ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)
‹‹በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ተኩል ውስጥ፣ ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች በማያባራ ጦርነት ያስጨረሰው የስልጣን ሱሰኞች የኤርትራው የኢሳያስ መንግስትና ካቢኔው፣ የኢትዮጵያ የአብይ መንግሥትና ካቢኔው፣ የትግራይ የደብረፂዮን መንግሥትና ካቢኔው፣ የኦሮሚያ የጃል ሽመልስ አበዲሳ መንግሥትና ካቢኔው በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መታገል ጊዜው አሁን ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለመታደግ ‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!›› “Though the war’s true toll is impossible to know, researchers from Belgium’s Ghent University estimate as many as half a million people have died so far: between 50,000 and 100,000 from the fighting, 150,000 to 200,000 from starvation and more than 100,000 from the lack of medical attention.” ………………………………………..(1)
የቤልጅየም ገንት ዩኒቨርሲቲ አጥኝዎች መሠረት ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ እስካሁን ድረስ እንደሞተ ተገምቶል፡፡ከ ሃምሳ ሸህ እስከ መቶ ሽህ ሰዎች በጦርነቱ፣ ከመቶ ሃምሳ ሽህ እስከ ሁለት መቶ ሽህ ህዝብ በድርቅና ርሃብ፣ እንዲሁም መቶ ሽህ ህዝብ የህክምና እጦት የተነሳ እንደሞቱ ገምተዋል፡፡ በጦርነት ወንጀል፣በስብአዊ መብት ጥሰቶችና በዘር ማጥፋት፣ በዘር ማፅዳት ወንጀል፣ በሴቶች መድፈር ፣በሲቪል ሰላማዊ ሰዎች ግድያ የረድኤት ምግብና መድኃኒት እንዳይደርስ በማድረግ ወዘተ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥትና የኤርትራ መንግሥት ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ በትግራይ፤ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው በቅደም ተከተል፤
1ኛ/ ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት ግንባር ሆነው የገዙ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴድ በዋነኝነት አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሎቹ ም/ሊቀመንበሮች እና ካቢኔያቸው ውስጥ በፊትና አሁን የሠሩ ሁሉ፤ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
2ኛ/ ህወሓት፣ በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ እስከአሁን ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡ የህወሓት ኃይል መቐለን ተቆጣጥሮ፣ ህወሓት የጦር አበጋዞች ጥቃቱን በመቀጠል ወደ አማራና አፋር ክልሎች ወረራ ፈፀመ ፡፡ የወያኔ ወታደሮች ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ ለተፈናቀለው ህዝብ ስቃይ የደብረፂዮን መንግሥት በዚህ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ ተጠያቂ ናቸው፡፡
3ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጀምሮ እስከ ተጠናቋል በተደጋጋሚ ጊዜ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው የህዝብ እልቂት፣ ሞት፣ መደፈርና ለተፈናቀለው ህዝብ ስቃይ ሰቆቃ፣ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
4ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ ለተፈናቀለው ህዝብ ስቃይ እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው፡፡ ለዳግም ጦርነት በዝግጅት ላይ ናቸው!!! ለዚህም ነው ይህ ጦርነት እጅግ አሳዛኝ እጅግ መራራና አሰቃቂ የሚሆነው፡፡ ‹‹ በሁለቱ ተፋላሚዎች የባህር ማዶ ሃገራት ዝቅተኛ ተፅዕኖ እርቅና የሠላም ድርድር ሂደቱ ውጤቱ ደካማ ነው፡፡ የዓለም ህብረተሰብና አገሮች ዋነኛ ትኩረት በዩክሬንና በራሽያ ላይ ሆኖል፡፡ በኢትዮጵያ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱ የቆመ ቢመስልም፣ በእርስ በርስ ጦርነቱ ተፋላሚዎቹ ያላቸው ብቸኛ ምርጫ ለዳግም ጦርነት ዝግጅት ብዙ የውጊያዎች ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡›› “There is little prospect of progress toward reconciliation and peace without more outside pressure. But with the world’s attention focused on Ukraine and Russia, there is every chance that both sides in the Ethiopian civil war will use the stalemate to rearm for still more fighting.”
‹‹መቼም የትም አይደገም›› “Never Ever Again!!!”
