* በሀገሬ በኢትዮጵያ ግን ከቶም ተስፋ አልቆርጥም !!! – መስፍን ማሞ ተሰማ

በኢትዮጵያችን ላይ የተደፋው ርኩስ የመጠፋፋትና የጥላቻ ፣ የጭካኔና የዘረኝነት መንፈስ መገለጫው ዓይነቱና መከሰቻው ስፍራ ከጎንደር እስከ ባሌ ከቤንሻንጉል እስከ ሐረር የዘለቀ ሲሆን ፤ ከሰውነት እሳቤና ርህራሄ ውጪ በመሰል ኢትዮጵያዊ ወገንና አካል ላይ ሳያባራ ላለፉት አራት ዓመታት ቀጥሏል።  መራሄ መንግሥቱ መገዳደሉ መፈናቀሉና ውድመቱ በራሱ ጊዜ ሲበቃው ይቆማል ሲል እጁን ከታጠበ ሰንብቷል።

አእላፍ ግን ህይወታቸውን አጥተዋል፣ እያጡም ናቸው።  በቢሊዮን ብር  የሚቆጠር ንብረት መውደሙ ቀጥሏል። በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብም በገዛ ሃገሩ ስደተኛና ተፈናቃይ ሆኗል። ረሃብና በሽታ ስር  ሰደዋል። አሸንፈናል የተባለው የሰሜኑ ጦርነት ትርጉም አጥቶ እና እንደ ዱቄት በትነነዋል የተባልነው ናዚስት ወያኔ በተደራጀና በጎለበተ ወታደራዊ ቁመና የአማራና የአፋር ክልልን በመሰረተ ልማትና በዕድገት 30 ዓመት የኋሊት መልሷቸው ህዝቡን አፈናቅሎ ዘርፎና የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሞ ወደ ጎሬው ሲመለስ  ያልተቋጨው ጦርነት ለአፋርና ለአማራው ህዝብ ማባሪያ ያጣ ሰቆቃ እንዲሆን ሆን ተብሎ ተትቷል። ዱቄት ሆኗል የተባልነው የኢህአዴግና ኢህአዴጋውያን አባት ናዚስት ወያኔ ከነሙሉ አቅሙ ከነዘግናኝ ወንጀሉ ከብልፅግና መንግሥት ጋር ለእርቅና ለሥልጣን በአንድ እጁ መትረየስ በሌላ እጁ አንቀፅ 39ኝን ይዞ ለድርድር ሽርጉድ እየተባለ ነው ። ያለ ጦርነት መኖር የማይችለውና ህልውናም የማይኖረው ናዚስት ወያኔ በአማራና በአፋር ላይ ዳግማዊ የምፅዐት ጦርነት መጀመሩ ደግሞ አይቀሬ ነው። ትህነግ በይፋ በአማራና አፋር ህዝብ ላይ በሚከፈተው ድጋሚ ጦርነት የብልፅግና መንግሥት ካለፉት ተደጋጋሚ ስህተቶቹ ተምሮ በወያኔ ላይ የማያዳግም ሁለገብ እርምጃ ካልተወሰደ አማራና አፋር የእልቂትና የውድመት መናኸሪያ ይሆናሉ።

ናዚስት ህወሓት ከተንቤን ገደል ወጥቶ ከሞት ወደ ህይወት ትንሣዔ ለማግኘቱ የብልፅግና መንግሥት መሰረታዊ ስህተት ውጤት ነው። ይህ ሳያንስ የዘር ማፅዳትና የህወሃት አርኪቴክት አቦይ ስብሃትንና ናዚስት ወንጀለኞችን በስተርጅና ዘመናቸው አስሮ ማቆየት በእግዜር ዘንድ ያስጠይቀኛል ሲል ብልፅግና በቴሌቪዥን የሚያሰቅቅ ንግግር አሰምቷል። ቀንደኞቹን ናዚስቶች ከእስር ፈትቶና ነፃነት ሰጥቶ በብዕር የሚተቹትን ጋዜጠኞች እያሳደደ ያስራል፣ ደብዛቸውንም ይሰውራል።

 

በዚህ ሁሉ ሀገራዊ ሰቆቃ ፣ ረሀብና ጦርነት  መኻል የብልፅግና ፓርቲ መንግሥት ከበርቻቻው ግብዣውና ብልጭልጠጭ ብልፅግናው (በተለይ በአዲስ አበባ) ቅጥ አጥቷል። ፖለቲካው ባለፉት አራት ዓመታት በሂደት እጅግ እየጎመዘዘ ከመምጣት አልፎ ለሀገርና ለኢትዮጵያዊነት ህልውና እጅግ አደገኛ ሆኗል።  የእርጉዝ እናት ሆድ በስለት ተተልትሎ ጨቅላ ሲገደል ፣ ህፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ በዘረኞች በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ከሚታረደውና ከቀዬው ከሚፈናቀለወ ህዝብ በላይ በአረንጓዴ አሻራ ለመከነ ወይም ተረግጦ ለሞተ ችግኝ በብዙሃን መገናኛ የሚንገበገብ መንግሥት ፣ በህዝብ ረሀብና የምግብ ጠኔ  በኑሮ ውድነትም ሰቆቃ ለሚሰቃይ ህዝብ ‘ጎመን በጨው ፣ ሙዝ በዳቦ’ በአማራጭ ምግብነት የሚሰብክ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ በለውጡ(?) ማግሥት ይከሰታል ብሎ የገመተ አልነበረም። ለውጡ ከዘመነ ወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዐተ አገዛዝ የቅርፅ እንጂ የይዘት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም።  አልሸሹም ዞር አሉ ሆኗል የብልፅግና ሥርዐተ መንግሥት ሁለገብ ተግባር። ሚሊዮናት ህፃናትን ይዘው ተፈናቅለውና መጠለያ አጥተው ብልፅግና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ህንፃ ያድሳል። የቢሮ ጌጣጌጥ ይቀያይራል።  በግብዣ ላይ ግብዣ እየጠራ ደረቅ ዳቦ ለናፈቀው ሕዝብ የትረፈረፈ መስተንግዶውን በቴሌቪዥን ያሳያል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀጥ ብሎ ለመቆም የለገማችሁ የዘመኑ ካህናት ሆይ! ሰማእታት አባቶቻችን ከሰማይ ቤት እያዘኑ ነው!

 

ኢህአዴግንና ኢህአዴጋውያን ሁሉ አቅፎ በብልፅግና ፓርቲ መታወቂያ ሥልጣን የያዘው መንግሥት በመላ ሀገሪቱ ለተከታታይ አራት ዓመታት የዘለቀውን የዘረኝነት መጠፋፋት፣ መፈናቀል ፣ ወደር  ያጣውን ግፍና ሰቆቃ ‘በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ክስተት ነው’ ሲል ያለ አንዳች ሀገራዊና መንግሥታዊ ሀላፊነት በአደባባይ ከመግለፅ በዘለለ መንግሥታዊ ግዴታውንና ሀላፊነቱ ሲወጣ አልታየም። ብልፅግና ህግንና ሥርዓትን ማስጠበቅም ሆነ ማስፈን እስካሁን አልቻለም። በገፍና በግፍ ለጠፋው የህዝብ ህይወትና ለወደመው ንብረት  ሀላፊነትንም ተጠያቂነትንም እንደ መንግሥት ሲወስድ አልታየም፣ አይታይምም።

 

ብልፅግና ለአራት ኪሎ መቀመጫው አስጊ ሁኔታ የተፈጠረ ሲመስለው ግን በእጁ የሚገኙትን የፀጥታ  ሃይላት የሚያሰማራበትና ርህራሄ አልባ እርምጃ የሚወስድበት ፍጥነትና ቅልጥፍና  አስገራሚ ነው። ለአብነት፤ ሀ/ አብዲ ኢሌ መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርግ ነው ብሎ በብርሃን ፍጥነት ሐረር ተገኝቶ  አብዲን የፊጥኝ አስሮና ሴራውን አክሽፎ ተመልሰሷል። ለ/ ባህር ዳር ላይ በነጄኔራል አሳምነው ፅጌ የሚመራ ሀይል መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርግ ተንቀሳቅሷል ሲል ባህር ዳር በቅፅበት ተከስቶ ከጄኔራሉና ቁጥራቸው በውል ካልተገለፀ የአማራ ልዩ ሀይሎች ዘግናኝ እልቂት በኋላ ሙከራውን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ለህዝብ ገልጿል። ሐ/ በዘፋኝ ሀጫሉ ሞት ማግሥት ከሶስት ዓመት በላይ እንኮኮ አድርጓቸው የቆዩት እነ ጃዋር መፈንቅለ መንግሥት ሊያደርጉ ነው ሲል ከያሉበት ሰብስቦ ወህኒ ዶሏቸዋል። መ/ ናዚስት ወያኔ የአማራና የአፋር ክልልን ወርሮና እጅግ አሰቃቂ አረመኔያዊ ድርጊቶችን ሲፈፅም ብዙ ትችትን ያስተናገደው ብልፅግና ወያኔ ወደ አዲስ አበባ ሲቀርብ ወታደራዊ ልብሱን አጥልቆ በመዝመት ናዚስቶችን አማራና ትግራይ አዋሳኝ ላይ ለቋቸው ‘ጦርነቱን አሸንፌያለሁ’ ብሎ ወደ መንበሩ ተመልሷል። አማራና አፋር ዛሬ ፍዳቸውን እየቆጠሩ አዲስ አበባ ግን ሰርግና ምላሽ ነው – ብልፅግና መንደር። የኢትዮጵያ ብልፅግና መንግሥት ወደ መንበሩ ለሚጠጋ በህግና ደንብ ማስከበር አርማ ሥር ሲዘምትና ወንበሩን ሲጠብቅ አስደናቂ ቅልጥፍና አለው። ሕዝብ ከዓመት ዓመት መጤ እየተባለ ከሚኖርበት ሲፈናቀልና ኢሰብዐዊ ጭካኔ ሲፈፀምበት፣ አብያተ ክርስቲያናትና መስጂዶች ከዐመት ዐመት ሲነዱ መንግሥት እንደ መንግሥትነቱ ለህግ መጓደል ለሥርዐት መጥፋት ለፍትህ አለመኖር ሀላፊነት ሲወስድ ፣ የተሰደዱትን ሲጎበኝና ተገቢውን እርዳታም ሲያደርግ አይታይም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እነ ደብረ ፂዮን ፤ የትግራይ ህዝብ ከኋላው ጠመንጃ ተደግኖበት እሳት ውሰጥ ግባ የሚባል አሳዛኝ መንጋ እንዲሆን አድርገዋል

 

ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና ፓርቲነት የተቀየረው መንግሥት በኢትዮጵያ ህግንና ሥርዐትን በማስፈን የኢትዮጵያውያንን በሀገራቸው በሠላም የመኖር በነፃነት ሰርቶ የመግባት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያዊነት የመንቀሳቀስ እና የመኖር የዜግነት መብታቸውን ማስጠበቅ ከቶም አልቻለም ወይም አይፈልግም።

 

ብልፅግና የቀደመ የኢትዮጵያን አኩሪ የነፃነትና የሉዐላዊነት ታሪክ ከዚህ ቀደም በዘመነ ወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ተሰምቶ በማያውቅ ስሜትና ቋንቋ በውደሳና ፉከራ ያሸበረቀ ዲስኩር በየጊዜው በየመድረኩ በማድረግ የሚስተካከለው ባይኖርም በተግባር ግን፤ ሀ/ እኒያ ጥንታውያን በአድዋም ይሁን በማይጨው፣ በካራማራም ይሁን በባድመ ከጠላት ጋር ሲተናነቁ ከፍ አድርገው የተሰዉላትን አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ንፁህ ሠንደቅ ዓላማ  እንደ ናዚስት ህወሃት ሁሉ በአሸባሪነትና በህገ ወጥነት ፈርጆ በየክብረ በዓሉ ላይ ሲያሳድዳትና በፀጥታ ሀይላቱ ከሕዝብ እጅ እየነጠቀ በየሜዳው ሲያዋርዳትና ሲወረውራት ማየት እጅግ የሚያበሳጭና የሚያስቆጭ የአራት ዓመት ተደጋጋሚ የብልፅግና ተግባር ሆኗል። ህገ ወጥ ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል እያለ ስንቶች በፀጥታ አስከባሪዎች ተደብድበዋል?! ስንቶችስ ለእስር ተዳርገዋል?! ብልፅግና ያደባባይ አማላይ ዲስኩሩ ለፓለቲካ ፍጆታ ፓለቲካዊ ገፅታ ግንባታ ከመሆን በቀር መንግሥታዊ  ሠንደቅዓላማን የማሳደድና ከኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የማገድና የማውረድ አስነዋሪ ተግባሩ እንደ ወያኔ ዘመን ሳያባራ እንደ ቀጠለ ነው።

 

ለ/ በዘመነ ብልፅግና ብሔራዊም ሆነ ሕዝባዊ ክብረ በዓላትን በሰላምና በነፃነት ማክበር  ከቶም አልተቻለም።  የብልፅግና ባለሥልጣናት ለምሳሌ የዐድዋ በዓልን ለማክበር ከሚያወጡት ተንኳሽና እብሪተኛ ፀረ ታሪክ ፀረ ሠንደቅ ዓላማ  መመሪያ የተነሳ በየጊዜው ዐድዋ ክብረ በዓል የታሪክና የሠንደቅ ዓላማ  የፍልሚያ በዓል ሆኗል። ዐድዋ ላይም ሆነ ማይጨው ካራማራም ሆነ ባድማ ለሉዓላዊነት የተውለበለበችው ባንዲራ የመጀመሪያ የክብረ በዓሉ የብልፅግና ሰለባ ሆና ትሳደዳለች። ትጋዛለች። ትዋረዳለች። ለጥምቀት ክብረ በዓልም ይኸው ድርጊት ተደጋግሞ ተከስቷል። መመሪያው መንግሥታዊ ነውና !!!

 

ናዚስት ወያኔ አራት ኪሎን ከለቀቀ ወዲህ ባሉት አራት ዓመታት ተተኪው ብልፅግና የመልካም አስተዳደር፣ የሰላም የፍትህና የሀገር ሉዐላዊነትን በሂደት ያሰፍን ይሆናል የሚለው ተስፋችን ከመሟጠጡም በላይ ይነጋል ያልነው እየጨለመ፣ ህግና ሥርዓት፣ ሰላምና ደህንነት ለሥርዓተ መንግሥቱ ወንበር ህልውና እንጂ ለህዝብና ለሀገር ህልውና እንዳልሆነ በተደጋጋሚ አሳይቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ሎጋው ሽቦዬ!...የጫረው እሣት ... ሲፈጀው ታየ።..." ( አባ ታጠቅ  ምንዳሁነኝ )

 

አዎ ኢትዮጵያ ላይ ህዝብ ድምፄን ከሰጠሁት ከቀደመ ስህተቱም ሆነ ዳተኝነቱ ወይም ከፋፋይነቱና ጥምቀተ ኢህአዴጋዊነቱ ተላቆ እንደ መንግሥት ሀላፊነቱን ይወጣል በሚል ተስፋ የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልፅግናን በመንግሥትነት አስቀምጦታል።  አዎ ይህ መንግሥት በዓለም መንግሥታት በኢትዮጵያ ህጋዊ መንግሥትነት ይታወቃል።  ይሁን እንጂ ብልፅግና በድህረ ወያኔ የአራት ዓመት መንግሥትነቱ ሲመዘን ፤ የጠፋው ህይወት፣ የተፈናቀለውና መጠጊያ ያጣው ህዝብ ብዛት፣ የሰላምና የዜግነት ነፃነት እጦት ፣ የወደመው ንብረትና፣ የተጣሰው ሀገራዊ ሉዓላዊነት ፣ የተሸረሸረው ኢትዮጵያዊነትና አብሮነት የደረሱበት ጡዘት፣ የብልፅግና ዳተኝነት፣ ሁሉን አዋቂነትና ከፈረስ ጋሪ የማስቀደም ተግባራት ኢትዮጵያን እጅግ አደገኛ ወደ ሆነ ምዕራፍ ላይ አድርሷታል።

 

አዎ ዛሬ በ2014 ዓ/ም ሀገራችን የምትገኝበትን ሐምሌያዊ ድባብ ሰባት ሚሊዮን ህዝብ የያዘው የናዚስት ወያኔ ተግባር ወጤት ነው ብለን አንድ መቶ አስር ሚሊዮን ህዝብን ከሚመራው ፣ የትየለሌ ባጀት፣ መንግሥታዊ መዋቅርና የጦር ሀይል ካለው ብልፅግና ትከሻ ላይ ማውረድ ከቶም አይቻልም። ግን ዛሬም ለኢትዮጵያ አልመሸም።  ብልፅግና ሆይ ይህ ምዕራፍ ለአንተም ህልውና ሆነ ለኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ ነውና ከኢህአዴጋዊ ርዕዮትህና ከኔ በላይ ለኢትዮጵያ አዋቂ ላሳር ከሚለው መንግሥታዊ ደዌህ ተላቀህ ድምፅ የሰጠህን ህዝብ ልብ ሰጥተህ ስማ፣ የሕዝብ መንግሥት እንድትሆን እንጂ ድምፅ የተሰጠህ የፉክክር ቤት የምትመራ መንግሥት እንድትሆን አይደለም። የየክልል መንግሥታት ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ መንግሥታት እስኪመስሉ ድረስ የታበዩት በአንተ አመራር ምክንያት ነውና የኢትዮጵያውያን ሁሉ መንግሥት መሆንህን ከዲስኩር ይልቅ መሬት ላይ በሚታይ ግብርህ አስመስክር። በግልፅ ከሚታይብህ የተደጋጋመ የስህተት አረንቋም ራስህን አፅድተህ ውጣ። ቅድሚያ የሚሰጠው መሰረታዊ ሀላፊነትህ ላይ ሥራ – እንደ ህዳሴው ግድብ!!! መንግሥታዊ ኃላፊነትህንና ግዴታህንም ተወጣ። ይህ ይሆን ዘንድ አልመሸብህምና ሳይመሽ አይምሽብህ!! ውስጣዊ ሰላሟ የተረጋጋ፣ ህግና ሥርዐት የሰፈነባት ኢትዮጵያ ለትንሳኤዋ መነሻና መድረሻ ብቻ ሳይሆን ለአንተም ህልውና አልፋና ኦሜጋ ነውና። ኢትዮጵያ ከአንተ በፊትም ነበረች ከአንተም በኋላ ትኖራለችና !!! አዎ ነገ ሌላ ቀን ነውና – በበኩሌ በሀገሬ  በኢትዮጰያ ግን ከቶም ተስፋ አልቆርጥም!!!

[ መስፍን ማሞ ተሰማ ግንቦት 2014 ዓ/ም ሲድኒ አውስትራሊያ ]

3 Comments

  1. I completely agree with the title of the article.
    It looks that we are still suffering from having been citizens of the oldest state in history. We have been conditioned to think of whoever is in power as the “government”.

    To say, “የኢህአዴግና ኢህአዴጋውያን አባት ናዚስት ወያኔ” and then wish for “ትህነግ በይፋ በአማራና አፋር ህዝብ ላይ በሚከፈተው ድጋሚ ጦርነት የብልፅግና መንግሥት ካለፉት ተደጋጋሚ ስህተቶቹ ተምሮ በወያኔ ላይ የማያዳግም ሁለገብ እርምጃ ካልተወሰደ” shows the pain and confusion we find ourselves in.

    Why would OPDO that salvaged TPLF from utter destruction and, in fact, resuscitated it, want to totally destroy it? Was what happened in the past really repeated mistakes or part of the gamble Shime so eloquently spoke in Oromigna about? Was leaving 20 million liters of petrol an unintentional mistake? How about the over billion dollar freshly minted Ethiopian money? How about the fully armed ten thousand soldiers left behind? Was leaving the anti-TPLF tigrayans of the temporary administration behind also an inadvertent mistake? Was evacuating from all the strategic positions in Northern Wollo and Southern Tigray just a stupid mistake? How about letting the TPLF keep thousands of WFP trucks for use in transporting troops, military hardware and loot? Was disseminating a disarming propaganda by telling the public that the TPLF has been reduced to ashes just a mistake? Well, the same exact thing is being repeated now. Propaganda is being disseminated to create the impression that the army has come back in full force and can defend the people with no need for the involvement of Fanno or other local militia. That was what Field Marshal Birhanu Jula (some say Hamsa Aleqa) said before he fled at a speed that exceeded the records of the famous Oromo athletes of Ethiopia as he run from Tembien to Sheno.
    You fool me once, shame on you. You fool me twice, shame on me. You fool me thrice, shame on my IQ, we can add.

  2. Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

    Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

    Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

    As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

    So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

    The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

    In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

    Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

    Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

    It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

    Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

    Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

    For us, Oromos, conederation is also the answer.

  3. To say, “የኢህአዴግና ኢህአዴጋውያን አባት ናዚስት ወያኔ” and then wish for “ትህነግ በይፋ በአማራና አፋር ህዝብ ላይ በሚከፈተው ድጋሚ ጦርነት የብልፅግና መንግሥት ካለፉት ተደጋጋሚ ስህተቶቹ ተምሮ በወያኔ ላይ የማያዳግም ሁለገብ እርምጃ ካልተወሰደ” shows the pain and confusion we find ourselves in.

    Why would OPDO that salvaged TPLF from utter destruction and, in fact, resuscitated it, want to totally destroy it? Was what happened in the past really repeated mistakes or part of the gamble Shime so eloquently spoke in Oromigna about? Was leaving 20 million liters of petrol an unintentional mistake? How about the over billion dollar freshly minted Ethiopian money? How about the fully armed ten thousand soldiers left behind? Was leaving the anti-TPLF tigrayans of the temporary administration behind also an inadvertent mistake? Was evacuating from all the strategic positions in Northern Wollo and Southern Tigray just a stupid mistake? How about letting the TPLF keep thousands of WFP trucks for use in transporting troops, military hardware and loot? Was disseminating a disarming propaganda by telling the public that the TPLF has been reduced to ashes just a mistake?
    Well, the same exact thing is being repeated now. Propaganda is being disseminated to create the impression that the army has come back in full force and can defend the people with no need for the involvement of Fanno or other local militia. That was what Field Marshal Birhanu Jula (some say Hamsa Aleqa) said before he fled at a speed that exceeded the records of the famous Oromo athletes of Ethiopia as he run from Tembien to Sheno.
    You fool me once, shame on you. You fool me twice, shame on me. You fool me thrice, shame on my IQ, we can add.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share