May 5, 2022
6 mins read

ሰላቶ ከዶጋሊ እስከ አሻድሊ (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

የቅኝ ገዢው ጦር ሠራዊትና ፊታውራሪው በዘመናት መካከል እየጠቆረ ስለመምጣቱ።

ogaliየአውሮፓ ወራሪም ሆነ ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው የአረብ መንጋ ለዘመናት ኢትዮጵያን ተመላልሶ ከማጥቃት ውድቀቱ የተማረው አጥቂው ሠራዊት እየጠቆረ የመሄዱን አስፈላጊነት ነው። በግልጽ አባባል ሙሉ በሙሉ የነጭ ሠራዊት ይዘው መጥተው በጀግኖች እናት አባቶቻችን ዶግ አመድ ተደርገው ተመልሰዋል። ለምሳሌ በዶጋሊ በራስ አሉላ ጦር ሙሉ በሙሊ አውሮፓዊ የነበረው ወራሪው ሠራዊት ያለ ወሬ ነጋሪ ተደምስሷል።  አንድም ሰው ሳይተርፈው። ከዚህ ትልቅ ትምህርት በመውሰድ በአድዋው ውጊያ ብዙ ኢትዮጵያውያን (ከዛሬው ትግራይና ኤርትራ ምድር) ቀላቅሎ አሰልፏል። ቢሆንም አብዛኛው ሠራዊት ነጭ ነበር።  በአድዋም እንደሚታወቀው በአንድ ቀን ውጊያ አብዛኛው ተደምስሶ የተረፈው ፈርጥጧል። ከአርባ አመት በኋላ ከዚህም ውድቀት ትምህርት በመውሰድ አሥር እጥፍ አፍሪካዊ ራዊት ቀላቅሎ አሰልፏል።  በጠረፍ ዶጋሊ እና ሰሐጢ ብሎም ወደ አምባላጌ ጭራሽም ዘልቆ አዲስ አበባ ለመድረስ ያበቃው ዋናው ቀመር ይኸው “ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ” የሚለው ከውድቀቱ የተማረው ስልቱ ነበር።

በዚሁ “ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ” ስልቱ ከፋሺስት ዘመን ውድቀቱ ትምህርት ወስዶ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አፍሪካዊ ወይም ጥቁር በሆነ ሠራዊት የመውረር ስልትን ተግብሮ በተሳካ ሁኔታ አራት ኪሎን ለዘመናት ለመቆጣጠርና በእጅ አዙር ለመግዛት የሀገሪቷንም ዋልታና ማገር እሴቶች ተራ በተራ ድምጥማጣቸውን ለማጥፋት መዝመት ችሏል። በዶጋሊ ዘመን ሙሉ ነጭ የነበረው የሰላቶ ጦር በአሻድሊ ዘመን ሙሉ ጥቁር ኢትዮጵያዊ ማስክ አጥልቆ ሃርድዌሩ አፍሪካዊ ሶፍትዌሩ ግን የተጠለፈ ተላላኪ ምስለኔ ሊሆን ችሏል። ነጩ ግራዚያኒ በጥቁሩ አቢይ አህመድ ተተክቷል። በግራዚያኒ ያልተቻለው በአቢይ እየተቻለ የሺ ዘመናት ተቋማትና እሴቶች ምስጥ እንደበላው ቤት እየተቦረቦሩ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ከሄሮዶቱስ ጀምሮ እስከ የእስልምናው ነቢይ መሐመድ ድረስ በፍትሕ ተምሳሌትነት እንዳልታወቀች ፍትሕ “ታውራ የድመት መጫወቻ እንደሆነች አይጥ” የአቢይ አህመድ መጫወቻ ሆናለች።

ተስፋ መቁረጥ ግን ፈጽሞ አይገባም። የኢትዮጵያ አምላክ ይዘገይ ይሆናል እንጂ ኢትዮጵያን አይተዋትምና። ግራዚያኒ በአራት ኪሎ ሲፏልል አዲስ አበባንም ሲያነድ ጀግኖቿን ሲያሳድድ ነበር።እግዚአብሔር ከየካቲት አሥራ ሁለት እልቂት ያተረፋቸው ጀግኖች እነ አብዲሳ አጋ ጣልያንን በገዛ ሀገሯ አርበድብደው ሮም ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንዳውለበለቡ መዘንጋት የለብንም።  ዘርዐይ ደረሰም እዚያው ሮም ላይ ነው ለሀገሩ ክብር ጎራዴውን አንስቶ የላቀ ጀብዱ ያሳየው።

የሰላቶ ቀለም መጥቆር የትውልዱን ትግል ከአባቶቻችንም ዘመን የከፋ ዳገት እንዳደረገው መካድ አይቻልም። ጭምብሉ ከተገለጠ በኋላ ግን የነጻነት ትግሉ እርምጃ የተፋጠነ እንደሚሆን እሙን ነው።  የዛሬ ሰማንያ አንድ አመት ለአባቶቻችን ድልን የሰጠ አምላክ አሁን ላይ ቋንቋ እየቀየሩ በላያችን ላይ የሚጎለቱትን የሰላቶ ወኪል ባንዳዎች ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ ለማስወገድ ንቃት፣ ብርታትና ድልን ይስጠን።

የአሉላ አባ ነጋ፣ የአብዲሳ አጋ፣ የበላይ ዘለቀ፣ የኡመር ሰመተር እና የዘርዐይ ደረስ አምላክ አይለየን።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop