ካላወቃችሁ፣ አንድ ጎበዜ ሲታፈን ሽህ ጎበዜዎች ወደ በረሃ እንደሚተሙ ካልተረዳችሁ አእምሯችሁ በርግጥም ሥራውን አቁሟል ማለት ነውና ወገን ካላችሁ አሁኑኑ ወደሀኪም ቤት ይዟችሁ ይሂድ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ በኦሮሙማ ፖለቲካ ጥርሳቸውን ተወቅረው ከሚስቁ ወገኖች መካከል አንዱ መሆኔን ልደብቅ አልፈልግም፡፡ የሚሠሩት ሁሉ የሚያሳዝነውና የሚያስለቅሰው እንዳለ ሆኖ አብዛኛው ግን በሣቅ ጦሽ የሚያደርግ ነው፡፡ በዋና ከተማ ውስጥ በመከላከያ መኪና አሥርና አሥራ አምስት እንደነገሩ የለበሱ ከዕውቀትም ከትምህርትም የተፋቱ ባለጊዜዎች አንድን ሰው አፍነው ሲወስዱ ይታያችሁ፡፡ ይህ ሕጻንነቱን ሳይጨርስ የመርከቢቷ መሪ የጨበጠ ጎልማሣ ሰውዬ ገና ብዙ ጉድ ሳያሳየን አይቀርም፡፡ እርግጥ ነው – እርግጥ ነው – መንገድ ጠራጊው ሲሄድ ግሩም ዘመን ይተካል፡፡ ይህንንም በኩራት እንመሰክራለን፡፡ አሸናፊውንም እናውቃለን፡፡ የዚያ ሰው ይበለን፡፡  …

1 Comment

  1. Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

    Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

    Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

    As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

    So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

    The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

    In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

    Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

    Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

    It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

    Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

    Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

    For us, Oromos, conederation is also the answer.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share