በዚህ ጦርነት የማን ልጆች ናቸው የሚሞቱት? ለምንስ ዓላማ? የደሃው ህዝብ ልጆች በዚህ ጦርነት ተማግደዋል፣ የሹማምንቶቹ ልጆች ውጭ አገራት ትምህርታቸውን ይከታተላሉ፡፡ የዶክተር ደብረፂዩን፣ የጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ልጆች በሃገረ አሜሪካ ይኖራሉ፡፡ የብልፅግና ባለሥልጣኖች ልጆቻቸውን ውጭ አገራት ልከው ያስተምራሉ፡፡ ለእነሱ ሥልጣን ሲባል ሚሊዮን የድሃ ልጆች በጦርነት ይማገዳሉ፣ ይሞታሉ፣ አካላተ ጎዶሎ ይሆናሉ፡፡ ብዙ ሽህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በጦርነቱ ህይወተቸውን አጥተዋል፡፡ የህወሓት ፋሽስት መሪዎች ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚደርሱ የህክምና ዶክተሮችና ማህንዲሶች ህይወት አስቀጥፈዋል፡፡
የብልፅግናም ፋሽስት መሪዎች በሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ብዙ ወጣቶች በከንቱ እንዲሰው አድርገዋል፣ ካዛ ጦርነት የተረፉትን ፋኖዎች በግፍ ለመግደል ቆምጠዋል፡፡ የእምዬ ኢትዮጵያ መሬት የትም አይሔድ፣ አንገታችን ተቆርጦ እንዴት እኖራለን! ሉን የነበረው የኤርትራ መሬት ተቆርሶ አልሸፈተም፣ ዛሬም እዚያው ነው፣ በስልጣን ሱሰኞች በግፍ የተለያዩት የሁለቱ ሃገሮች ህዝቦች ግን ዛሬ በፍቅር ተገናኝተዋል፡፡ ነገ የትግራይና የኢትዮጵያ ህዝብ በእናንተ መቃብር ላይ ዳግም በፍቅር አብሮ ይኖራል፡፡ የኢሳያስ፣ የደብረፂዮንና አብይ ለሥልጣናቸው ሲሉ ምን ያህል ሰዎች መሠዋት አለባቸው? የሞቱትን ልጆች ዳግም አናገኛቸውም፣ የምንጣላበት መሬት ባድማ፣ ሽራሮ፣ ወልቃይት፣ ራያ ወዘተ የደም መሬቶች ግን እዚያው ናቸው?
‹‹Land to the Tiller›› to ‹‹Land to the Invester››
በዓለም አቀፍ ንግድና ኢኮኖሚ እድገት መሠረት ከ‹‹መሬት ላራሹ›› ወደ ‹‹መሬት ለኢንቨስተሩ!!!›› ተዘዋውሮል፡፡ በኢትዮጵያ ሦስት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለባህር ማዶ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ቻይና ወዘተ ተሰጥቶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ የግሎባላይዤሽን ትዝታ ነው፡፡ የዓለም ኃብት የተያዘው በጥቂት ኃብታሞች ነው፡፡ የአዲስ አበባ መሬት የተያዘው በውጭና በሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ነው፡፡ በዩናይትድ አረብ ኢሚሬቶች የለገሃር ፕሮጀክት፣ የቻይና ኢንቨስተሮች፣ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ የሼህ አላሙዲን ወዘተ ኢንቨስተሮች ኃብት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የወርቅ ማዕድን ሁሉ የተያዘው በእንግሊዝ፣ በቻይና፣ በግብፅ፣ በአላሙዲን የኃብት ይዞታ ነው፡፡ ገንዘብ ያለው ኢንቨስተር በነዚህ የጦርነት ቀጠናዎች ላይ ባድማ፣ ሽራሮ፣ ወልቃይት፣ ራያ ወዘተ ኢንቨስተሩ በሠላም የማልማት መብትና ሰው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መሥራት መብቱ ከተጠበቀ፣አብሮ ማልማት ይቻላል፡፡ ወልቃይቴ በፍቅር ማንም መጥቶ ቢያለማ የፍቅር ሃገር ነው፡፡ የአማራና የትግራይ ህዝብ በእራሱ ሽማግሌዎች ይታረቃል፡፡አብይና ደብረፂዮን ከነጭፍሮቻቸው ከሠላም አደራዳሪነት ይወገዱ እንላለን፡፡ የውጭ ኢንቨስተር እንዲያለማ እየጋበዝን የሃገር በቀል ኢንቨስተሮችን ሃብት በሻሸመኔ፣ አርሲ፣ አጣዬ፣ ጂማ፣ ወዘተ ማውደምና የሰው አንገት ማረድ ሰው ሰው ያልሸተተ አረመኔዊ ድርጊት ነው፡፡ ላለፉት አራት ዓመታት በኦነግ የአማራው ህዝብ መታረድ የፌዴራል መንግሥት መሪ አብይና በሌሎች ክልሎች አለማውገዝና ዝምታ አንድ ቀን ያስጠይቃል፡፡ ሰው እንዴት ይታረዳል፣ የሴት ጡት እንዴት ይቆረጣል!!!
ሰው ሰው የሸተተ የሠለጠነ ሰው አስተሳሰብ መመሪያችን ማድረግና በፍቅር በመኖር ጦርነት በቃን በማለት በሚያጣሉን መሪዎቻችን ላይ ማመፅ ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ አመፅ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማዎች ማቀጣጠል አለብን፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች ሞተዋል!!! ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጁ ነው ልናስቆማቸው ይገባል!!! ወላጆች ጦሪ ቀባሪ የተማሩ ልጆቻቸውን በጦርነት ተነጠቁ፣ ጦርነት በቃን!!! ‹‹መቼም የትም አይደገም›› “Never Ever Again!!!” በማለት የእናቶች ዕንባን እናስቁም!!! አንድ ህፃንን ለማሳደግ ስንት ዓመታት የደከሙ እናቶችን እኛ ተማርን በተባልን ልጆቻቸው የደም ዕንባ አስለቀስናቸው፡፡ እህቶች፣ እናቶችና ህፃናቶች በግፍ ተደፍሩ፡፡ የደም እንባ በደም መሬት ይብቃ!!! በዓሉ ግርማ እንደ ሞተው አባቴ ናፈቀኝ፣ ዛሬ ባይኖርም ድሮ ነግሯን ነበር፣
‹‹አሸዋ ውስጥ ተቀብረው የቆዩ ሁለት የሰው ጭንቅላት አጥንቶች አግኝቼ እየተመለከትኩ ሳስብ ነበር የቆየሁት፡፡ በመጨረሻ ሁለቱን አጥንቶች አስተያየሁ፡፡ የትኛው ይሆን የቱ? አንዱን ከሌላው ለይቼ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ሁለቱም አንድ ዓይነት ቅርፅ ያላቸው የኢትዮጵያዊያን ጭንቅላት አጥንቶች ነበሩ፡፡ ሁለቱንም አጥንቶች ካገኘኃቸው ሥፍራ መልሼ በጥንቃቄ አሸዋ ካለበስኳቸው በኃላ እያዘንኩ ወደ መኪናየ ስሄድ›› ኦሮማይ፣ በዓሉ ግርማ
“[I came late as I spent hours looking at two skulls that I got in the sand. I looked at the two skulls. I couldn’t recognize which skull belonged to whom? Both were the skulls of two Ethiopians that have similar structures. I put the two skulls in the sand carefully and covered them with sand and with a deep sense of grief I went to my car. ] Like Tsegaye, the character, Colonel Wolday, who is the army chief of the strategic mountain 1702, is aware that the people who are engaged in the fighting are the people of one Ethiopia. The war is betwe en the children of Ethiopia as read below (1983: 293):”
‹‹ከነዚህ ሰዎች ጋር አንድ ላይ ብንቆም ይህን ገዢ መሬት ይዘን እሚበግረን የውጭ ጠላት ከቶ አይኖርም ነበር፡፡ ሁለታችንም ወኔ ለወኔ የምንተዋወቅ ያንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ነበርን፡፡ ያለመታደል ነው፡፡ ለዚህም ነው ይህ ጦርነት እጅግ አሳዛኝ እጅግ መራራና አሰቃቂ የሚሆነው፡፡›› “[With such great landscape, no foreign enemy would win us if we stand together with these people. All of us are the children of Ethiopia who can understand each other’s bravery. We are really unfortunate. That is the reason for the war is to be very tragic and bitter.] Therefore, all such comments could have contributed to the dismissal of Bealu from his job and his disappearance.”
በአብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ በሱዳን ተወራለች፣ በኤርትራ ተወራለች፣ በህወሓት ጦርነት፣ በኦነግ ሸኔ ጦርነት በየቦታው ተለኩሶል፡፡ ብልፅግና እያሉን አገር ገንቢው ግማሽ ሚሊዮን ወጣቶች በጦርነት ተማገዱ፡፡ ብዙ ሽዋች አካለ ስንኩል ሆነዋል፡፡ ሚሊዮኖች ቀያቸውን ለቀው በመጠለያ ካንፖች ሠፍረዋል፡፡ በድርቅና ርሃብ ሚሊዮኖች የሚበሉትና የሚጠጡት አጥተዋል፡፡ የቤት እንሰሳቶች አልቀዋል፡፡ ወያኔና ብልፅግና ህዝቡ እርዳታ እንዳይደርሰው በማድረግ ይወነጃጀላሉ፡፡ አውሮፓ አገራቶችና አሜሪካ እህል ይሰፍሩልናል፣ እኛ መሣሪያ እየወለወልን ወንድም ለወንድም እንገዳደላለን፡፡ ሁለቱም ወገኞች ለዳግም ጦርነት በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ መጀመሪያ አገራችንን ከውጭ ጠላቶች በህብረት ሆኖ መከላከል በተገባ ነበር፡፡ ወያኔና ብልፅግና ለስልጣን ሱስ ሲሉ ወጣቱን በጦርነት ይማግዱታል፡፡
ፖለቲካ የማያውቁ የሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞቹ ለግማሽ ክፍለ ዘመን እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡ በኢትዩጵያ ውስጥ በዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት በጉጠኛነት፣ በዘውገኛነትና በዘር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች መኃል፤ የኢህአዴግ ህወሓት (የትግራይ)፣ ኦህዴድ (የኦሮሞ)፣ ብአዴን (አማራ)፣ ደቡብ (ደኢህዴን) ወዘተ በዘርና ቌንቌ ላይ የተመሠረተ የማንነት መታወቂያ የሚሠጡ የንግድ ድርጅት ጋር ይወዳደራሉ፣ በዛም የዘርህ ግንድ ተጣርቶ መታወቂያ ይሰጥህና በጀት ተደልድሎልህ፣ ሥራና ደሞዝ ይቆረጥልሃል ማለት ነው፡፡
ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ ‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርዓት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ የዘርና ቌንቌ ያለት ሃገር በመሆኖ ወደ ሰማንያ መንግሥታት ምሥረታ መሸጋገራችን አይቀሬ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም በኢኮኖሚ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት አመችነት፣ በጂኦግራፊያዊ አከላለል ቢከፋፈል ግጭት ይጠፋል፡፡ ክልሎችን በዘር እና በቌንቌ በድንበር እየለያዩ መለየት የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ፣ የሃዲያ፣ ወዘተ ‹‹ክልላዊ ብሄራዊ መንግሥት›› በማለት ድንበርና ወሰን ማካለል ወደማያባራ የድንበር ግጭትና ጦርነት ህዝብን ይከተዋል፡፡ ዛሬ የምናየው በየቦታው የተከሰተው የህዝብ መፈናቀል የህወሓት/ኢህአዴግ የፈለሰፈው በዘር እና በቌንቌ ላይ የተመሠረተ የፊዴራል መንግሥት ሥርዓት አወቃቀር ነው እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በመላ ሃገሪቱ ከአንዱ ግዛት ወደ አንዱ ግዛት በነፃነት ተዘዋውሮ የሚሠራበትና የሚኖርበት ወርቃማ ዘመን አከተመ፡፡ ኦህዴድ ብልጽግና ተረኛና ዘረኛ አገዛዝ፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የቀሰቀሰው ኦሮሙማ የመስፋፋት ጦርነት ከአማራ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ክልሎች ጋር የድንበር ግጭት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ!!!
ምንጭ
(1)The World’s Deadliest War Isn’t in Ukraine, But in Ethiopia/By Bobby Ghosh | Bloomberg/March 23, 2022 EDT