Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በስልክ ለማዳመጥ610-214-0200 አክሰስ ቁጥር 729369#
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ የካቲት 3 ቀን 2005 ፕሮግራም
<<በኢቲቪ በሙስሊም መሪዎች ላይ የተቀናበረው ፊልም ዓላማ ፍርሃት መፍጠርና በተለይ ከቀድሞ ጀምሮ በሰላም የኖሩትን ክርስቲያንና እስላምን ለመለያየት ነው።በተለይ የክርስቲያኑ ህ/ሰብ ሙስሊሙን እንዲጠራጠር ለማድረግ መተማመን እንዳይኖር ያለመ ነው። ይህን ፊልም አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝቡ ዓላማውን አውቆታል።ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖችና ራሳቸው ሙስሊሞችን ለመለያት መሆኑን ተረድቶ አልተቀበለውም …>> ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
<..የካቲት 12 የኢትዮጵያውያን የሰማዕታት ቀን ለ76ተኛ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊከበር ነው። የጣሊያን መንግስት በአዲስ አበባ በሶስት ቀን 30 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል። …ይህ ወንጀል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰነድ እንዲመዘገብና ለደረሰውም ጉዳት የጣሊያን መንግስት ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል ለመጠየቅ በተለይ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያንን ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ መታሰቢያ መስራታቸውን ለመቃወም ነው …> አቶ ኪዳኔ አለማየሁ በጣሊያን መንግስት ላይ ኢትዮጵያውያን ሊያደርጉት ያሰቡትን ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ከሚያስተባብሩት አንዱ (ሙሉውን ቃለ መጠይቅ አድምጡ)
ዜናዎቻችን
ሲፒጄ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ተዘግቶ የነበረው ክስ ተከፍቶ መክሰስ የተፈለገው አገዛዙ ጥቂት የሚተቹ ድምጾችን ሙሉ ለሙሉ ለማፈን ነው ሲል አወገዘ
በፒያሳ ታሪካዊ ቤት በእሳት ተያይዞ የሰው ሕይወት ጠፋ
ፒያሳ የሚገኘው እሳት አደጋ እሳቱ ከጠፋ በሁዋላ መምጣቱ በነዋሪዎችና በአካባቢው ፖሊሶች ላይ ቅሬታ ፈጠረ
የኢትዮጵያ መሬት ነጠቃ አሁንም የዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆነ
የኢቲቪ የታሰሩ የሙስሊም መሪዎችን ለማጥላላት የሰራው ፊልም የሕግ ጥሰት አለበት ተባለ
ሁለት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከሚሰሩበት ፓርኪንግ 1.4 ሚሊዮን ዶላር አጭበርብረው ለግላቸው በመውሰዳቸው ተፈረደባቸው
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አገዛዙ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ለማጋጨት በኢቲቪ ያቀረበው ፊልም ሕዝቡ እንዳልተቀበለው ገለጹ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን