ዛሬያችንም ሆነ ነጋችን በፈጣሪያችን በክርስቶስ እጅ ናት ፡፡ እኛ ሰዎች በጊዜ ፣ በቦታና በሁኔታ እንገደባለን ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜና ሰዓት ምንም ሳይገድበው ከሁላችን ጋር የሚገኘው ሁሉን ቻዩ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው ፡፡ ወልድን ያየ አብን አይቶታልና ፤ የስራውንም ግሩምነት ተመልክቷልና ፤ ከቅዱስ መጸሀፍቱም ተረድቷልና ፤ ነፍሱን ለመድኃኒዓለም ሰጥቶ እስከሚጠረው ድረስ ፈጣሪውን እያመሰገነ ይኖራል ፡፡ ሰዎች ዛሬ እንሙት ነገ ፈፅሞ አናውቅም ፡፡ ይኽንንም ዝንጋታችንን ፈጣሪ ተገንዝቦ ; በመፀሐፍ ቅዱስ በሉቃስ 12 እንዲህ ሲል ምክሩን በምሳሌ እንደሰጠን አስታውሱ ፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤው ሞት መኖሩን በተጨባጭ የሚሳውቅ ነው ፡፡ እናም ያለፀፀት ለመሞት ዛሬ በትንሣኤው ቀን እኛም ከይሁዳዊ ፀባይ እንፋታ ፡፡ በበርባን ፀባይ መጓዛችን ያብቃ ፡፡
13 . ከሕዝቡም አንድ ሰው፦ መምህር ሆይ፥ ርስቱን ከእኔ ጋር እንዲካፈል ለወንድሜ ንገረው አለው።
14 .እርሱም፦ አንተ ሰው፥ ፈራጅና አካፋይ በላያችሁ አንድሆን ማን ሾመኝ? አለው።
15 . የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው።
16 . ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት።
17 .እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ።
18 .እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤
19 . ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።
20 . እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው።
21 .ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው።
ለእኛ ግን እንዲህ ሲል ጌታ ይመክረናል ።
22 . ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ ።
23 .ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና።
24 . ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም፥ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፥ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተስ ከወፎች እንዴት ትበልጣላችሁ?
25 .ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?
26 . እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ?
27 . አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም።
28 . እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን በሜዳ የሆነውን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?
29 . እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤
30 . ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል።
31 . ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።
ሉቃስ 17
አሥራሰባት ደግሞ ሥለ ትእግሥት ና ይቅርታ ይነግረናል ። በዓለም በግለሰብም ሆነ በመንግሥታት ደረጃ ይኼ ይቅር ባይነት እምብዛም አይሥተዋልም ።
1 .ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤
2 . ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።
3 . ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፦ ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።
4 .በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ፦ ተጸጸትሁ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።
የፅሑፌ ማሣረጊያ የኢየሱስ ሥቅለት ና ትንሣኤ ነው ።
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ ሰውን ከአዳም ና ሄዋን ሞት ለማዳን እና ወደ ዘላለም ህይወት ለመመለስ ፣ እንደ ሰው ኖሮ ፣ ሰው ሊቋቋመው የማይችለውን ሥቃይ ሥለ ሰው ሐጢያት ተቀብሎ ፣ በመሥቀል ላይ ተሠቅሎ ፣ በሦሥተኛው ቀኑ ከሞት ተነሥቶ የዘላለም ህይወት እንዳጎናፀፈን ከሉቃሥ ወንጌል ምዕራፍ 23 እና ጥቂቱን እንሆ ብዬ ፅሑፌን እቋጫለሁ ።
ሉቃስ 23
15 . ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም፤
16_17 . እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ። በበዓሉ አንድ ይፈታላቸው ዘንድ ግድ ነበረና።
19 .እርሱም ሁከትን በከተማ አንሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ ነበር።
20 .ጲላጦስም ኢየሱስን ሊፈታ ወድዶ ዳግመኛ ተናገራቸው፤
21 .ነገር ግን እነርሱ፦ ስቀለው ስቀለው እያሉ ይጮኹ ነበር።
22 . ሦስተኛም፦ ምን ነው? ያደረገውስ ክፋት ምንድር ነው? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው።
23 . እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል በረታ።
24 .ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት።
25 . ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
ሉቃስ 24
23 . ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፦ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር።
24 .ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።
25 . እርሱም፦ እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤
26 . ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።
27 .ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።
28 . ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።
29 . እነርሱ፦ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።
30 . ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤
31 .ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።