May 05, 2022
ጌታቸው ረዳ
በአንዋር መስጅድ ስለ ጎንደር ሙስሊሞች የተካሄደ ታላቅ ተቃውሞ ሃሩን ሚዲያ ከቦታው ልዩ ዘገባ
እንዴት ሰነበታችሁ? አማን ነው? ተብሎ የሚጠየቅበት ወቅት ነን። የእስላሞች መሪ የሜካ ‘ሒጃዝ’ ተወላጅ ነበረው የ45 አመቱ ጎልማሳ “ነጋዴ” መሐመድ ኢብን አብደላ (ነብዩ መሐመድ) ከሞተ በሗላ የማይጣጣሙ ሁለት የእስልምና እምነቶች ተከሰቱ። “ሱኒ እና ሺዓ”። ቆይተውም ወደ 73 ከፍሎች ተከፍለዋል።
Sunnī Islam. Shīʿa Islam. Kharijite Islam. Murijite Islam. Muʿtazila Islam. Sunnī Shīʿa.,. እና በአገራችን የታወቁት “ሱኒ ፤ ሰለፊ ፤ ወሀቢያ” የመሳሰሉ አሉ።
ሰሞኑ ለፕሮተስታንት፤ ለእስላሙና እና ለኦሮሞ ነገድ የሚወግነው በጠ/ሚኒሰትርነት የተቀመጠው አብይ አሕመድ በሚመራው መንግስታዊ ጎሰኛና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ‘ጸረ ተዋዶ’ ሴራ እየጠነከረ ሄዷል። በጎንደር ከተማ ተከሰተ የተባለ እስላሞች እና ክርስትያኖች የሞቱበት ሁወከት ምክንያት ስርዓቱ የሚከተለው ሰበብ ነው።
ይህንን ሁለት አሳብቦ የተኛ የሚመስለው 30 አመት ሙሉ “ውስጥ ለውስጥ፤ ሲነሽጠውም በግሃድ” “ኢትዮጵያን እስላማዊት” በማድረግ ላይ ያለው ጽንፈኛው የውሃቢ እስልምና አራማጁ ቡድን “አላህ ወ አክበር! አላህ ወ አክበር! ተጠቂ ሆነን ተከሳሽ ሆነናል!” እያለ አዲስ አባባ ከተማ ውስጥ አጼ ሃይለስሳሌ ያሰሩላቸውን ኣንዋር መስጊድ በመስበሰብ በሙሰሊሞች መዝሙር እየታጀበ “ፋኖ ሌባ! ፋኖ ይውደም!” በማለት መስጊድ ግቢ ውስጥ ወጣቱም ሽማግሌ እናቶችም ጭምር ሳይቀሩ ‘አፍንጫ ሲነካ ዓይን ያለቅሳል’ እያሉ በልቅሶ የታጀበ በጥላቻ የታወረ በሺዎቹ ተሰብስበው “ፋኖ ከምድረገጽ እንዲጠፋ” ሲያወግዝ የዋለው “ሙጃሃዲኑ” የውሃቢሰት ክንፍ የዘረጋው ቪዲዮ እንድታደምጡት ለጥፌዋለሁ።
“እስከዛሬ ድረስ ችለን እንጂ ተቻችለን አልኖርም” የምትለዋ ውሃቢዎቹ የሚወድዋት የ30 አመት ሙሉ መፈክራቸው ትናንትም አዲስ አበባ የመስጊድ ሰልፋቸው ላይ በጽሑፍ ዘርግተዋት ሲያስነብቡን ውለዋል።
ይህች መፈክር የብዙዎቹ ጽንፈኛ ዋሃቢዎች ተወዳጅ መፈክራቸው እና ወዴት እያመራን እንደሆንን አመላካች መፈክር ነች። አክራሪ የውሃቢያ ተከታዮች የተከተሉት “ፋኖ ጸረ ትግሬ” የሚለው የወያኔ መፈክር ፤ዛሬ ደግሞ ውሃቢስቶቹ ሳይሸማቀቁ ሳያድሩ “ፋኖ ጸረ እስልምና ነው” እያሉ ፋሺሰቱ ወያኔ “የእስላም ሴቶችን ከየቤታቸው እየገባ እንዳይደፍራቸው ህይወታቸው የሰው “የፋኖ” አባሎች በመኮነን “ፋኖ ይደምሰስ” እያሉ ሲያወግዙት ውለዋል”። ያጠፉ ግለሰቦች ካሉ መወንጀል አንጂ ፋኖ ይደምሰስን ምን አመጣው?
ብዙዎቻችሁ እባካችሁ ስለ ሃይማኖት አትነካኩ ፤ይባባሳል ፤ዝም በሉ ስትሉ ሰምቻለሁ። ምስኪን ምሁራኖችም ተመሳሳይ ሲለፈልፉ ብዙ ጊዜ አድምጫለሁ። እስላሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ከክርስትያኖች በባሰ የተበደሉት ነገር የለም”’ እኩል ተስተዳድረናል፤ ኖረናል፤ ተምረናል፤ተብደለናል፤ እኩል ሞተናል። ስለዚህ እንደምታውቁኝ እኔ ጋር ማባበል፤ መደባበስ የለም። ‘ሃቁን ተናግሮ ከመሸበት…” የሚለው የኔ ባህሪ ነውና እስልም ወገኖቻችን ቢመራችሁም ከምትናገሩት “የፈጠራ ትርክት” እና “ጂሃዳዊ” ስብከት ሂስ ማቅረብ የግድ ነው።
እስላሞች 30 አመት ሙሉ በምቾት ነበሩ። ትግሬዎችና ኦሮሞ እስላሞች ያልነበራቸው የቦታ ካርታ አጝኝተው ተስፋፍተው 3/4ኛውን ኢትዮጵያ ካርታ ቅርምት ገብተው ከሚገባቸው በላይ ተስፋፊ ሆነው የበላይ ሆነው አይተናቸዋል።
ኦሮሞና እስልምና በማያያዝ ክርሰትያኑን በፖለቲካና በሃይማኖት ረገድ ሲያርዱት ነበር የቆዩት። በዚህ ዘመን የተበደለው እስላም ነው የሚለው አሳሳች መፈክር በተቃራኒው መነበብ አለበት።
ጎንደር ከተማ የታየው የክርሰትናም ሆነ እስልምና ተከታይ ወገኖቻችን ሁከትና ሞት አወግዛለሁ። ሆኖም “ውሃቢያው ቡድን” ድክመት አለ በተባሉ አካባቢዎች እሳት እየጫረ በየሰላማዊ ሰልፉ የሚያስተጋባው “ፖለቲካዊ ድምጽ” ማቆም አለበት።
ይህ ብቻ ሳይሆን “ትሬንዱን/ጎዳናው” የቀውስ ቀስቃሽ “ፈለጎቹን” እየተከትልን ስንመረምር 30 አመት ሙሉ “ቦታ መቀራመት፤ ጥንታዊ ሃውልቶችን ማፍረስ፤ ቤተጸሎቶችን ማቃጠል፤ በቤተክርስትያን አጠገብ ፊት ለፊት እና ጎን ለጎን መስጊድ መገንባት፤ ከጂማ፤ ከወለጋ፤ ከሐረር፤ ከባሌ….ወዘተ..ማባረር… ፤ ሰውን በቢላዋ ማረድ፤ንብረት ማውደም ክርስትያኖችን ያነጣጠረ ጥቃትና ከቦታቸው ማባረር… ሲፈጸም ኖሯል። ሃቁ ይህ ነው።
ነገሮችን ለማጤን ወደ ኋላ ልውሰዳችሁ።
ዘንድሮ በትምህርት ክፍል ውስጥ፤ ወንበሮችን በማራራቅ ሴት እስላም ህጻናት የክፍል ጓዶቻቸው ባሉበት ክርስትያን ህጻናት ቁጭ ብለው ክፍል ውስጥ እያዩ ሲሰግዱ የሚያሳይ ፎቶ አይታችኋል አደል? ይህ ሁሉ ከኋላ ቀስቃሽ ቡድን አለው።
“ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም” እስከሚሉ ድረስ ሰዎችን ሁሉ እንድዋጋ ታዝዣለሁ” የሚለው በንግድ ስራ ሲተዳደር የነበረው የነብያቸው የመሐመድ ስብክት በመከተል “Ethio Muslims Interfaith Dialogue for Justice” የተባለው “የዩቱብ ቲቪ ፓል ቶክ” ዋና ባለቤት የሆነው ባሰውዲ የውሃቢው አክራሪ ሃይል ድጋፍ የሚደረግለት “አቡ ሃይደርና አንዳንድ እሱን መሳይ ጽንፈኞች በመሰባሰብ እስልምና በኢትዩጵያ ዋና አትኩሮታቸው በማድረግ በክርስትና አማኞች ጥቃት እንዲደርስ ቤተጸሎቶቻቸው እንዲቃጠሉ በግልጽ ሲሰብኩ የተቀዳ መረጃ አለ፡ ዛሬም ቀጥሎበታል ።
አምና አክራሪ ውሃቢ ተከታዮች መስቀል አደባባይ ካልሆነ ሌላ ቦታ በዓላችንን አናከብርም ብለው “ኢድ አደባባይ” የሚል ጠብ ጫሪ መፈክር ይዘው እንደታዩ ይታወቃል። ውሃቢስቶቹ “አዲስ አባባ ከንቲባ ተብየዋ ኦነግዋ አዳነች አበቤን” አይዟችሁ ባይነት ተመርኩዘው ሴራ እየጎነጎኑ ነው።
ለበርካታ አመታትም አክራሪ ውሃቢ እስልምና በኢትዮጵያ ተስፋፍቷል እያልኩ ነበር። እነ አቡበከርም ሆኑ እነ አሕመዲን ጀበል በወያኔ ሥርዓት ከመታሰራቸው በፊት ትንንሾቹ ወጣቶችን እየሰበሰቡ ሃይመኖት እየሰበኩ ጣልቃ በማስገባት ክርስትናን እና ኢትዮጵያን እንዴት ሲያበጠለጥሉ እንደነበር በርካታ መስረጃ ንግግሮቻቸው እያቀረብኩ ሳስነብባቸሁ እንደነበር ይታወሳል። ምናልባትም ለፌስ-ቡክ እንግዳ ስለሆንኩኝ ብዙ ወዳጆቼ “ኢትዮጵያን ሰማይ” ሳታውቁት ኖራችሁ ስለሚሆን በድረገጼ ላይ ካቀረብኳቸው ሰነዶች ሄዳችሁ ተመልከትዋቸው።
በወሎ ክ/ሃገር የሚገኙ ኦረሞ ተብለው የተከለሉ ከተሞችና ትንንሽ ከተሜ ገጠሮች በእሳት እንዲወድሙ የተደረገበት ምክንያት ክርሰትናን እና አማራን ለማጥፋት መሆኑን ልብ በሉ።
“ኦሮሞና እስልምና አንድ ናቸው፤ ኦሮሞ ሲጠናከር እስልምና ይጠናከራል፤ እናንተም ትጠናከራላችሁ፤ እናንተ ስትጠናከሩ ጎንደር ውስጥ አክሱም ውስጥ ያሉ እስላሞች ይጠናከራሉ…” እያሉ ሲሰብክ የነበረው “ጃዋር መሓመድ” የአደባባይ ስብከት ውጤት ዛሬ ፍሬው እያየን ነው። በየከተማው የሚታየው እነሆ የውሃቢ “አክራሪ አስልምና” ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እስላሞች “አደፈጡ እንጂ ልብ እንዳልገዙ” እንድታውቁት የምወተውተው ለዚህ ነው።
ስለሆነም እንደገና ወደ ኋላ ተመልሰን የዚህ እንቅስቃሴ ህቡእ ፍላጎት ምንነት ዳግም መፈተሹ አስፈላጊ ስለሆነ ከአመታት በፊት የነበረው የሙስሊሞቹ ፍላጎት ከሸሪዓ መንግሥት ምስረታ ፍላጎት ጋር የተገናኘ እንደነበረና ዛሬ ግን እስላማዊውና ፕሮቴስታናዊው “አምታቹ” አብይ አሕመድ አጀንዳቸውን አስፈጽሞላቸው እጅና ጓንቲ ሆነው አባቱ አይደሉም ተብለው የሚነገርላቸው የበሻሻ አባቱ በሞት ሲለዩ እነ አቡበከር እነ አሕመዲን ጀበል ወዘተ…. ጅማ ድረስ ሄደው ቀብሩ ላይ ተገኝተዋል። የመለስ ዜናዊ አባት ሲሞቱ ግን ዓድዋ ድረስ ሄደው ቀብር አልተገኙም። ለምን? ግልጽ ነው።
ወያኔ ከመንግሥትነቱ ሊወገድ ከ6 አመት በፊት የነበረው የሙስሊሞቹ ጥያቄ ምን ነበር? አንዱን ይያቄአቸው ልጥቀስ እንዲህ ይል ነበር፦
“በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” (የሙስሊሞች የተቃውሞ ድምጽ) – ምንጭ (አንድ አድርገን ነሀሴ 5 2005 ዓ.ም) ፡-
ከ6 አመት በፊት የነበረው እና ዛሬ የሚደመጡ መፈክሮችና ፍላጎቶች አልተለወጡም። ያኔ በሙስሊሞች የበዓል እለት አዲስ አበባ በብዙ ቦታዎች በተቃውሞ ስትናጥ መዋሏን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ኢቲቪን ሳይቀር ተቀባብለው መዘገባቸው ይታወሳል፡ በተነሳው ግጭት ፖሊስ ብዙዎችን ማረፊያ ቤት ማጎሩም ይታወቃል፡፡ በወቅቱ የታሰበበትና የተጠና ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚገኙ መረጃዎችን ያመለክታሉ ፤ የዛሬዎቹ እና የያኔ የባነሮቹ/ፅሒፎች/ ተመሳሳይነት ፤ የመፈክሮቹ ይዘት ፤ ተቃውሞ የተነሳበት ፍላጎት አንድ ናቸው።
አንድ ነገር ላስታውሳችሁ። በወቅቱ እንደ ስታስቲክ ኤጀንሲ መሰረት በአዲስ አበባ ውስጥ 72 በመቶ ክርስቲያኖችና 16 በመቶ ሙስሊም ማህበረሰብ ይኖራል የሚል መረጃ ቢኖረውም ፤ የወጣው ሕዝበ ሙስሊም ግን እውን ይህ ሁሉ ሰው አዲስ አበባ ውስጥ ይኖራልን? የሚያስብል ጥያቄ አስነስቶ እንደነበር ታስታውሳላችሁ፡፡
በመሰረቱ “በበዓላቸው ወቅት ከዚህ በፊት በኢድ ፤ በአረፋ እና በተለያዩ ወቅቶች የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ገጠር የመግባት ሂደት የሚስተዋል ሲሆን በዚህ በዓል ግን የተገላቢጦሽ ሆኖ አልፏል፡፡” ይላሉ አንድ ጸሐፊ። ሰዎች ከአዲስ አበባ ወደ ገጠር የሚገቡበት በዓል ሳይሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የመጡበት ሆኖ ተስተውሏል ይህ ሁኔታ በቁጥር ብዛታቸውን ለማሳየት እና ድምጻቸውን እጅጉን አጉልተው ለማሰማት እንደተጠቀሙበት ለመመልከት ተችሏል፡፡ ውሃቢው እጅግ መጠናከሩ ማሳያ ነው። ክርስትያኑ ግን ተበታትኖ እርስ በርሱ ሲነታረክ ይውላል።
ታስታውሱ እንደሆን በ2004 ዓ.ም (በነገራችን ላይ “ዓ.ም” አመተምሕረት ለእስላሞች አመተ ፍዳ ነው ብለው ስለሚያምኑ በዓረቦች ዛመን አቆጣጠር ነው የምንቆጥረው ይላሉ ውሃቢስቶቹ። ሰንደቃላማም በሚመለከት ላለማውለብለብም እንዲሁ የምኒሊክ አዋጅ ሦሰቱ ቀለማት ከክርስትና አያይዞ ስላወጀው አንቀበለውም ይላሉ፤ የደሴ የሐረር የበሻሻ-ጅማ ሙጃሃዲኖቹ)
በ2004 ዓ.ም. ሐምሌ ላይ በአወሊያ ትምህርት ቤት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ እዚህ ደረጃ ሊደርስ ችሏል፡፡ በወቅቱ ጥያቄው ከአወሊያ መስኪድ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት በግላጭ በማይክራፎን ‹‹ጅሀድ›› በማወጅ ነበር ነገሩን የቆሰቆሱት “አልሓባሽ ከኢትዮጵያ ምድር ይውጣ!” ይል ነበር። ይህ የጅሀድ ጥሪን የተቀላቀሉ በርካቶች በወቅቱ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመጋጨት ብዙዎች መታሰራቸውን ብዙዎች ላይ ቀላልና ከባድ አደጋ መድረሱን የቀርብ አመታት ትውስታችን ነው፡፡
ይህ በሆነ ከአንድ ቀን በኋላ በአዲስ አበባ በአምስቱም አቅጣጫዎች በህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች በገፍ እየተጫኑ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የነበሩ በርካታ የእስልምና ተከታዮችን እንደነበርም በወቅቱ ተዘግቧል፡፡ በወቅቱ በሰልፉ ወቅት ከተነሱ በርካታ መፈክሮች ውስጥ አንዱ “በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ በሀገሪቱ ላይ እስላማዊ መንግሥት እንዲቋቋም የሚፈልጉ ሰዎች ጥያቄ ነው፡፡ ውሃቢስቶቹ ሃይማኖታዊ ጭንብላቸውን እንደለበሱ የወደፊት ራዕያቸውን ለማሳካት “ሙስሊሞች ፓርቲ ለመመስረት ጥያቄ አቅርበው እንደነበርም መዘንጋት የለበትም፡፡
ባኦሆዴዱ ጠ/ሚ በአብይ አሕመድ ዘመን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውሃቢስቶቹ ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ ፤ ህዝበ ክርስቲያኑን በሰይፍ ፤ ሲያሳድዱ ፤ የህይወት መስዋዕትነት የሚያስከፍል ድርጊቲ “ብልጽግናው መንግሥት” ዝም በማለቱ ሃውልቶችን እስኪያፈርሱ ደርሰው የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓቸዋል፡፡ ትላንት ጎንደር ላይ የታየው ሁከትና ግድያ ወደ “ፋኖ ይውደም” መፈክር የማስደመጡ መልዕክት የውሃቢው አለመተኛት ምልክት ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ሱኒ ተከታዮች ሲሆኑ ፤ “ሰለፊ እና ወሀቢያ” ጥቂት ነበሩ ዛሬ
‘ጺማቸው ባዠረገጉ’ ከአረቦቹ በበበለጠ ፍጥነት ፈጣን አረብኛ ቋንቋ የሚያነበንቡ የሳውዲ ውሃቢ እና ፓኪስታን ሄደው የተማሩ “ባችለር ዲግሪ ያላቸው ጀለቢያ የሚለብሱ፤ ዓረብ መሳይ ውሃቢስት ኢትዮጵያዊያን” ወጣቱ ስለተሰበከ በብዛት እነሱ ወደ መሆን ተሸጋግረዋል።
ታስታውሱ እንደሆን የአሜሪካ መንግሥት ከአዲስ አበባ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከው ‘በዊኪሊክስ’ ተጠልፎ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ ውስጥ ወሀቢያን ሰፍረውበታል አስተምህሮታቸውን ያካሂዱበታል ካለባቸው ቦታዎች ውስጥ “ደሴ ፤ ሐረር ፤ ጅማ እና አርሲ” ይገኛሉ ፡፡ አሁንም ከአመታት በፊት የተተከለችው የአክራሪነት ፍሬ አዲስ አባባ ውስጥም መናሃሪያቸው ሆና ፍሬ እያፈራች ትገኛለች፡፡
የአንበሳውን ድርሻ (100 %) የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ዕድሜ ከሰጠው ግብጽ ውስጥ እንደነበረው “የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ” የፕሮተስተንት እና እስልምና ውህድ አድርጎ ሕገ-መግስቱን ከሼሪያ ህግ ቀስ በቀስ እንደሚያዋህደው ጥርጥር የለውም።
“በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሚል ጥያቄ ላይ ደረሰ………… ነገስ ጥያቄው ምን ይሆን? ያኔ ከሦስት አመት በፊት በዘመነ ሃይለማርያም ደሳለኝ የነበረው እስላሞች ውከላ ላሳያችሁ፡-
ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus (ጴንጤ) እምነት ተከታይ ነው ፤ ምክትሎቹ ሦስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ውስጥ ሁለቱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ነበሩ ፡፡ የምክር ቤቱ ቁንጮ አባ ዱላ ገመዳ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው ፤ የኢህአዴግ ጽ/ቤት አላፊም ሙስሊም ነው፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ከተመረጡ 169 የህዝብ ተወካዮች ከ70 በላዮቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ፤ (ምንጭ ፡-የምክር ቤቱ ድረ-ገጽ http://www.hopr.gov.et/HPR/faces/c/mps.jsp) ፤
በጠቅላላው ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ከ547 መቀመጫ ውስጥ ከ220 በላይ የእስልምና ተከታዮች ናቸው:
ካሉት 16 ቋሚ ኮሚቴዎች
(1)-አቶ ሳዲቅ አደም የሕግ፤ የፍትህና አለስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፤
(2)-ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤
(3)-ወ/ሮ አይሻ እስማኤል የባህል፤ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙኃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ፤
(4)-ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሊቀመንበር ፤
(5)-አቶ መሐመድ አብዶሽ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤
(6)-አቶ መሐመድ ዩሱፍ አርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፤
(7)-ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር
በመሆን ካሉት 16 ቋሚ ኮሚቴዎች ሰባቱን (7ቱ) እስላሞች ናቸው?
በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የሚቆጣጠሩት ፤ በም/ቤቱ የአማካሪ ኮሚቴ አባላት የ21 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ዘጠኙ (9ኙ) ሙስሊሞች ናቸው።
እስላሞቹ ይህንን ሳይበቃቸው “እስካሁን ድረስ ችለን እንጂ ተቻችለን አልኖርንም” የሚለው ጎንደር ላይ የተከሰተውን ሁለት አስመልክቶ የትናንትናው መፈክራቸው ያስደመጡንና ያስነበቡን ስንመለከት ዛሬም በዘመነ አብይ አሕመድ “ምክር ቤት” ተብየው በአክራሪ እስላማዊ ኦነግ” ተመራጮች የተሞላው ምክር ቤት ከዚህ በላይስ እንዴት አድርገው መውረር ነው የፈለጉት?
ታዲያ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ያስነበቡን “እስካሁን ድረስ ችለን እንጂ ተቻችለን አልኖርም! ፋኖ ይደምሰስ! ፋኖ ሌባ! …አላህ ወ አክበር!…” የሚለው መፈክራቸው ስናደምጥ እስላሞቹ አላማቸው ምን ድነው? ብለን መጠየቅ አለብን።
እነዚህ ሰዎች ትንሽ ቢፍቋቸው ጥያቄያቸው ሌላ ሆኖ እንደሚገኝ ልናውቅ ይገባል፡፡ያንቀላፋ የሚመስለው ጽንፈኛው የውሃቢው ቡድን” ሰበብ የማሽተት ሱሱ ተነስቶበት “ፋኖ ይደምሰስ “ ፋኖ ሌባ” ሲል ዓላማው ምንድነው? ጂሃዲሰቱ በየከተማው ድክመት አለ በተባሉ አካባቢዎች እሳት እየጫረ በየሰላማዊ ሰልፉ የሚያስተጋባው “ፖለቲካዊ ድምጽ” ማቆም አለበት።
ጨርሻለሁ!
ጌታቸው ረዳ
ETHIOPIAN SEMAY