May 9, 2022
6 mins read

የግንቦት ቀጠሮ  (ፍርዱ ዘገየ) 

ኧረ ፋኖ! ፋኖ!

እንደ ዝንብና እንደ ክፉ መንፈስ ግንቦትን የሚወዱት ደደቢታውያን (ደብረጽዮን እና አቢይ አህመድ)፣ ፋኖን ለማጥፋት ግንቦት ላይ ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል። ግንቦት ሦስት። አማራ ፋኖ ያለውን ያህል ባንም ሁሌ ስለማያጣ ቆሻሻውን ሥራ የሚሠራ የባንዳ ሹምባሽ ባሕርዳር ከረመ ተብሏል። የት? አቫንቲ ሆቴል። የስሙም ሥምረት የሚደንቅ ነው። ለባንዳ መኝታ የሰላቶ ስም ያለው ሆቴል! አቫንቲ! በጣልያንኛ ወደፊት? ቀጥል? ግፋ! ግባ! እንደማለት ነው። የጣልያን ባንዳ ኦሮሞም አማራም ትግሬም የሆንክ ሁላ ወደፊት ግፋ! ሀገር አጥፋ! ወገን አውድም! የተባለ ይመስል በአቫንቲ ሆቴል ሰፍሮ ሲያሴር፣ ሲያደራጅ ሰንብቶ አሁን ለግንቦት ቀጠሮ ይዟል። የመንፈስ መመሪያው ከጣልያን የወረደለት ስለሆነ ትውልድም ተሻግሮ አቫንቲ! የሚለውን ነው የሚያደምጠው።

የፋኖ ምርጫ

1 በላይ ዘለቀ (የሶማው) በስሙኒ ገመድ ተንጠልጥሎ መሞት

2 ደርበው አየለ (የዱር ቤቴው) አሥሩን ባንዳ ደራርቦ መሄድ

3 እሸቴ ሞገስ (የይፋቱ) ዘጠኙን ባንዳ አራግፎ መሄድ

4 ደመቀ ዘውዱ (ወልቃይቴው) ባንዳውን ረፍርፎ በወገን ታጅቦ ትግሉን መቀጠል

እነዚህ ናቸው የፋኖ መንገዶች። ትናንትም ዛሬም። ምሳሌው ብዙ ስለሆነ ያታክታልና እነዚህን ለናሙና መርጠናል።  ፋኖን ማዳን የፋኖ ብቻ ሳይሆን የሕዝቡም ግዴታ ነው። ላንተ ነጻነት ለሚሞትልህ ፋኖ መቆም ከተሳነህ የደህንነትህ ዘብ የሆነውን ፋኖን ካስወገዱ በኋላ ሰንሰለቱን፣ ሜንጫውን ወይም የመቅበሪያውን ዶዘር ይዘው እደጅህ ድረስ ይመጡልሃል።

የአማራ ሕዝብ ሶሥት ዐይነት ነው። ፋኖ፣ ባንዳና ባርያ። ምርጫውም እንግዲህ ሦስት ነው ማለት ነው። አቅም፣ ወኔ፣ አባት፣ ያለው ፋኖ ይሆናል። ሆድ ያለው ባንዳ ይሆናል። ጀግናውን የሚያስገድል ቆሞ ተመልካች ደግሞ ባርያ ይሆናል።

ምርጫ በምርጫ ነው። ቡፌው ቀርቧል የሚስማማህን መርጠህ አንሳ። የመጨረሻው ምሽግ ላይ ቆመሃል፣ መሸሻ መጠጊያ የለህም። ከተኛህም ጅራፉ ቀስቅሶ ወይም ወደ ወህኒ ወይም ወደ መቃብር ያወርድሃል። ባንዳም ብትሆን ፋኖ ሲያልቅ የመሳደድ ተራው ያንተ ነው። ግንቦቴው ካልጠፋ ሰላም አይኖርህም። እንቅጩን ስንነጋገር።

ከላይ የተጠቀሱትን ዝነኛ ስሞች ለማያውቁ መጠነኛ ማብራሪያ

በላይ ዘለቀ። ጣልያንን በአምስት አመቱ ትግል የመከተ ስመጥር አርበኛ፣ የጎጃም ተወላጅ። ጣልያን ከተባረረ በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በስቅላት የገደሉት።

ደርብ አየለ። ወያኔ በውደቀቷ ዋዜማ ተቃውሞ ስለበዛባት እንደዛሬው አቢይ አህመድ ባንዶችን ልካ ትጥቅ ልታስፈታው ስትል አሥራ ምናምኑን አቁስሎ ወደ ሰባቱን ባንዳዎች ረፍርፎ የተሰዋ የዱር ቤቴ፣ ጎጃም ተወላጅ።

እሸቴ ሞገስ። የይፋት ተወላጅ ከልጁ ጋር ሆኖ ወያኔ በዳግም ወረራዋ ወደ ደብረ ብርሃን የምታደርገውን ግስጋሴ የመከተ ዘጠኝ ባንዳ ረፍርፎ የተሰዋ።

ደመቀ ዘውዱ። ወያኔ የወልቃይትን ጥያቄ ለማሰናከል አፋኝ የትግራይ ልዩ ኃይል እቤቱ ድረስ ብትልክበት፣ መሣሪያ አንስቶ አጥቂዎቹን ያወደመ፣ ሕዝቡም ደርሶ ያስጣለውና ትግሉን ለማስቀጠል የቻለ የጎንደር ዘመናዊ አርበኛ። የወያኔ ውድቀት ዋና ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop